Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, April 20, 2016

በዘላላም ወርቃገኘሁ መዝገብ ከተከሰሱት መካከል ሁለቱ በነጻ ሲሰናበቱ ሌሎች ጥፋተኞች ተባሉ


ሚያዚያ ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመዝገብ ቁጥር 166/07 በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው ጉዳያቸው በ19ኛው ችሎት እየታየ ከሚገኙት መካከል አቶ ባህሩ ደጉናና ዮናታን ወልዴ በነጻ ሲሰናቱ ቀሪዎቹ ጥፋተኞች ተብለዋል፡፡
በዚህ መዝገብ ውስጥ ስማቸው ሰፍሮ የሚገኘው ተከሳሾች ዘላለም ወርቃገኘሁ፣ ሃብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ አብርሃ ደስታ ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ዮናታን ወልዴ፣ አብርሃም ሰሎሞን፣ ሰሎሞን ግርማ፣ ባህሩ ዳጉ እና ተስፋዬ ብርሃኑ ናቸው፡፡
ከእነዚህ መካከል የፖለቲካ ድርጅት መሪዎቹ ቀደም ብሎ እንዲፈቱ የተወሰነ ቢሆንም፣ ከአቶ ሃብታሙ አያሌው በስተቀር ሌሎቹ አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ ፍርድ ቤቱ በዛሬው ውሎው ደግሞ አቶ ባህሩ ደጉና አቶ ዮናታን ወልዴ በ19ኛ ችሎት በሽብርተኝነት ክስ ተከሰው በእስር ቤት ለአመት ከዘጠኝ ወር ከቆዩት ውስጥ ሁለት ተክሳሾችን ፍርድ ቤቱ በነፃ ያሰናበታቸው ሲሆን ሌሎቹን ጥፋተኞች ናቸው ብሎአል፡፡
አቶ ባህሩ ደጉ በማእከላዊ እስር ቤት ራቁቱን ተደብድቧል፤ከድብደባ ብዛት ሽንቱን መቆጣጠር ተስኖት ነበር፣ እንዲሁም የገዛ ሽንቱን እንዲጠጣ ተገድዷል፣ ‹‹የግንቦት ሰባት መሪ ብርሃኑ ነጋ ምንህ ነው? ከአንዳርጋቸው ጽጌስ ምን አለህ? ብርሃኑ ዘመድህ ነው?›› የሚሉ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እንደቀረቡለት እንዲሁም ‹‹ከጉራጌ መወለድ ወንጀል ነው እንዴ?››ሲል በችሎት ፊት መጠየቁን፣‹‹ጉራጌ ሲሰርቅና ሲያጭበረብር እንጂ ሲታገል አያምርበትም እየተባለ መደብደቡን፣‹‹የደም ስርህን በጥሰን እንገልሃለን፤ፖሊሱ፣አቃቤ ህጉ፣ፍርድ ቤቱ፣ ደህንነቱ…ሁሉም የኛ ነው፤ አንተን 20 አመት እናስርሃለን›› እየተባለ ስቃይ እንደተፈጸመበት ለችሎቱ መናገሩን ነገረ ኢትዮጵያ ቀደም ብሎ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials