Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, April 24, 2016

በጃማይካ የኃይለስላሴ የልጅ ልጅ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

በጃማይካ የኃይለስላሴ የልጅ ልጅ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

ERmias
 የአጼ ኃይለ ስላሴ የልጅ ልጅ የሆኑት ልዑል ኤርሚያስ ሳህለ ስላሴ በጃማይካዋ አይስላንድ ከተማ በተገኙበት ሰዓት ከፍተኛ የክብር አቀባበል የተደረገላቸው መሆኑን የጃማይካው ኦብዘርቨር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡
ከባለቤታቸው ልዕልት ሳባ ከበደ ጋር የሶስት ቀናት ጉብኝት ለማድረግና የአያታቸውን 50ኛ ዓመት የጃማይካ ጉብኝት ለማክበር በስፍራው የተገኙት ልዑል ኤርሚያስ ሳህለ ስላሴ በተደረገላቸው አቀባበል የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
በመቶዎች የሚቆጠሩ ራስ ተፈሪያን ፣ሴቶችና ህጻናት በኖርማን ማንሌይ አለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ በመገኘት ከአሜሪካ የመጡትን ልዑል በዝማሬ አጅበው ተቀብለዋቸዋል፡፡
ራስ ተፈሪያኑ ልዑሉን ከተቀበሉ በኋላ በሰጡት አስተያየት ከዛሬ ሐምሳ ዓመት በፊት ጃማይካን ለመጎብኘት ከመጡት ንጉስ ጋር የአሁኑ የልዑሉ ጉብኝት እንደማይወዳደርም ተናግረዋል፡፡
ልዑሉን የጃማይካ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትም የክብር አቀባበል ያደረጉላቸው መሆኑን ያወሳው ጋዜጣው የኃይለ ስላሴ የልጅ ልጅ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ልዑሉ በኪንግስተን ከተማ ከንቲባ የተበረከተላቸውን ታሪካዊ ስጦታ ከተረከቡ በኋላ ወደ ጀግኖች ሙዚየም በማምራት በማርከስ ጋርቬይ የመታሰቢያ ሐውልት ላይ ጉንጉን አበባ አስቀምጠዋል፡፡
ጃማይካዊያን በተለይም ራስ ተፈሪያንስ ለቀድሞው የኢትዮጵያ ንጉስ አጼ ኃይለ ስላሴ የተለየ አክብሮትና ፍቅር ያላቸው መሆኑ ይታወቃል፡፡
ምንጭ ጃማይካ ኦብዘርቨር

No comments:

Post a Comment

wanted officials