ህወኃት ውጥረት ላይ ነው
ህወሓት እና ሕዝቡ አሁንም አልተግባቡም። ሕዝቡን ለማሳመን ስልጠናው ቀጥሏል።
ከሓምሌ 21/2006 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 16/2006 ዓ/ም ልዩ የሆነ የህወሓት ዝቅተኛ አመራር ስልጠና በትግራይ ክልል እየተሰጠ ይገኛል። ይህ ስልጠና ከቀጠና አመራሮች ጀምሮ እስከ ዞን የህወሓት መሰረታዊ አደረጃጄት እና ሴሎች በሙሉ ያቀፈ ነው። ስልጠናዊ በአንድ ጥናታዊ መጽሓፍ ተንተርእሶ በየ ገፁ እየተነበበ ሲሆን በተጨማሪመ በትግሉ ወቀት የተቀረፁት የተለያዩ የህወሓት ፊለሞች እየቀረቡ ይገኛሉ። ለሁሉም ተሰበሳቢ የክልሉ መስተዳድርና የህወሓት ሊቀ መንበር አቶ አባይ ወልዱ በላኩት ደበዳቤ መሰረት 80 ብር የዉሎ አበል ተወስኗል።
በሁሉም ዞኖች ለ6 ቀናት በተከታታይ የቀረበ አጀንዳ አንድ አይነት ነበር።
1. ህወሓት እንዴት ተመሰረተ?
2. በትግሉ ወቅት እንዴት ተንቀሳቀሰ?
3. ከትግሉ በኋላ እንዴት ነበር?
4. በአሁኑ የትግራይ ህዝብ ህወሓትን እንዴት ይመለከተዋል? የሚሉ ነበሩ።
በተለይ በመቀለ እየተካሄዳ ያለው ስልጠና ለምሳሌ ብንወስድ ሁሉም የመቀሌ ክ/ከተሞች ያቀፈ ሲሆን አይደር፣ ሰሜን፣ ሃወልቲ ሦስቱ በአይደር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ በሚገኘው አዳራሽ ሲሰበሰቡ ሐድነት፣ ቀዳማይ ወያነ፣ ኩሓ፣ ደግሞ በሃፀይ ዮወሃንስ ትምህርት ቤት በስልጠና ላይ ይገኛሉ። በሁለቱም የሰበሰባ ማዕከሎች ድርጅቱ ያልጠበቃቸው በርከት ያሉ ጥያቄዎች ተነሰቷል።
ከነዚህም ውስጥ
1. አብዛኛው ተሰበሳቢ በትግሉ ወቅት የተሳተፈና አሁን የተሰጠ ያለውን ስልጠና በተደጋጋሚ የወሰደ ከመሆኑም ባሻገር በእድሜ ሸምግለናል። ሰለዚህ እድሉ ለወጣቶች ለምን አልተሰጠም?
2. ድርጅቱ ከመመስረት ጀምሮ እሰከ ድል ባለን አቅም ሁሉ ተካፍለናል። አሁን ግን የትግራይ ህዝብ ተረስቶ የተገባለትን ቃል ሳያገኝ ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው የሚቀሰቀሰው?
3. እኛ በትግሉ ወቅት አካላችን የተጎዳን ታጋዮች መለስ ከዚህ ቀደመ ተደራጁ ብሎ 180 ሰዎች ሁነን ፈረስወአት እንዱስትሪ የሚባለውን ማህበር አቋቁመን መንቀሳቀስ ስንጀመር እውነት መስሎን ነበር። ኋላ ላይ ግን ሁሉም ታጋይ ከጨዋታ ውጭ በማድረግ 5 ሰዎች ድርጅቱን በግላቸው ስም በማዛወር ይዘዉታል። በዚህ ረገደ ህወሓት እያወቀ ፍቃደ ሰጥቷቸዋል። ታድያ ይህ ሁሉ በደል ተሸክመን እንዴት የህዝቡ በሶት በቻ ለማዳመጥ ትጠይቁናላችሁ?
4. በደርግ ግዜ የታገልን ታጋዮች የጡረታ መብታችን ሳይከበርልን በሻዕቢያ ወግያ የዘመቱ የጡረታ መብታቸው ተከብሮላቸዋል። ለምን ተለያየን?
5. ህወሓት ተላንት ሲከተለው የነበረው ዲሞክራሲያዊ መንገድ አሁን ትቶታል። በትግራይ የአሰተዳደረ ችግር፣ የፍትህ እጦት፣ ሙሰና በዝቷል። ሰለዚህ ህዝቡን በከባድ ችግር ላይ ነው ያለው። በህወሓት በኩል ምን አይነት መፍትሔ ተዘጋጅቷል? የሚሉና ሌሎች በዙ ጥያቄዎች ጎርፈዋል።
አንዳንዱ ከነቁጣና ስድብ ጭምር ሲናገር ነበር። ለማነኛው ስልጠናው ገና አላለቀም። አሁን ህወሐት በህዝቡ ያለውን አመኔታ ጥርጣሬ ውስጥ መግባቱ በሚገባ ተረድቶታል።ሁኔታው መግባባት ስላልፈጠረ ሕወሃቶች ውጥረት ውስጥ ስለገቡ የሰበሰቡትን ሕዝብ ለማሳመን ሌላ 3 ተጨማሪ የስልጠና ጊዜ ጨምረዋል።

No comments:
Post a Comment