Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, April 11, 2016

አሜሪካዊው አይነስውር ‹‹ሚስቴ ጥቁርነቷን በመደበቅ አጭበርብራኛለች››አለ

ፍቺ ጠይቋል
አሜሪካዊው አይነ ስውር ለ32 ዓመታት በትዳር አብራው የቆየችን ህጋዊ ሚስቱን ለመፍታት ለፍርድ ቤት የፍቺ ጥያቄ አቅርቧል፡፡አባወራው ለትዳሩ መፍረስ ምክንያት በማድረግ ያቀረበውም ባለቤቱ አፍሪካ አሜሪካዊት መሆኗን  ሳያውቅ ማግባቱን በመጥቀስ ነው፡፡
የፍቺ ጥያቄውን ያቀረበው ቴክሳስ ውስጥ ለሚገኘው የትራቪስ ካውንቲ ፍርድ ቤት ነው፡፡
የ59 ዓመቱ ጆን ፖል ዴቪስ የ56 ዓመቷን ባለቤቱን ላቶያህ ጆንሰንን ፍርድ ቤት በገተረበት ክሱ ‹‹አይነ ስውርነቱን በመጠቀም ማንነቷን በመደበቅ ስትጠቀምብኝ ቆይታለች ብሏል፡፡ጥቁር መሆኗን ከመነሻው ቢያውቅ ኖሮ በፍጹም ጋብቻ እንደማይመሰርቱም መግለጹ ተሰምቷል፡፡
ጥቁር መሆኗን ባውቅ ኖሮ እንደማላገባት ታውቃለች ያለው ከሳሽ ‹‹በዚህ ምክንያትም ጥቁርነቷንና ዘሯን ደብቃኝ ኖራለች››ብሏል፡፡
‹‹ይህች ቀጣፊ ሴት ያልሆነችውን እንደሆነች በማስመሰል ከ30 ዓመታት በላይ በእኔ ስትጠቀም ኖራለች››በማለት ተናግሯል፡፡
ጎልማሳው አይነ ስውር በማብራሪያው በመቀጠልም‹‹ጥቁር መሆኗን ያወቅኩት ከሶስት ሳምንታት በፊት አንድ ጓደኛዬ ነግሮኝ ነው፡፡አብረን በቆየንባቸው አመታት በሙሉ ነጭ ትመስለኝ ነበር፡፡ላደረገችብኝ ነገር በሙሉ ወህኒ ቤት መወርወር ይገባት ነበር››ብሏል፡፡
በአንጻሩ ፍቺ የተጠየቀባት ወይዘሮ ባለቤቷ የሚናገረውን ታስተባብላለች፡፡የሰውነቷን የቆዳ ቀለም ልትደብቅበት የምትችልበት መንገድ እንደሌለ በመግለጽ ጥቁር መሆኗን እንደሚያውቅ ትገምት እንደነበር ትናገራለች፡፡
‹‹ስለቆዳ ቀለሜ ጥቁርነቴ ጠይቆኝ ስለማወቁ ምንም ትዝ አይለኝም፡፡ነገር ን ያውቃል ብዬ እገምታለሁ፡፡በፍጹም ነጭ ነኝ ብዬ ያልሆንኩትን ለመምሰል ሞክሬ አላውቅም፡፡ደግሞም እርሱን በማግባቴ ምክንያት የተጎዳሁት እኔ እንጂ እርሱ ሊሆን አይችልም፡፡ምግቡን ከማብሰል ጀምሮ ልብሶቹን ላውንደሪ እስከመውሰድ የመሳሰሉትን ስሰራለት የኖርኩት እኔ ነኝ፡፡የህይወቴን 32 ዓመታት ያጠፋሁት ይህንን ዘረኛ በመንከባከብ መሆኑም ያሳዝነኛል››ብላለች፡፡
ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት ከሁለት ሳምንት በኋላ ከሳሽና ተከሳሽ በድጋሚ ችሎት ይቀርቡ ዘንድ ቀጠሮ መስጠቱ ታውቋል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials