Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, April 24, 2016

አንድ ኬንያዊ ከኦቦ በቀለ ገርባና 21 ሰዎች ጋር በሽብር አዋጁ ተከሰሱ



በታህሳስ ወር በፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ገርባ ለአራት
 ጊዜያት ያህል አራዳ ምድብ ችሎት እየቀረቡ በፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሲጠየቅባቸው ቆይቶ በዛሬው
 ዕለት ከሳሾቻቸው ለማንም ሳያሳውቁ በቀለንና ከእርሳቸው ጋር የተከሰሱ ሌሎች 21 ሰዎችን ልደታ ከፍተኛው 
ፍርድ ቤት 19ኛው የወንጀል ችሎት በማቅረብ በጸረ ሽብር አዋጁ መሰረት ክስ መስርተውባቸዋል፡፡



የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቋንቋ መምህሩ በአራቱ የአራዳ ፍርድ ቤት ውሏቸው በጠበቃቸው

በኩል ሲከራከሩ ቢቆዩም ዝግ በተደረገው በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ጠበቃቸው 
አለመገኘታቸው ታውቋል፡፡

የመንግስት አቃቤ ህጎች በዛሬው ዕለት በልደታ ፍርድ ቤት የሽብርተኝነት ክስ ከመሰረቱባቸው

ሰዎች መካከልም አንድ ኬንያዊ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡


ከኦቦ በቀለ ጋር ፍርድ ቤት የቀረቡት ተከሳሾች ከአዲስ አበባና ከአዳማ የተያዙ መሆናቸው የታወቀ

ሲሆን የሚበዙት ከኦሮምኛ ቋንቋ ውጪ ክሱ የቀረበበትን የአማርኛ ቋንቋ የማያውቁ በመሆናቸው

በቀጣይ አስተርጓሚ እንዲቀርብላቸው መታዘዙ ተሰምቷል፡፡


መደረጋቸውን ሰምተዋል፡፡

በቀለና ቀሪዎቹ የህሊና እስረኞች አራዳ ፍርድ ቤት ከሰዓት በኋላ እንደሚቀርቡ የሰሙ ሰዎች ወደ

አራዳ ፍርድ ቤት ለማምራት በተዘጋጁበት እስረኞቹ በማለዳ ልደታ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ



አቃቤ ህግ በክስ መዝገቡ በአራተኝነት ባስቀመጣቸው ኦቦ በቀለና ቀሪዎቹ ተከሳሾችን ከኦሮሚያ

ክልል ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በማገናኘት በኦነግ አባልነት፣አመጽን በማበረታታት፣በአምቦና አዳማ

ንጹሐን ዜጎች እንዲገደሉና ንብረት እንዲወድም በማድረግ በሚሉ ወንጀሎች ከስሷቸዋል፡፡


ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ተከሳሾቹን ከማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ በማውጣትም ወደ መደበኛ ወህኒ ቤት

እንዲያዟዙራቸው በማዘዝ ተከሳሾች ለቀረበባቸው ክስ ምላሽ እንዲሰጡም ለቀጣዩ ማክሰኞ

ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡


No comments:

Post a Comment

wanted officials