የሃረር ነጋዴዎች አዲስ እና ወያኔ የለቀቀው ብሶት ተከስቷል ይላሉ። ሓረር ውሃና መብራት ናፍቃለች።
=================================================
በሸዋ በር አከባቢ እና በመብራት ሃይል አከባቢ ባለፈው ሱቃቸው የተቃጠለባቸው ነጋዴዎች ለ እያንዳንዳቸው በቆርቆሮ የተከፋፈለ እና አንድ ሜትር በአንድ ተኩል የሆነች መደብ የተሰጣቸው ሲሆን ቀሪው መሬት ክልሉ ለኢንቨስተሮች በሚል ሰበብ በሙስና ለባለስልጣናት የግል ጥቅም ለማዋል በመራወጥ ላይ ነው ሲሉ ነጋዴዎች አማረዋል። እንደበፊቱ ያለን የንግድ ሱቅ እንዲመለስልን እና እንድንገነባ ይፈቀድለን የሚሉት ነጋዴዎች ከአንድ አልጋ የምታንስ የበሬ ግንባር በምታክል መደብ ላይ ምን ዘርግተን ልንሸጥ ነው ሲሉ ብሶታቸውን አሰምተዋል።

መጀመርያ ከነበሩት እና ከተቃጠሉት ሱቆች በተጨማሪ የተሰሩ 150 ሰፋፊ ሱቆች ለባለስጣናት ቤተሰቦች እና ዘመዶች እንዲሁም ለአዳዲስ የመሃል ሃገር የመጡ ሰዎች የተሰጡ ሲሆን ቀሪ መሬቶች ለኢንቨስተር በሚል ሰበብ ዘረፋ ሊካሄድባቸው መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል። ለነጋዴው ወያኔ 50 ኪሎ ስንዴ እና ስኳር ከመስጠቱ ውጪ ምንም እርዳታ ያላደረገ ሲሆን የክልሉ ፕሬዝዳንት በነጋዴው ጉዳይ ላይ ምንም አይነት ነገር አልፈርምም በማለቱ ነጋዴው ከነቤተሰቡ እየተሰቃየ ይገኛል።
ሃረር ውሃና መብራት ናፍቋታል የሚሉን ነዋሪዎች ብሶታችንን አደባባይ ይዘን የወጣን ቀን ክልሉ ያበቃለታል ሲሉ እየዛቱ ነው። ባለፉት ወራቶች በክልሉ የውሃና የመብራት እጦት ከመስፋፋቱም በላይ ከነበረበት በ እጥፍ ብሶ እየታየ መሆኑን ነዋሪዎቹ ጥርሳቸውን ነክሰው ይናገራሉ። አዲስ አበባ ባቡር እና መንገድ እየዘረጋን ነው የሚል ልማታዊ ሰበብ ይሰጣል እዚህ ሃረር ደሞ የምን ልማታዊ ሰበብ ሊሰጠን ነው እንዲህ በመብራት እና ውሃ እየበደሉን ያለው ሲሉ ምሬታቸውን ያሰማሉ፡፤ ለወደፊት ለሚመጣው ልማትታለኝ በሰማይ እንድንለማመድ እያበረታቱን ከሆነ ይነገርን ሲል ህዝቡ አቤት ብሏል። በቀን ውስጥ ለ 2 ወይንም 3 ሰአታት ያህል ባቻ በጸሎት የምትቆየው መብርራ አሁን ጭራሽ እየጠፋሽ ሲሆን ውሃ በሃረር ከታየች ሳምንት አልፏታል ሲሉ ነዋሪዎቹ ይገልጻሉ።
በመልካም አስተዳደር እጦት የምትሰቃየው ሃረር ከተማ እንዲሁም በዘረኝነት በፍትህ እጦት እና በመሰረታዊ አገልግሎት በአድሎዋዊ አሰራር በስፋት የተንሰራፋበት ባለስልጣናት ከነዘመዶቻቸው በዘረፋ እና ሙስና የተጨማለቁበት መሆኑን ህዝቡ ይናገራል። ይህንን አምባገነን መንግስት በጋራ በአንድነት ለመገርሰስ ብዙ መስራት ይጠበቅብናል። #MinilikSalsawi
No comments:
Post a Comment