Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, May 6, 2014

ሃሮማያ ዩንቨርስቲ የሃረር ካምፓስ ድጋሚ ሁለት ያልፈነዱ ፈንጂዎች ተገኙ

ሃሮማያ ድጋሚ ሁለት ያልፈነዱ ፈንጂዎች ተገኙ: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Harer‬ ‪#‎Oromoprotest‬‪#‎Haromaya‬
ሃሮማይ ዩንቨርስቲ የሃረር ካምፓስ በፖሊሶች ድንገት ተወሮ ነበር።ተማሪዎች ታርደው ተገኝተዋል ማን አረዳቸው?
የሃረር ነጋዴዎች አዲስ እና ወያኔ የለቀቀው ብሶት ተከስቷል ይላሉ። ሓረር ውሃና መብራት ናፍቃለች።
ምንሊክ ሳልሳዊ ፦ ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ሰበብ የፈነዳው የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ እስከዛሪ ድረስ ውጥረቱ እንደቀጠለ መሆኑ ይታወቃል ፡፤ የተቃውሞው ድባብ አሁንም አጥልቶባቸው ካሉ የምስራቅ ኢትዮጵያ ዩንቨርስቲዎች የሃሮማያ የድሬዳዋ እና የሃሮማያ ሃረር ካምፓስ ተጠቃሽ ናቸው።
በሃሮማያ ዩንቨርስቲ ባለፈው ሳምንት በኳስ ሜዳ ተሰብስበው በነበሩ ተማሪዎች ላይ በተወረወረ ቦምብ ተማሪዎች የሞቱ ሲሆን በርካቶች ቆስለው ሕክምና እየተከታተሉ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ ። ከዛም በተከታይ በዩንቨርስቲው ውስጥ ብሄርን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች ተከስተው ተማሪዎች መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን በአከባቢው እንዳይንቀሳቀሱ እየተደረገ መሆኑን ዘገባዎች ጠቁመዋል።
በትላንትናው እለት እና ዛሬ የደረሱን መረጃዎች እንደሚያሳዩት በሃሮማያ ዩንቨርስቲ ሃረር ካምፓስ ተቃውሞ ያሰሙ ተማሪዎች በፌዴራል ተከበው እንደተደበደቡ እና አሁንም ግቢው በፖሊስ ተወሮ እንደሚገኝ የሃረር ነዋሪዎች ገልጸዋል። የተወሰኑ ተማሪዎች ለሕይወታቸው በመፍራት ግቢውን በመልቀቅ በውጪ ቤት ተከራይተው መኖር መጀመራቸውን እንዲሁም በየቤተክርስቲያኑ ተጠልለው እንደሚገኙ ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል።
በትላንትናው እለት ዋናው ግቢ ሃሮማያ ዩንቨርስቲ ተማሪዎችን በጠዋት ስብሰባ የጠራው የወያኒው መንግስት ስብሰባው ላይ ጠንከር ያሉ ጥያቄዎች ያቀረቡትን እና እየተካሄደ ያለውን ፍጅት የተቃወሙትን እንዲሁም በመማር ማስተማሩ ሂደት ላይ ወያኔ እየፈጠረ ያለውን ችግር የተናገሩትን እንዲሁም ተቃውሞ ያሰሙ ተማሪዎችን ያላወገዙትን በግልጽ ከስብሰባው እያወጡ የክልሉ ፖሊሶች እንደደበደቧቸው የአይን እማኞች ተናግረዋል።
ያለፈው ያቀነባበረው ፍንዳታ አልበቃ ያለው ወያኔ በድጋሚ ለማፈንዳት ያቀዳቸው ፈንጂዎች ከሽፈው መያዛቸውን ከቦታው የተገኙ መረጃዎች ሲያሳዩ ፈንጂውን ይዘዋል ተብለው የተገኙ ተማሪዎች የኦሮሞ ተወላጆች ያልሆኑና ከመሃል ሃገር የሄዱ ተማሪዎች እንደሆኑ ምንጮቹ ሲያረጋግጡ የተያዙት ሁለት አባላት በመሃል ሃገር የሕወሓት አባል ሆነው የተመዘገቡበት መታወቂያ የተገኘባቸው ሲሆን አማርኛ ትግሪኛ እና ኦሮምኛ እንደሚናገሩ ታውቋል።
እነዚሁ ተማሪዎች ከነፈጂያቸው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ወዲያው ወደ አዲስ አበባ ለምርመራ ተብሎ የተላኩ ሲሆን ሲንቀሳቀሱበት በነበረው አከባቢ ሁለት ተማሪዎች ታርደው መገኘታቸውን የክልሉ ፖሊስ አረጋግጧል። ፖሊስም ይሁን ተማሪውች ታርደው የተጣሉ ተማሪዎች ፈንጂ ይዘው ከተገኙት ጋር ግንኙነት ሊኖረው ይችላል በሚል ጥርጣሪያቸውን ቢገልጹም የአከባቢው ፖሊሶች ወደ አዲስ አበባ የላኳቸውን ተማሪዎች መልሰው ለማግነት አለመቻላቸው ሲታወቅ በኳስ ሜዳ የፈነዳው እና ለዜጎች ሞት እን ቁስለት ምክንያት የሆነው ቦምብ ያፈነዳው ማን እንደሆነ እስካሁንም ምርመራው አለመጀመሩ ታውቋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials