Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, April 17, 2016

85 በመቶ የሚሆነው አርሶ አደር ባልተማረበት ሁኔታ የመንግስትን የልማት እቅድ ማሳካት አይቻልም ተባለ


ሚያዚያ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት ሁለተኛውን የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት ከያዛቸው እቅዶች መካከል የተጠናከረ የጎልማሶች ትምህርት ፕሮግራም አንዱ ቢሆንም፣ ባለሙያዎች ግን በእቅዱ አተገባበር ላይ የሰላ ትችት ሰንዝረዋል፡፡
ሰሞኑን በክልል ደረጃ በተደረገው የባለሙያዎች ውይይት እንደተነገረው የ2008 ዓም የጎልማሶች ትምህርት እየተቀዛቀዘ ሄዶአል፡፡ የጎልማሶች ትምህርት ፕሮግራም የልማቱ ቁልፍ መሳሪያ ነው ብሎ የሚያምን አመራር አለመገኘቱን ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡
በእድገትና ትራንስፎርሜሸን ሁለተኛ እቅድ ላይ የተቀመጡት አብዛኛው ግቦች 85 በመቶ የሚሆነው አርሶ አደር ባልተለወጠበት ሁኔታ በመሆኑ፣ እቅዱ አይሳካም ሲሉ አንድ ባለሙያ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፍ ገልጸዋል፡፡
ስራን በቅንጅት ለመፈጸም አለመቻል ለውድቀቱ ተጨማሪ ምክንያት ነው ያሉት ባለሙያው፣ የጤና፣ የግብርናና የትምህርት ሴከትሮች በአንድነት ከመስራት ይልቅ በራሳቸው ስራ ላይ ብቻ ትኩረት ማድረጋቸውን ነቅፈዋል፡፡
መንግስት በጎልማሶች ትምህርት ስም ከተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ሌሎች ለጋሽ አገራት ከፍተኛ ገንዘብ ይቀበላል፡፡ ለዚሁ ተብሎ የተበጀተው በጀት አብዛኛው ለማስታወቂያ እንደሚወጣና አርሶ አደሩ የተረፈው ነገር እንደሌለ ምንጮች ይገልጻሉ፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials