በሰበካ ጉባኤዉና አዲስ ተሹመው በማገልገል ላይ በሚገኙት አስተዳደር መካከል የተፈጠረዉን አለመግባባት ፕሪቶሪያ የሚገኘዉ ኢንባሲ በቀጥታ ኢጁን አስገብቶበታል:: እረዘም ላለ አመታት ቤተ ክርስቲያኗን ሲያገለግል የነበረዉ የሰበካ ጉባኤ በቀጥታ ከኢትዮጵያ በመጣ ደብዳቤ የታገደ ሲሆን ሰበካ ጉባኤዉ እግዱን አልቀበልም በማለት ጸንቷል የኢትዮጵያ ኢንባሲ ጣልቃ ገቦች ሰበካ ጉባኤዎችን በማስፈራራ ሐገርህ ቤት ሰርተሓል ከየት እንዳመጣህዉ ትናገራለህ በማለት እያስፈራሩ ሲሆን ሰበካ ጉባኤዉ በበኩሉ አዲስ ተሹመዉ የመጡት አስተዳደር አባ ጾመ ልሳንን በአስገድዶ መድፈር በተጭበረበረ የጉዞ ሰነድ መክሰሱን ተንተርሶ ጸቡ ተካሯል።
ወደ የሚመለከተዉ አካል የሰበካ ጉባኤዎቹን እቅድ ለማረጋገጥ የተንቀሳቀሱ አጣሪ ወገኖች እንደጠቆሙት ከኢትዮጵያ ኢንባሲ ደብዳቤዉ ትክክለኛ እነደሆነና አርፈዉ የታዘዙትን እንዲያከናዉኑ ማስጠንቀቂያ ደርሷቸዋል።
ጠቅለል ባለ መልኩ ወደ 14. 000. 000 ( አስራ አራት ሚሊዮን ) ራንድ የሚገመት ያህል ራንድ መጭበርበሩን እንደማስረጃ ይዘናል የሚል አካል በበኩሉ ጣቶቹን ወደ ሰበካ ጉባኤዎቹ እየጠቆመ ሲሆን። ቤተ ክርስቲያኗ ከፍተኛ ገቢ የምታስገባ ከመሆኗ አንጻር ሐገር ቤት የሚገኘዉን በአቡነ ማቲያስ የሚመራዉን ሲኖዶስ እንዲሁም የህወሃትን ቀልብ መሳቧን እማኞች አረጋግጠዋል፡፤
በዚህም የተነሳ ቀድሞ በቤተክርስቲያኗን ሲያገለግሉ የነበሩት አቡነ ያእቆብን በማንሳት የራሳቸዉን ደጋፊና አካል የሆኑትን አባ ጾመ ልሳንን በስተዳደርነት ያለ በቂ ደንብ ወደ ቤተ ክርስቲያኗ በማላክ በአንድ አመት ከስምንት ወር ብቻ ከምእመናን የተሰበሰበ በርከት ያለ ገንዘብ ወደ ሀገር ቤት ሲኖዶስ በኙሁ አስተዳደር በኩል የተላከ ሲሆን ሰበካ ጉባኤዉ በተመሳሳይ መልኩ ለስተዳደሩ የአንድ አመት ከ ስምንት ወር ደሞዝ ባለምክፈልና በማግለል ምክንያት ሁለቱ አካላቶች ተካረዋል።
የጆሃንስበርግ መድሔኒያለም ቤተ ክርስቲያን በደቡብ አፍሪካ በንግዱ ዘርፍ በመሰማራት በራሷ ስም የመዋለ ሕጻናትና በርከት ያሉ ሕንጻዎች ባለቤት መሆኗን የደረሰን መረጃ ያረጋግጣል።
ዛሬ 11/04/2016 ማምሻ ላይ አጠቃላይ ስብሰባ የተተራ ሲሆን የኢትዮጵያ ኢንባሲ እና ተወካዮቹ በሰበካ ጉባኤዎቹ ላይ እንዳሻቸዉ ሊያቅራሩና ሊያስፈራሩ እነደሚመቱ እየዛቱ እነደሆነ እየተሰማ ሲሆን የሰበካ ጉባኤዎቹ መካከል ኤርትራዊያኖችም እነደሚገኙበት ለመረዳት ተችሏል።
No comments:
Post a Comment