Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, April 13, 2016

ቤልጂየም ባለባርኔጣውን ተፈላጊ ያዘችው

big deal
ትናንት አርብ በቤልጂየም የተያዘው የሽብር ድርጊት ተጠርጣሪ በብራስልስ አየር መንገድ የቦንብ ጥቃት አድርሰው ከነበሩት ሁለት ወንድማማቾች አጠገብ የነበረው ባለባርኔጣው እርሱ መሆኑን ለፖሊስ በሰጠው ቃል መግለጹን አቃቢያነ ህጎች ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡
አቃቤ ህጎቹ ሙሀመድ አብሪኒ ለመርማሪዎች በሰጠው ቃል በብራሰልሱ የመጋቢት ወር የቦንብ ጥቃት ተሳትፎ ማድረጉን አምኗል ብለዋል፡፡ ተጠርጣሪው በህዳር ወር 130 ንጹሐን ለተገደሉበት የፓሪሱ የሽብርተኞች ጥቃት እጁ እንደነበረበትም ይነገራል፡፡
አብሪኒ በተያዘበት ዕለት ሌሎች አምስት ተባባሪዎቹም በቤልጂየም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ገብተዋል፡፡በብራሰልስ ዛቬንቴም ኤርፖርትና የሜትሮ ስቴሽን ላይ በተፈጸመ የሽብር ጥቃት 32 ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸው አይዘነጋም፡፡
መርማሪዎች በብራስልስና ፓሪስ ከተሞች በደረሱ ጥቃቶች እጃቸውን ያስገቡ ሽብርተኞች ከአይኤስ አይኤስ ጋር ግኑኝነት እንዳላቸው ያምናሉ፡፡
የ31 ዓመቱ አብሪኒ የጥምር ዜግነት ባለቤት ስለመሆኑ ይነገራል፡፡የሞሮኮና ቤልጂየም ዝርያ እንዳለውም መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡አቃቤ ህጎቹ ሲፈለግ የነበረው ባለባርኔጣ እርሱ መሆኑን ስላመነበት ሁኔታ ሲያስረዱ ‹‹ለብሶት የነበረውን ጃኬት ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ ከወረወረ በኋላ ባርኔጣውን መሸጡን እንደተናገረ ጠቅሰዋል፡፡
መርማሪዎች በአብሪኒ ላይ ባደረጓቸው የዲኤንኤና የአሻራ ምርመራዎች በብራስልስ በመኖሪያ ቤትና በፓሪስ ጥቃት በደረሰበት ዕለት ጥቃት አድራሾቹ ተጠቅመውታል በተባለ መኪና ላይ ተመሳሳዩን ማግኘታቸውን ገልጸዋል፡፡
ምንጭ ቢቢሲ

No comments:

Post a Comment

wanted officials