Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, April 12, 2016

በኢትዮዽያ የሚንቀሳቀስ ኩባንያ በፓናማ (የሙስና ቅሌት ስነድ) ውስጥ ተጋልጧል





ከሁለት ቀናት በፊት በአለም አቀፍ ደረጃ ይፋ የተደረገውና ፓናማ ፔፐርስ (Panama Papers) በሚል የተሰየመው የሙስናና የገንዘብ ማሸሽ ቅሌት የተጋለጠበት ግዙፍ መረጃ የአለም የመገናኛ ብዙሀንን ስራ አብዝቶባቸዋል።የእነማን ስም ተነሳ? የትኞቹ ኩባንያዎችስ አሉበት? የሚለውን ለማጣራት ጋዜጠኞች በር ዘግተው ስነዱን እየመረመሩ ነው።



በርካታ የላቲን አሜሪካ የእስያና የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት በቅሌት መዝገቡ በስፋት ተዳሰዋል። አፍሪቃም ከቅሌቱ አላመለጠችም። ባለሀብቶችና የፖለቲካ ሹማምንት በድብቅ በቤተሰቦቻቸው አልያም በቅርብ ወዳጆቻቸው ስም ከሀገር አሽሽተው የደበቁትን ገንዘብ የደበቀላቸው በፓናማ የሚገኝ ሞሳክ ፎንሲካ (Mossack Fonseca) የተባለ የህግ አማካሪ ነው። ይህ ተቋም ገንዘቡን የህግ ክፍተት ወዳለባቸው ትናንሽ ሀገሮች በማሸሽ የማማከር አገልግሎት ይሰጣል።የስዊስን ባንክ የመሳሰሉትን ደግሞ ለመሸጋገሪያነት ይጠቀምባቸዋል።

ባለሀብቶች ታክስ ለመሸሽና በስርቆት ያገኙትን ሀብት ወደዚህ ተቋም በመውሰድ ይሸሽጋሉ።የሩሲያው ቭላድሚር ፑትቲን ስማቸው እየተብጠለጠለ ነው። በስማቸው ሁለት ቢሊያን ዶላር በወዳጆቻቸው ስም ደግሞ የትየለሌ የሆነ ገንዘብ መዘረፉን ስነዶች ያመለክታሉ። የደቡብ አፍሪቃው ጃኮብ ዙማና የቀድሞ የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሀፊ ኮፊ አናን በወጣት ልጆቻቸው ስም የተቀመጠ ገንዘብ ተግኝቷል።

ይህ አይነቱ የገንዘብ ማሸሽ በተለየ ታክስ ላለመክፈል የሚደረግ ሲሆን በዘረፋ የተገኘንም ገንዘብ ለመሸሸግ ይመረጣል። ታዋቂ ስፖርተኞችና የፊልምና ሙዚቃ ኢንደስትሪው ባለፀጎች እዚህም እዚያም የራሳቸውም ሆነ የቤተሰቦቻቸው ስም መነሳቱ አልቀረም።

የእንግሊዙ ጠ/ሚ/ር ዴቪድ ካሚሮን አባት ስም ከዝርዝሩ መገኘቱ ፖለቲካዊ አተካሮ እንዳይቀሰቅስ ስጋት አለ። በሌሎች ሀገሮችም ቢሆን የፖለቲካ ቅሌቱ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ያነሳሳ ይሆን ወይ የሚለውን ሁሉም በጉጉት እየጠበቀው ነው። ከመረጃው ገና የቀረ ስላለ የብዙዎች ስም በመጪው ሰነድ ውስጥ ይኖር ይሆናል።

በአለማቀፍ የምርመራ ጋዜጠኞች ህብረት International Consortium of Investigative Journalists (ICIJ) እና በመገናኛ ብዙሀን እጅ የገባው ይህ ሰነድ ማንነቱን ባልገለፀ አካል ተጠልፎ የተገኘ ነው። ይፋ የተደረገው መረጃ 11.5 ሚሊየን ስነድ የያዘ ነው።

በኢትዮዽያ በማዕድን ዘርፍ ለመሰማራት ከአምስት አመት በፊት ፈቃድ ያገኘው የእስራኤሉ ኤንግልኢንቨስት በዚሁ የቅሌት ሰነድ ላይ ስሙ ተጠቅሷል። ድርጅቱ በእስራኤልና በአዲስ አበባ ተቀማጭ የሆኑ ባለሀብቶቹን ዝርዝሯል። ከተዘረዘሩት ግለሰቦች መካከል አንዱ የስሙ የመጀመሪያ ፊደል “Y” ብቻ በሰነዱ ላይ ስፍሯል። ይህ ምናልባትም የግለሰቡን ማንነት የበለጠ እንድንጠይቅ የሚገፋፋ ሳይሆን አይቀርም። ግለሰቡ ኢትዮዽያዊ ላይሆን ይችላል፣ ስሙን መሸሸጉ ግን ሰለዚህ የማዕድን ኩባንያ እንድንመራመር የሚጋብዝ ነው። የእንግሊዘኛውን ዋና መረጃ ከታች ይመልከቱት


Another company registered by Engelinvest in Anguilla is Irisgianman. Besides the registration itself, it is hard to identify the connection between the subsidiary and the parent company. The goal of the new company, which was established in October 2011, is mining activity in Ethiopia. Its shareholders, according to the registration documents, are two Israelis, one named Iris Levenstein and the other identified as Y., and Valona Giancarlo, an Italian national residing in Addis Ababa.

No comments:

Post a Comment

wanted officials