Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, April 16, 2016

የህወሓት‬ አገዛዝ ታጣቂዎች በአርማጭሆ ሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ የግድያ ዘመቻ ከፈቱ

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
‪#‎ትክል‬ ድንጋይ እና አካባቢው በህወሓት ሰራዊት ተከቦ የጦር ቀጠና እንደመሰለ እየተገለፀ ነው፡፡
‪#‎43ኛ‬ ክፍለ ጦር የአባላቱ ቁጥር ተመናምኖ በሻለቃ ደረጃ በመድረሱ በ24ኛ ክፍለ ጦር ስር እንዲሆን ተደርጎ ከሸዋ ሮቢት ወደ አዘዞ እና ዳንሻ መዛወሩ ታወቀ፡፡
===================================================Ginbot 7   =56
የህወሓት አገዛዝ ታጣቂዎች በአርማጭሆ ሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ የግድያ ዘመቻ ከፈቱ፡፡
በላይ አርማጭሆ ኩርቢት የተሰማሩት የህወሓት ታጣቂዎች ሚያዚያ 3 2008 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡00 ላይ አቶ አርጋው ሲሳይ ወደተባሉት ድሃ ገበሬ ቤት በመሄድ ገድለው ንብረታቸውን ዘርፈው ተመልሰዋል፡፡Ginbot 7   =56
የአርማጭሆ ምስኪን ገበሬዎች በህወሓት ታጣቂዎች የግድያ እርምጃ እየተወሰደባቸው እና የዝርፊያ ተግባር እየተፈፀመባቸው የሚገኙት በአርበኞች ግንቦት 7 አባልነት ስለተጠረጠሩ ብቻ እንደሆነ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡
ትክል ድንጋይ እና አካባቢው በህወሓት ሰራዊት ተከቦ የጦር ቀጠና እንደመሰለ እየተገለፀ ነው፡፡
ከሚያዚያ 3 2008 ዓ.ም ጀምሮ የህወሓት ፌደራል ፖሊስ፣ ልዩ ኃይልና የመከላከያ ሰራዊት ትክል ድንጋይ እና አካባቢውን በስፋት ወሮታል፡፡ የጦር ሰራዊቱ ቁጥር እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡ ነገር ግን ምክንያቱ ምን እንደሆነ በውል ተለይቶ አልታወቀም፡፡
የትክል ድንጋይና አካባቢው ነዋሪዎች ከፍተኛ ስጋት ላይ ናቸው፡፡
43ኛ ክፍለ ጦር የአባላቱ ቁጥር ተመናምኖ በሻለቃ ደረጃ በመድረሱ በ24ኛ ክፍለ ጦር ስር እንዲሆን ተደርጎ ከሸዋ ሮቢት ወደ አዘዞ እና ዳንሻ መዛወሩ ታወቀ፡፡
43ኛ ክፍለ ጦር ወደ ሶማሊያ ዘምቶ አብዛኞቹ አባላቱ ተደምስሰው ውልቁን ቀርቶ የተመለሰ ሲሆን ከሌሎቹ ክፍለ ጦሮች በመቀነስና አዳዲስ አባላትን በማስገባት መልሶ አንዲያንሰራራ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡ ነገር ግን አባላቱ በየዕለቱ ስለሚከዱ በአሁኑ ወቅት ከክፍለ ጦርነት ወርዶ በሻለቃ ደረጃ ይገኛል፡፡ ማዘዣ ጣቢያው ጅማ የነበረው የደቡብ ምዕራብ ዕዙ 43ኛ ክፍለ ጦር ሰሞኑን ከሸዋ ሮቢት ተነስቶ ወደ አዘዞ እና ዳንሻ ተዛውሯል፡፡
በሻለቃ ደረጃ የሚገኘውና ስሙን ብቻ ተሸክሞ መና የቀረው 43ኛ ክፍ ጦር ወደ ሰሜኑ ክፍል የተዛወረው በስሩ ሆኖ 24ኛ ክፍለ ጦርን በውጊያ እነዲያግዝ ታስቦ እንደሆነ ምንጮቻችን ገልፀዋል፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials