ሰኞ ሚያዝያ 3 ቀን 2008 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡30 ሰዓት አካባቢ በደረሰው አደጋ 18 ሰዎች ጉድጉዱ ውስጥ የሰመጡ ቢሆንም፣ ለሰባት ሰዓታት በተደረገ ከፍተኛ ጥረት የስምንቱን ሰዎች ሕይወት ለማትረፍ መቻሉን፣ የሻሸመኔ ከተማ ፖሊስ መምርያ አስታውቋል፡፡
መፀዳጃ ቤቱ የተቆፈረው መቼ እንደሆነ እንደማይታወቅና ይዞታው ግን የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፣ ያስቆፈሩት ግለሰብ መሞታቸውንና ‹‹ሕያው የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን›› የሚባለው የአምልኮ ማካሄጃ አዳራሽ ከተገነባ አንድ ዓመት እንደሆነው ገልጸዋል፡፡
ወደታች ሰባት ሜትር ጥልቀት ያለው ጉድጓድ በመሆኑ የሰመጡትን ሰዎች ለማውጣት በጣም አስቸጋሪ እንደነበር፣ ነገር ግን የአካባቢው ነዋሪዎችና ፌዴራል ፖሊስ ወደ ሥፍራው በመሄድ፣ በመቆፈሪያ ማሽን እየተቆፈረ የስምንት ሰዎችን ሕይወት ለማትረፍ መቻሉን ምክትል ኢንስፔክተር ታምራት ገልጸዋል፡፡ ከተረፉት ሰዎች አምስቱ ከፍተኛ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸውም አስረድተዋል፡፡
ምንጭ ሪፖርተር
No comments:
Post a Comment