Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, April 6, 2016

የድምጽና ምስል ግንኙነት የሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ ክፍያ ለመጣል እየተመከረበት እንድሆነ ኢትዮ-ቴሌኮም አስታወቀ

የድምጽና ምስል ግንኙነት የሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ ክፍያ ለመጣል እየተመከረበት እንድሆነ ኢትዮ-ቴሌኮም አስታወቀ

ኢሳት (መጋቢት 28 ፥ 2008)
ቫይበርና ሌሎች የስልክ ጥሪ አገልግሎት የሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ ክፍያን ለመጣል አሊያም ሌሎች አማራጮችን ለመጠቀም ኢትዮ-ቴለኮም እየመከረ እንደሚገኝ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አንዱአለም አድማሴ ለጋዜጠኞች አስታውቀዋል።
አገልግሎቱን የመቆጣጠር ቴክኖሎጂ እንዳለው የገለጸው ድርጅቱ ከአገልግሎቱ ባለቤቶች ጋር በመደራደር አመታዊ የትርፍ ድርሻቸው ክፍያ እንዲፈጽሙ መግባባት እንደሚቻልም አመልክቷል።
በአገልግልቶቹ መስፋፋት ከፍተኛ ገቢን እያጣ እንደሆነ የሚገልጸው ኢትዮ-ቴሌኮም አማራጮችን በማየት የተሻለውን ለመጠቀም ምክክር እየተካሄደ እንደሆነም ይፋ አድርጓል።
የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች በበኩላቸው አዲስ ሊጣል የታሰበው ክፍያ አገልግሎቱን እንዳይጠቀሙ የሚያደርግ እንደሆነና የስልክ ቁጥሮች ምዝገባውም ቁጥጥር ለማጥበቅ የታሰበ ነው ሲሉ በመግለጽ ላይ መሆናቸውን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል።
ኢትዮጵያ በኢንተርኔትና በስልክ አገልግልቶች ላይ ከፍተኛ ቁጥጥርን የምታደርግ ሃገር መሆኗን የተለያዩ አካላት ሲገልፁ መቆየታቸው የሚታወቅ ሲሆን፣ ተግባራዊ ሊደረግ የታሰበውም አዲሱ ቁጥጥር ይህንኑ ድርጊት የሚያጠናክር እንደሆነም ተገልጿል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials