ሕወሓት የሚመራው መንግስት በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞች ውስጥ እየወሰደ ያለውን እርምጃ የሚደግፍ እና የሕዝቡን ጥያቄ የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በተለያዩ ከተሞች ሊጠራ መሆኑ ተሰማ:: ይህም ሆን ብሎ ሕዝብን ከሕዝብ ለማናቆር የተሰራ ደባ ነው ሲሉ ታዛቢዎች ገለጹ::
ምንጮች እንደሚሉት ሕወሓት የሚመራው መንግስት በኢትዮጵያ ላይ በስፋት የተያያዘዉን የመሬት ቅርምት በመቃወም ወደ አደባባይ የወጡ ወገኖችን በተለይም በኢትዮጵያዊ ኦሮሞ ተወላጆች ላይ እየወሰደ የሚገኘዉን “ድብደባ፣ እስራትና፣ ግድያ በመደገፍ እርምጃዉ ተመጣጣኝና ትክክለኛ ነዉ; እንዲሁም የማስተር ፕላኑን የሚቃወሙትም ጸረ ልማት ኃይሎች ናቸው” በማለት በሃገሪቱ የተለያዩ ከተሞችና በተለያዩ አለም አቀፍ ሐገራት ሰልፍ ለመጥራትና ህዝብን ከህዝብ ቂም ለማቃባትና ደም ለማፋሰስ ዝግጅቱን ጨርሷል።
እንደምንጮቹ ገለጻ ከሆነ ይህን ሰልፍ ለማስፈጸም የዚህ ወንጀል ቀጥተኛ ተሰላፊ የሆኑት ካድሬዎችና የወያኔ የፖለቲካ ሰዎች እንዲሁም የአንድ ለአምስት አባላቱ ግዳጃዊ ትእዛዝ ተሰጥቷቸዋል:: በዚህም ግዳጃዊ ትእዛዝ መሰረት አዲስ አበባ፣ ባህር ዳር፣ ድሬዳዋ ቅስቀሳዉ ተጀምሯል::
ሕወሓት የሚመራው መንግስት ይህን ዓይነቱን ሰልፍ ለመጥራት ያሰበው አሁንም የኦሮሞን ሕዝብ ከሌላው ሕዝብ ለመነጠልና ሕዝብን ከሕዝብ ለማቃቃር እንደሆነ ሕዝብ ልብ ሊል ይገባል የሚሉት አንድ የፖለቲካ ታዛቢ ይህን የሕወሓት መንግስት ሕዝብን ከሕዝብ የማናከስ ተግባር እንዲህ ሲሉ ይገልጹታል:- “ኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ እናስተውል! ዛሬ በኦሮሞ ወጣቶች ላይ የፈጸመውን ነገ ህወሀት የቀረው ብሄረሰብ ላይ በግፍ እንደሚፈፆመው አልጠራጠርም:: የወንድሞቻችን ደም ነው የፈሰሰው:: የወያኔ መሳሪያ ከመሆን እንቆጠብ:: ምን ያረጉናል?.. ከነሱጋ ካልተባበርን ረሀቡንና ችግሩን ይኸው እያየንው ነው:: ከዚ የባሰ አይመጣም ::እነሱ ይጠፋሉ… እንኳን እነሱ የአለም አምባገነኖች ጠፍተዋል… መጨረሻ ህዝብ ነው የሚቀረው:: እባካቹ ትውልዱን ደም አናቃባ;;ው የወንድሞቻችንን ህመም አብረን እንታመም:: ህወሓት ገደል ጫፍ ላይ ነው ያለው:: ለምንድነው ገፍትረን ወደ መቃብሩ ማንጨምረው? ህወሓት እኛ አንድ እንዳንሆን በየሚያዛቸው ድህረ ገጾች,, በሰላማዊው ሰልፍ ህዝብን ለመቀስቀስ እየሰራ ነው:: አሁን በካድሬዎቹ በኩል ቤት ለቤት እየዞረ ኑ የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ ተቃውሙ ብሎ ሰላማዊ ሰልፍ ለመጥራት ዝግጅቱን ጨርሷል:: ልብ ያለው ልብ ይበል ሕዝቡም ይህን ሴራ ያክሽፍ!!”
No comments:
Post a Comment