Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, April 24, 2016

11 የአሜሪካ ሴናተሮች ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አፈና አወገዙ


የኢትዮጵያ መንግሥት በሲቪል ማኅበረሰብ ላይ እያካሄደ ነው ያሉትን አፈና እንደሚያወግዙ አሥራ ሁለት የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት የሆኑ እንደራሴዎች ለምክር ቤቱ የውሣኔ ሃሣብ ረቂቅ አቅርበዋል።



በሕገመንግሥት የተረጋገጡ መብቶቻቸውን እየተጠቀሙ ተቃዋሞዎቻቸውን በሰላማዊ መንገድ በሚገልፁ ሰልፈኞች፣ በጋዜጠኞችና በሲቪል ኅብረተሰብ አባላት ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ግድያ የታከለበት የኃይል እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የገለፁ የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ ወመሰኛ ምክር ቤት አባላት አድራጎቱን በብርቱ እንደሚያወግዙ ያሳወቁበትን የውሣኔ ሃሣብ ነው ይፋ ያደረጉት።

ሰነዱን ያዘጋጁትና የሴናተሮቹን ተቃውሞ የመሩት ዴሞክራቱ የሜሪላንድ አንጋፊ ሴናተር ቤን ካርዲን እና ሪፐብሊካኑ የፍሎሪዳው ሴናተር ማርኮ ሩቢዮ ናቸው።



ሪፐብሊካኑ የፍሎሪዳው ሴናተር ማርኮ ሩቢዮ /ፋይል ፎቶ/

የውሣኔ ሃሣቡን የያዘው ሰነድ የኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች ሲቪሎችን መግደላቸው በተገለፀበት በአሁኑ ሁኔታ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሃገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር የገባውን የደኅንነት ውል መልሶ እንዲፈትሽ ይጠይቃል።

የሴናተሮቹ የውሣኔ ሃሣብ መግለጫ ሰነድ ረቂቅ አክሎም የኢትዮጵያ መንግሥት እየወሰዳቸው ያሉ የኃይል እርምጃዎችን እንዲያቆምና አጥፊዎች እንዲጠየቁ ያሳስባል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials