Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, April 28, 2016

የማኅበረ ቅዱሳን ዐውደ ርእይ ከግንቦት 17 – 22 ቀን በኤግዚቢሽን ማዕከል እንዲካሔድ ዕውቅና አገኘ


የማኅበረ ቅዱሳን ዐውደ ርእይ ከግንቦት 17 – 22 ቀን በኤግዚቢሽን ማዕከል እንዲካሔድ ዕውቅና አገኘ






የአዲስ አበባ አስተዳደር የከንቲባ ጽ/ቤት፣የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ዕውቅናውን የሰጠው፥ ዛሬ፣ ሚያዝያ 11 ቀን 2008 ዓ.ም.፣ ከጠዋቱ 3፡00 ላይ እንደኾነ የማሳወቂያ ቅጹ ያመለክታል፡፡
“የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ማሳወቅ” በሚል ዓላማ ባገኘው ዕውቅና ከግንቦት 17 – 22 ቀን 2008 ዓ.ም.በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ምሸት 4፡00 ድረስ ለሚካሔደውና ከ100 ሺሕ በላይ ተመልካች እንደሚጎበኘው ለሚጠበቀው የ፭ኛው ዙር ልዩ ዐውደ ርእይ መንግሥት የፖሊስ ጥበቃ ድጋፍያደርጋል፡፡
የማኅበሩ አመራር እና የዝግጅቱ ዐቢይ ኮሚቴ፣ ቀደም ሲል ከመጋቢት 15 እስከ 22 ቀን 2008 ዓ.ም. በዚያው በኤግዚቢሽን ማዕከል እንዲካሔድ ታቅዶ የነበረው የ፭ኛው ዙር ልዩ ዐውደ ርእይ መርሐ ግብር ባልተለመደ ሕግና አሠራር እክል ከገጠመው ደቂቃ ጀምሮ፥ የአዲስ አበባ አስተዳደርንና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ጨምሮ ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እና ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ ሓላፊዎች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በትዕግሥት ሲያካሒድ ሰንብቷል፡፡
ውይይቶቹ በተካሔዱባቸው አጋጣሚዎች ኹሉ፣ መርሐ ግብሩን ለማስተጓጎል በማሰብ የአዲስ አበባ አድባራት አማሳኞች ያወጡትንና በሌላቸው ሥልጣን ለክልል መንግሥታት ሳይቀር ያሰራጩትን መግለጫ መግፍኤ በሚገባ ለማጋለጥ ወዲያውም ደግሞ፤ የማኅበሩን ዓላማና የአገልግሎት ስልቶች በጥልቀት ለማስገንዘብ መልካም አጋጣሚ የተፈጠረ ሲኾን፤ የማኅበሩ አመራርም፤ በመጨረሻ፣ ለ፭ኛው ዙር ልዩ ዐውደ ርእይ የከተማው አስተዳደር ለሰጠው ዕውቅና ምስጋናውን አቅርቧል፡፡


ኦርቶዶክሳዊው ምእመን፥ ትምህርተ ሃይማኖቱን፣ ሥርዐተ እምነቱን፣ ክርስቲያናዊ ትውፊቱንና ታሪኩን ተረድቶ ከሐዋርያዊት፣ ኵላዊትና ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ጋር ያለውን መስተጋብር እንዲያጠናክር ብሎም ድርሻውን ተገንዝቦ የበኩሉን እንዲወጣ የማድረግ ዓላማ ያለውና “ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን: አስተምህሮዋን እንጠንቅቅ፤ ድርሻችንን እንወቅ” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው ፭ኛው ዙር ልዩ ዐውደ ርእይ፣ የማኅበሩ ስትራተጅያዊ ዕቅድ አካል ሲኾን፤ በመደበኛው አሠራር፣ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በወቅቱ ተገቢውን ድጋፍና ዕውቅና አግኝቶ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቆ ለመታየት የሰዓታት ዕድሜ ሲቀረው መታገዱ ይታወሳል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials