(ዘ-ሐበሻ) ዘ-ሐበሻ ትናንት እሁድ በዘገበችው መሰረት ለ3 ጊዜያት የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር:: ዛሬ ከአዋሳ አካባቢ ያነጋገርናቸው ወገኖች እንደገለጹልን ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ በ24 ሰዓታት ውስጥ ለ6ኛ ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጡ ተከስቷል::
ይህ ዜና ከተጠናከረበት 20 ደቂቃ በፊት ለ6ኛ ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጡን ያስታወቁት ዘ-ሐበሻ ያነጋገረቻቸው ወገኖች በደረሰው አደጋ በርካታ ወገኖች ወደ ሆስፒታል እንደተወሰዱ… በፎቅ ላይ የሚኖሩ ወገኖችም ወደ ምድር መወረዳቸውን ነግረውናል::
በሐዋሳ ነዋሪው በከፍተኛ ሁኔታ ተደናግጦ ይገኛል::
ለሐዋሳ እንጸልይ!
No comments:
Post a Comment