Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, April 13, 2016

ወያኔ ስለ ልማት የሚደነፋዉ በኢቲቪ ዉስጥ ነዉ::ሰሜን ሸዋን እንደ ማሳያ ህዝቡምም ከብቱም ካንድ ወንዝ ይጠጣሉ






አብርሃም ታዬ



የህዝብ ጠላቶች አገሩን ተቆጣጥረዉት እያሉ ስለ ህዝብ ልማት ማዉራት በራሱ ቀልድ ነዉ:: :- የ ሰሜን ሸዋን እንደ ማሳያ ህዝቡምም ከብቱም ካንድ ወንዝ ይጠጣሉ
---------------------------------------------------------------------------------
-ወያኔ ስለ ልማት የሚደነፋዉ በኢቲቪ ዉስጥ ነዉ:: መሬት ላይ ምንም እንደሌለ ያዉቃል:: የነሱ አሽከር የሆኑት ሀይሎች ደግሞ እንኳን ተግባራዊ ልማት ሊሰሩ ይቅርና የልማት ትርጉሙ ምንድን ነዉ ቢባሉ አይገባቸዉም::


- በስዕሉ ላይ የምታዩት በሰሜን ሸዋ ዉስጥ በመንዝ ወረዳ በመዘዞ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ዉስጥ በልማት እጦት የሚሰቃይ ህዝብ ሲሆን አሁንም ልብስ የሚታጠበዉ በእንዶድና በድንጋይ ላይ ነዉ:: በጣም የሚያሳዝነዉ ታዲያ ማጠቢያውም የመጠጡም ዉሃ ምንጩ አንድ ላይ የተደባለቀ ከመሆኑ የተነሳ ብዙ ብክለት ስለሚደርስ ህዝቡ ለከፍተኛ በሽታ የተጋለጠ ነዉ::

- ለምሳሌነት ይሄን ቀበሌ አነሳንዉ እንጅ ሁሉም የሰሜን ሸዋ አካባቢዎች ተመሳሳይ ናቸዉ:: ከአዲስ አበባ 50ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኙ አካባቢዎች የመንገድ ትራንስፖርት የላቸዉም:: ከላይ በስዕሉ እንደሚታዬዉ የመጠጥ ዉሃቸዉ እና ልብስ ማጠቢያቸዉ የተበከለ ነዉ::አንድ ወንዝ ዉስጥ ልብሳቸዉን ያጥባሉ: ከብታቸዉን ያጠጣሉ: ለእራሳቸዉ ለመጠጥ የሚሆን ዉሃ ይቀዳሉ:: ይሄም እንግዲህ ምናልባት በአካባቢዉ አንዲት ወንዝ ካለች ነዉ:: አለዚያ ግን ለመጠጥ ዉሃ ፍለጋ እና ለከብቶቻቸዉ ዉሃ ፍለጋ ግማሽ ቀን ሲዞሩ ይዉላሉ::

-በዚህ የእሳት መከራ ዉስጥ የሚመላለሰዉን ህዝብ ወያኔ ለሌላዉ ወንድሙ ኢትዮጵያዊ ምን ብሎ ያስተዋዉቀዋል? ነፍጠኛ ትምክህተኛ እና አንተን የገዛ ህዝብ ብሎ ያስተዋዉቀዋል::ይሄን በችግርና በመከራ ዉስጥ ያለ ህዝብ በበሽታ ከምድረ ገጽ እስኪጠፋ ዝም ብሎ እያስተዋለዉ በሌሎች ዘንድ ግን ስለዚህ ህዝብ ጥላቻን ይነዛል::

-እዚሁ ሰሜን ሸዋ ዉስጥ ብዙ የኦሮሞ ወረዳዎችም አሉ:: እንደ አማራ ወረዳዎች ሁሉ ምንም የለማ ነገር የላቸዉም:: ወያኔ ግን ስለ እነዚህ የኦሮሞ ወረዳዎች ወደ ሌላዉ ህዝብ የሚያሰራጨዉ መልዕክት ምንድን ነዉ? ኦሮሞዎች ሊገነጠሉ ስለሆነ አትመኗቸዉ የሚል ነዉ::ኦሮሞዎች በአማራዉ አይን በጥርጣሬ እንዲታዩ የቤት ስራቸዉን ይሰራሉ:: አማራዎችም በኦሮሞዎች ዘንድ በጥርጣሬ እንዲታዩ አበክረዉ ጥላቻን ይረጫሉ::

-ብአዴን እና ኦህዴድ የተባሉት የጸረ ህዝብ ስብስቦች ደግሞ ህዝባቸዉ ዉስጥ ያለዉን የችግር መከራ ከማስተዋል ይልቅ ወያኔ በሀሰት ጭንቅላታቸዉ ዉስጥ የጠቀጠቀባቸዉን ተረት ተረት ተሞልተዉ በፖለቲካ ስካር ዉስጥ ናቸዉ::

-የህዝብ ጠላቶች አገሩን ተቆጣጥረዉት እያሉ ስለ ህዝብ ልማት ማዉራት በራሱ ቀልድ ነዉ:: የህዝብ ጠላቶች ህዝቡ ስለልማቱ እንዳይጠይቃቸዉ በርካታ ተረት ተረት እየፈጠሩ ግራ ያጋቡታል:: ልቡን ያሻክሩታል:: እነሱ አገር መሸጥ : ህዝብ መከፋፈል: ጥላቻ መንዛት: ባንዳዎችን ከህዝቡ መሃል በጥንቃቄ መልምለዉ ማዉጣት ያዉቁበታል:: እናም ዋናዉ የህዝባችን ጠላቶች ደግሞ ከህዝቡ መሃል በወያኔዎች ተመልምለዉ የወጡት ብአዴን እና ኦህዴድ የሚባሉ የባንዳ ስብስቦች ዉስጥ የመሸጉ ሀይሎች ናቸዉ::

-ህዝብ ግን ትምህርት ቤት የለዉም:: መጠጥ ዉሃ የለዉም:: ለእንሥሳቶቹ ዉሃ መጠጥ የለዉም:: ትራንስፖርት የለዉም:: የተቆረጠ እና እጅግ በመከራ ዉስጥ የሚኖር ነዉ::ከአካባቢዉ ተሰዶ የሚሄድበት ቦታ የለም:: ህዝቡ ምን እንዲሆን ተፈልጓል? በበሽታ : በርሃብ እና በስደት ከምድረ ገጽ እንዲጠፋ ተፈልጓል::

-ወያኔዎች በዚህ ሁሉ ነገር ዉስጥ አንድ ነገር እርግጠኛ መሆን ይፈልጋሉ:: ጥላቻ እና እርስ በእርስ መለያዬት እህዝቡ ጆሮ ዉስጥ መድረሳቸዉን ከህዝቡ መሃል በመለመሏቸዉ ባንዳዎች ማረጋገጥ ይፈልጋሉ:: ደግሞም ያደርጉታል::

-ህዝቡ መሃል ገብታችሁ ህዝቡን ብትጠይቁት የወያኔዎችን ደባ እየሳቀ ያስረዳችኋል:: ግን ብአዴን እና ኦህዴድ በሚዲያ ላይ እንዲሁም በልዩ ልዩ መንገድ የህዝቦችን ልዩነት ከፍ አድርገዉ ይሰብካሉ::ህዝባችን ግን በልማት እጦት ከምድረ ገጽ ሊጠፋ ነዉ::

No comments:

Post a Comment

wanted officials