Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, May 16, 2014

Holy Synod in exile annual meeting started

በስደት ያለው ሲኖዶስ ጉባዔ የመጀመሪያ ቀን ውሎ የቀረበው አንድ ወጥ የሆነ ቃለአዋዲ ጸደቀ

የሃገር ቤቱ ሲኖዶስ በአዲስ አበባ የውጪው ሲኖዶስ በአሜሪካ የግንቦት ወር አጠቃላይ ጉባኤያቸውን እያደረጉ ይገኛሉ። በበስደት ላይ ያለዉ ህጋዊዉ ቅዱስ ሲኖዶስ የመጀመሪያዉ ቀን ዉሎ በአጭሩ ይህን ይመስላል።

በጉባኤው ላይ ስለ መንበረ ፓትርያሪኩ አጠቃላይ አስተዳደር በሰፊዉ ከተወያየ በኃላ ዉሳኔዎችን አሳልፏል።
በስደት ላለችዉ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድ ወጥ የሆነ ቃለ አዋዲ ተዘጋጂቶ የቀረበ ሲሆን ለዉይይት ቀርቦ ጠቅላላ ጉባኤዉ ተወያይቶበት «ቦርድ» የሚለዉ በህጉ ሰበካ ጉባኤ በሚለዉ ተተክቷል።
በጉባኤው ውስጥ የሚገኙት የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንዳስታወቁት በጉባኤው ላይ አዳዲስ አቢያተ ክርስቲያናት ወደ ህጋዊዉ ቅዱስ ሲኖዶስ መቀላቀላቸው ተገልጿል።
ጉባኤው “የካህናቱ ኑሮ የተሻለ እንዲሆን፣ በእዉቀታቸዉም ሁለገብ እንዲሆኑ ተግተዉ መማር አለባቸዉ በሚለዉ ጉባኤዉ በሰፊዉ ተወያይቶበታል” ያሉት ምንጮቻችን “ምእመናን በሃይማኖታቸዉ እንዲጸኑ ሀገራቸዉን በጸሎት እንዲያስቡ ጉባኤዉ በሰፊዉ ሲነጋገሩበት ውለዋል” ሲሉ መረጃውን አድርሰውናል።
በጉባኤው ውስጥም ሌሎች በህጋዊው ሲኖዶስ ውስጥ የሌሉ አብያተ ክርስቲያናት በስደት ወዳለዉ ሲኖዶስ እንዲቀላቀሉ ምን መደረግ አለበት? በሚልም ሰፊ ዉይይት አድርገዋል።
የቀጣዩን ቀን ውሎ እንመለስበታለን።

No comments:

Post a Comment

wanted officials