Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, April 27, 2016

የኢትዮጵያዊቷ ሞደሊስት የዘር ሐርግ ፍለጋ ከአሜሪካ እሰከ ኦሞ ወንዝ የተደረገ የጉዞ ቅኝት (ታምሩ ገዳ)






“እነዚህ ድንቅ ጎሳዎችን በስልጣኔ ሰም ከመጥፋታቸው በፊት መጎብኘቴ ትልቅ እድል ነው”ሞዲሊስት ፋጡማ ስይድ

እውቋ ሞደሊስት ፋጡማ ሰይድ የሁለት እህቶቿን በሶማሊያው የአርስ በርስ ጦርነት ካጣች በሁዋላ ከአስራ ሶስት አመቷ ጀምሮ በሰደት ያደገችበት የአሜሪካኑ የቦስተን ከተማን በተለይ ደግሞ ዛሬ ብዙዎች የሚያውቋት የኒዮርክ ከተማን “ቤቴ ነው “ብትለውም በውስጧ አንድ የጎደላት ነገር እንዳለ ከተረዳቸው ክረምረም ብላለች። እርሱም የማንነቷ ጥያቄ እና የዘር ሐረጓ ከየት እንደ ተመዘዘ ጠንቅቆ ማወቅን ነበር ።

ከኢትዮጵያዊ አባቷ እና ከሶማሊያዊ እናቷ በመጸነስ የዛሬ 29 አመት ወደዚህ አለም ብቅ ያለቸው ፋጡማን ብዙዎቹ ምእራባዊያን የፋሺን አዘጋጆች እና ስፓንሰሮች የሚያውቋት በ ጥቁር ፣እንቁ እና ሞደሊስትነቷ በኒዮርክ፣በፓሪስ፣በሎንዶን፣በሚላን ፣ በአቴንስ እና በመሰል መደረኮች ላይ ውብ ምስሎቿን እንጂ ከየተኛው ምድር እንደ በቀለች እራሷም ብትሆን ከልጅነት ምናቧ ውጪ በቅጡ የምታውቀው አትመሰልም ነበር።

ለዚህም ይመሰላል በቅርቡ ከምትኖርባት የኒዮርክ ከተማ በመነሳት የሰው ልጆች መገኛ ከሆነቸው ከምድረ ኢትዮጵያ በተለይ ደግሞ የወላጅ አባቷ የዘር ሐርግ ከሚመዘዘባት እና በዘመናዊ ስለጣኔ ስም (ለሸንኮራ አገዳ ተክል ልማት እና ለግልገል ጊቤ ሶስተኛ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀችት ሲባል) ከ200 ሺህ በላይ የአካባቢው ነዋሪዎች ከቀያቸው የመፈናቀል አደጋ ሊገጥማቸው ይችላል አሊያም የተፈጥሮአዊ የአኗኗር ኡደታቸው ሊቋራጥ ግድ ይላል ተብሎ የሚሰጋላቸው በጥንታዊ እና ማራኪ የአኗኗር ስልታቸው የበርካታ ጎብኘዎች እና የተመራማሪዎች ቀልብን የሚስቡት ከ 12 የሚበልጡ የተለያዩ ጎሳዎች የሚገኙበት ከኦሞ ወንዝ አቅራቢያ (ከደቡባዊው የአገሪቱ ክልል) ነበር የተጓዘችው።የፋጡማ የደቡብ ኢትዮጵያ ጉብኘት የዘር ሐረጓን ፍለጋ ብቻ ሳይሆን በስልጣኔ ሽፋን ከአይናቸን ሊጠፉ የሚችሉትን የኦሞ ወንዝ ያፈራቸው ኢትዮጵያዊያኖችን በግንባር እና በአይኗ ተገኘታ ለመቃኘት ሲባል “ከጊዜ ጋር የተደረገ እሸቅድምድም” መሆኑን አስረግጣ ተናግራለች።


ከዘመናችን እውቅ ሞዲሊስቶች መካከል አንዷ የሆነችው ፋጡማ የኢትዮጵያ ምድርን ስትረግጥ እነዚያ ብዙ ምእራባዊያን የምጣኔ ባለሙያዎች የመሬት ሽያጩ እርሷ ከከተመችበት ከኒዮርክ ከተማ እጅግ የናረባት የ አ/አ ከተማ እና ዘመናዊ ህንጻዎቿን ብዙም ሳትቃኝ በበነጋታው የዘር ሐርጓ ትስስርን ለመፈለግ ወደ ደቡባዊ ኢትዮጵያ ያደረገችው ጉዞን በተመለከተ በአለም ታዋቂ ሞደሊስቶች ፣የፋሺን ዲዛይነሮች ፣አደናቂዎች እና የመሳሰሉት ዙሪያ የሚያውጠነጥነው “ቮጎስ” የተባለ ታዋቂው መጽሄት ባለፈው ቅዳሜ ሚያዚያ 9/2016 እኤአ ሲዘግብ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ደም ሰላላት እውቋ ሞዲሊስት ፋጡማ ሲዘግብ ፋጡማ በኢትዮጵያ ቆይታዋ የልጅነት ጊዜዋን ባሳለፈችው አርብቶ አደሮች በሚበዙበት በጎረቤት ሶማሊያ (በእናቷ አገር) የነበረው ኑሮ በኦሞ ወንዝ ዳርቻ ከሚኖሩ ጋር ተመሳስይነት እንዳለው ለመረዳት መቻሏን ተናግራለች።

እራሰቸውን በተለያዩ መንገዶች ከሚገልጹት ከሙርሲዎች (ከንፈራቸውን በትልቅ ሸክላ የሚወጥሩት) ፣ከዶርዚዎች (በሸማ ፣በ ፈትል ሰራ እና በድንቅ የጎጆ ቤት አሰራር የተካኑት)፣ ከ ከሮዎች (እራሳቸውን ነጭ አፈር በመቀባት የሚያሰወቡት) ጎሳዎች ጋር ለመገናኘት ከመቻሏ በተጨማሪ ወንድ ልጆች ለጉርምሳና ለመድረሳቸው መለኪያ/መፈተኛ የሆነው በርድፍ በቆሙ የቀንድ ከብቶች/ሰንጋዎች ጀርባ ላይ መዘለል ፣ ታዋቂው የምሽት ጭፈራን ( ኢቫንጋዲን) ከማየት በመለጠቅ በዶርዜዎች ቤት ተገኝታ በልጅነቷ ታደርገው የነበረው ለእናቶች ውሃ የመቀዳት ባህልን በተግባር ተወጥታለች ፣የሸማ ሰራ/ ጥጥ የመፍተል ስልጠናን ወስዳለች ፣ የማህበረሰቡን ከብቶችም ጠብቃላቸዋልች ።በስተመጨረሻም ከደሳሳ ነገር ግን በፍቅር ከተሞላው ጎጆዋቸው ተጋብዛ ቡና በጋራ ለመጠጣት በቅታለች። ዘውትር ቢቀርቧቸው እና ቢጎበኙ ከማይሰለቹት የደቡብ ኢትዮጵያ ተወላጆች እና ተፈጥሮ የደለቸው መልካ ምድሯ ጉብኝት መልስ በአ/ አ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ወዳጅ ዘመዶቿ ጋር በዚያ በመከረኛው እና ትወልድ ገዳይ በሆነው በጫት እና ሺሻ(ሁካ) ዙሪያ እንደተገናኘች ፣ለማሰታውሻነት የተለያዩ ኢትዮጵያ ነክ አልባሳትን እና ጌጣ ጌጦችንም እንደገዛች የመትናገረው ፋጢማ የኢትዮጵያ ጉዞዋ ከአይምሮዋ የማይረሳ ትዝታ እንደጣለባት እና የምስራቅ አፈሪካ ቁርኝቷን ይበልጥ ያጠናከረላት መሆኑንም ሳትገልጽ አላለፈችም።

ፋጡማ በደቡብ ኢትዮጵያ(የኦሞ ወንዝን ብቸኛው ተገናቸው እና እስትንፋሳቸው ያድረጉ) ወገኖቻቸን ማየቷን በተመለከተ “በህይወቴ ውስጥ ትልቅ ከምላቸው ክስተቶች መካከል ጉልሁ እና አንዱ ነው “ በማለት ከጉዞዋ መልስ በቲዊተር አካውንቷ ላይ ያሰፈረቸው ሲሆን የእነዚህ ዝርያቸው በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮአዎ ክስተቶች ሳቢያ በመመናመን እና በመጥፋት ላይ ያሉት ጎሳዎች የመኖር እና ያለመኖር ጉዳይን በተመለከተ የተለያዩ የሰበአዊ መብት እና የአካባቢያዊ እንክብካቤ ተቶርቋሪዎችም ጭምር ስጋት ከመቼውም ጊዜ በላይ ሲያሰተጋባ ይሰማል። በተቃራኒው ደግሞ “ቱሪዝምን ጨምሮ በሁሉም መሰክ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ እሆናለሁ” የሚለው (ባለ ራእዩ) አገዛዝ ጩሀቱን እና ውግዘቱን በተመለከተ “ተቃውሞው ለዜጎች ዘላቂ መብት ከሚቆረቆሩ ወገኖች ሳይሆን ፈርንጆችን ለማሰደሰት ከሚዳክሩ ቡድኖች የመነጨ ወቅሳ ነው”በማለት ስጋታቸውን ያጥላላል። ታዲያ እዚህ ላይ ትልቁ ጥያቄ የኦሞ ወንዝን መከታ ያድረጉት ቀደምት እና በአለማችን ላይ እጅግ ውብ የሆነ የአኗኗር ስልት ካላቸው ጎሳዎች የሚጠቀሱት ወገኖቻቸንን ባሕላቸውን፣ እኗኗራቸውን እና ቀያቸውን ሳይቀይሩ ህይወታቸው የሚሻሻልበትን መንገድ መቀየስ ወይስ በዘመናዊነት ምክንያት “ነበሩ”ሚለውን ብሄልን ማፋጠን? የሚሉ የሁለት የክርክር መድረኮች ተከፍተዋል

No comments:

Post a Comment

wanted officials