Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, January 7, 2016

አዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች ከጥር 6 እስከ ጥር 8, 2008 የሚካሄድ ሕዝባዊ ተቃውሞ !!


በተጠቀሱት ቀናቶች ሁላችንም በያለንበት ቦታ በመሆን የአገዛዝ ስርዓቱ በህዝብና በሃገር ላይ እየፈፀም ያለውን ወንጀል ፣ ህጋዊ ጥያቄ ባቀረቡ ዜጎች ላይ አየተወሰደ ያለዉን እስራት ና ግድያ ፣ የሃገራችን ድንበር ለሱዳን መንግስት ተቆርሶ መሰጠቱን እንቃወማለን ።
ተቃውሞዉ የሚገለፀዉ በኡኡታና በኳኳታ ይሆናል ።
ኡኡታ ፦ ሁላችንም በያለንበት ( በመኖርያ ደጃፍ ፤ ጊቢ ዉስጥ ፣ በስራ ቦታ ፣ በመንገድ ላይ …..ወዘተ ኡኡታ ማሰማት )
ኳኳታ ፦ በአቅራቢያችን ድምፅ ማሰማት የሚችሉ ማንኛዉንም ነገሮች ማስጮህ ( ማብሰያ መመገቢያ ቁሳቁስ ፣ የቆርቆሮ የብረት አጥርና በር ፣ ተሽከርካሪዎች ፣ የተለያዮ ሰራዎች ማከናወኛ መሳሪያዎች ፣ በመንገድ በግርግዳ ተለጣፊ ወይም ተንጠልጣይ ማወስታወቂያዎች፣ የብረት ምሶሶዏችና ድልድዮች…….ወዘተ በመደብደብ በማጋጨት ማስጮህ )
እነዚህ ተግባራቶች በተመሳሳይ ሰዓት ከተለያየ ስፍራ ለመፈፀም የሚያመቹ ፣ አንድ ላይ መሰብሰብን የግድ የማይሉ ሲሆኑ ጨቋኙን የወያኔ ስርዓት ለማስወገድ አንቅፋት የሆኑብንን ፍርሃትና መለያያትን በቀላሉ የምንሰብርባቸዉ እንዲሁም የእምቢተኝነት መግለጫዏች ናቸዉ።
የጊዜ ሰሌዳና ተግባር ፦
ጥር 6 ዐርብ ጠዋት 4 ሰዓት ከሰዓት በኃላ 7 ሰዓት ምሽት 2 ሰዓት ጀምሮ ከ 10-15 ደቂቃ ኡኡታ ….ኡኡታ
( የቀኑ መርሃ ግብር ከጁምዐ ሶላት በፊትና ሶላት ከተጠናቀቀ በኃላ ይሆናል )
ጥር 7 ቅዳሜ ጠዋት 4 ሰዓት ከሰዓት በኃላ 7 ምሽት 2
ሰዓት ጀምሮ ከ10-15 ደቂቃ ኳኳታ…..ኳኳታ
ጥር 8 እሁድ ጠዋት 4 ሰዓት ከሰዓት በኃላ 7
ሰዓት ጀምሮ ከ10-15 ደቂቃ ኡኡታ….ኡኡታ
( የቀኑ መርሃ ግብር የቤተክርስቲያኖች ፀሎት ከተጠናቀቀ በኃላ ይሆናል )
ጥር 8 እሁድ ምሽት ከ2 ሰዓት ጀምሮ ከ10-15 ደቂቃ ኡኡታና ኳኳታ … ኡኡታ ኳኳታ በመቀላቀል እምቢተኝነታችንን ገልፀን የመጀመሪያዉ ዙር የተቃዉሞ መረሃ ግብራችን ይጠናቀቃል።
አስተባባሪ ኮሚቴው ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials