Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, April 6, 2016

የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር በጎንደር ህዝብ ላይ ጦርነት ከፈተ!

የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር በጎንደር ህዝብ ላይ ጦርነት ከፈተ!,,,,,,የትግራይ ነጻ ዓውጭ ግንባር ነው ወይስ የትግራይ ሕዝብ? የትግራይ ኦንላየን ጸሓፊዎች እንደሚሉት ከሆነ፥ በጎንደር ሕዝብ ላይ ጦርነት ያወጀው የትግራይ ሕዝብ ነው፥ ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ ለ25 ዓመታት መሬቱን ነጥቀው፥ ድምጹን ዓፍነው የተቆጣጠሩት የወልቃይ ጠገዴ ሕዝብ እኛ አማራ ነን ስላለ፥ ብዙዎች ለማመን ቢሳነንም ከመቀሌ የሚወጡት መረጃዎች የሚያመለክቱትም እሄንኑ ነው፥
==========================================================
ወያኔ ገና ካፈጣጠሩ ጀምሮ አማራን ለማጥፋት ዓላማው አድርጎ የተነሳ መሆኑ ቢታወቅም፤ በተለይ በጎንደር/አማራ ህዝብ ላይ ለሃያ አምስት ዓመታት ያህል የወልቃይት ጠገዴ፤ ካፍቲያ፤ ሁመራና ጠለምት ህዝብ በገሃድ ባካሄደዉ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለማመን የሚከብድ አሰቃቂ ድርጊት ፈጽሟል።
ጀግናዉ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ፤ የወያኔ አረመኒያዊ ጭፍጨፋ ሳይበግረው፤ ትግስትና ጥበብ በተላበሰ መልኩ ለብዙ ዓመታት “ጎንደሬ፤ አማራ ነን፤ ለወያኔ አንገዛም” በማለት በቆራጥነት ለማንነቱ በመታገል መስዋዕትነት እየከፈለ ይገኛል። በርግጥም፤ ሁላችን እያየን
ያለነው ሃቅ፤ የወያኔ ግፍ እና በደል፤ እንዲሁም እሥራት እና ግድያ በጠነከረ ቁጥር፤ በኮሚቴ የሚመራው፤ ሰላማዊ የማንነት ትግላቸው፤ ፍትህና ነጻነት ለምንሻ ሁሉ የሚመለከተን ሁኗል። በመሆኑም በሁላችንም ልብ ውስጥ ሰርፆ፤ ትግሉን ከአንድ አካባቢ ወደ መላው የአማራ ማንነት አቀጣጥሎታል።
የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር በተግባር እንደታየዉ፤ ወራሪ ቡድን በመሆኑ፤ ህዝቡን እየጨፈጨፈ፤ አንጡራ ሃብት ከዉጭ ጠላቶች ጋር በመተባበር እየዘረፈ ያለ፤ አጥፍቶ፤ ጠፊ ቡድን በመሆኑ፤ ነገ ባንተ ሳይ ሳይደርስ ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝ ከጎንደር ወንድሙ/ እህቱ ጎን እንዲቆም መልክታችን እናስተላልፋለን። የሰሞኑ ወያኔ በጎንደር ላይ የከፈተው ጦርነት፤ የተጠነሰሰው መቀሌ ላይ በተደረገው ሚስጥራዊ ስብሰባ ሲሆን፤ ቀመሩም፤ ጎንደርን ደረጃ በደረጃ አጥቅተዉ፤ እንዴት በሌላ ክ/ሀገር የሚኖረውን አማራ እንደሚያጠፉ የወሰኑበት ሚስጢታዊ ዶክሜንት በተጋለጠ ማግስት ነዉ።,,,,,,,,,,,,,,, የትግራይ ነጻ ዓውጭ ግንባር ነው ወይስ የትግራይ ሕዝብ?
የትግራይ ኦንላየን ጸሓፊዎች እንደሚሉት ከሆነ፥ በጎንደር ሕዝብ ላይ ጦርነት ያወጀው የትግራይ ሕዝብ ነው፥
ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ ለ25 ዓመታት መሬቱን ነጥቀው፥ ድምጹን ዓፍነው የተቆጣጠሩት የወልቃይ ጠገዴ ሕዝብ እኛ አማራ ነን ስላለ፥ ብዙዎች ለማመን ቢሳነንም ከመቀሌ የሚወጡት መረጃዎች የሚያመለክቱትም እሄንኑ ነው፥

No comments:

Post a Comment

wanted officials