Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, August 13, 2014

በትግራይ ክልል አራት መቶ ሺ ህዝብና በሚሊየን የሚቆጠሩ የቤት እንስሳትን የሚቀልብ በለስ ወደመ

በትግራይ ክልል አራት መቶ ሺ ህዝብና በሚሊየን የሚቆጠሩ የቤት እንስሳትን የሚቀልብ በለስ ወደመ

አቶ አስገደ ገ/ስላሴ
በትግራይ ክልል በምስራቃዊ ሰሜን፣በደቡባዊ ምስራቅ በደቡብ ዞኖች የሚኖሩ ከ 1.5 ሚሊየን የሚቀጠሩ እንስሳ ዘቤት የሚቀልብ በለስ የሚባል እፅዋት የህዋሃት መሪዎችና እነሱ የሰርዋቸዉ ደንቆሮ የሳይንስ ተመራማሪ ተብዬዎቹ ሃርና ቀለም ከበለስ አፍርተን ትግራይን ሃብታም እናደርጋታለን በሚል ጥናት የጎደለዉ አውዳሚ ባክቴርያ (ቫይረስ) ሊሆን ይችላል አስገብተዉ በበለስ እፅዋት በማራባታቸዉ ያ የተራባዉ ባክቴርያ ሃር ሳይሆን አመረተዉ ለዚሁ ለተጠቀሰዉ ህዝብ ከ 6ት ወር በላይ 95% የምግብ ፍጆታዉን ይሸፍናል። ሁሉም እንስሳ ዘቤትም አመት ሙሉ ከመመገባቸዉ ህዝሠቡ ለራሱ ለምግብነት ከመጠቀሙ አልፎ ለገበያ እየወረደ በመላዉ የኢትዮጵያ ክልሎች በማሰራጨትበመሸጥ ብዙ ብር ያፍስ ነበር። የነዚህ አካባቢ ህዝብ ከሚያዚያ ወር ግማሽ እስከ ጥቅምት ወር ከላይ እንደጠቀስኩት በሚመገቡት በለስ ነበር።
ስለ በለስ ጥቅም የትግራይ ክልል መሪዎች የነሱ ስሪት ምሁሮች የነሱ ተላላኪዎች የመቐለ ዩኒቨርሲቲ በለስ ተመራማሪዎች ምንም መነሻ የሚሆን የሳይንስ ግኝት በተጨባጭነት የሌላቸዉ ከበለስ ይህን የሚያክል ቶንክ ሃር ቀለም ማርማላት በማምረት በመቶ ሽዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ስራ እንፈጥራለን እያሉከ 13 አመት በላይ በነዛ የፈለጉት ውሸትና ማደናገሪያ ዲስኩራቸዉን የሚያሰራጩባቸዉ ሚድያዎች አድርገዉ ለትግራይ ህዝብ የህልም እንጀራ ያበሉት ነበር።ሌላ ቀርቶ የበለስ ግንድ በመቁረጥ ለምግብነት ለመጠጥ ፣ ለማርማላት ይጠቅማል ተብሎ ለሁሉም ፕሮጀክቶች የሚያስተባብሩ ቢሮ ተመስርቶ ከእርዳታ ሰጪ አገሮች ብዙ ውሸት የውሸት ፕሮጀክቶች እያዘጋጁ እርዳታም ያገኙ ነበር። ውጭ አገር እየሄዱም ስለ በለስ ምርምር ለልመና እንዲመቻቸዉ ብዙ የሃገራችን የውጭ ምንዛሪ በልተውታል ሰብስበውታል የየግላቸዉ ህንፃ ሰርተዋል።
ይህ ሁሉ የደንቆሮ ምርምር አሁን ተጋለጠ
የህወሃት ግብታዊ የሆነ የሳይንስ ግኝት ያሃርና ቀለም ያመርታል ብለዉ ያመጡት ክንችያ የተባለዉ ባክቴርያ በመቶ ሺ አመት የሚቆጠር ህዝቦች ከአመት የምግብ ፍጆታ ከ 60% የሚጠቀሙበት በባክቴርያ ወድሟል እየወደመም ይገኛል። ለዚሁ ለማስረጃነት በትግራይ ክልል ደቡባዊ ምስራቅ በደቡብ በተለይ በራያ መኾኒ ወረዳ በሕንጣሎ በአላጀ እንዲሁም በከፊል እንደርታ ወረዳ አፅቢ ወንበርታ ወረዳዎች ስፋቱ 300 ኪሎ ሜትር ቁመቱ 300 ኪሎ ሜትር ስፋት ( 36000 ስኴር ኪሎ ሜትር መሬት የበቀለ በለስ ሙሉ በሙሉ ወድሟል። ይህ እፅዋት ሞቶ እንደተጣለ እንስሳ በለስም ወደመ።በነዚህ አካባቢ የሚኖሩ ዜጎች ተርበዋል እንስሶችም የሚበሉት አጥተዉ እየሞቱ ይገኛሉ።ለህዝብ የሚበላ ለእንስሳ መኖ የሚሰጥ ወገን የሚሰማቸዉ መሪዎች የሉም። በተለይ ደግሞ ትልቅ አደጋ ደርሶባቸዉ በሞዴልነት ለመጥቀስ በድሮ የዋጅራት ወረዳ ደቡብ 76000 ዜጎች ለመጥቀስ በራያም እንደዚሁ መኾኒ ወረዳና አካባቢዋ ከ 80000 ህዝብ በላይ ረሃብ ላይ ወድቀዋል እንስሳት እየሞቱ ናቸዉ።
የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ተመራማሪ ሳይንቲስቶች በህዝባችንና በንብረቱደርሶ ላለዉ የምርምራቸዉ ውድቀት አሳፍሯቸዉ ለሁኔታዉ ተቆርቋሪ ሆነዉ ከመቅረብ ዝምታን መርጠዉ ድምፃቸውን ደብቀዉ ይገኛሉ ።ህዝቡ ግን በተለይ የሕንጣሎ ዋጅራት የመኾኒ ወገኖች እስከ የክልሉ ፕሬዚደንት ኣባይ ወልዱና ኪሮስ ቢተዉ ኣቤት ቢሉም ሰሚ ጆሮ አላገኙም።
የዋጅራት ህዝብ በበለስ መውደም ብቻ አይደለም የከሰረዉ ሰፊ የእርሻዉ ማሳዉ መቐለ ለሚገኘዉ ስሚንቶ ፋብሪካ የሚጠቅም አፈር ስላለዉ ኢፈርት ምንም ግምት ሳይሰጥ መሬቱን ቀምቶት ይግኛል። ከዚህ አፈር የተወሰነ ኮሚሽን እንኳ ቢከፈለዉ ለ 76000 የዋጅራት ህዝብ ይቀበለዉ ነበር ኢፈርት ግን አንድ 2ጃ ደረጃ ት/ቤት ሰርተንላችሁ በማለት እያተላሉዋቸዉ ይገኛሉ። እነዚህ ዜጎች የይገባኛል ጥያቄ ሲያነሱም ብዙ ሰዎች በማሰር ሽብር ፈጥራቹሃል ተብለዉ በእስር ተሰቃይተዋል ለአፍ ጉርስ በማጣ ታቸዉ አዛውንት ሴቶች ህፃናት ለስደት ሲፈልሱ ወጣቶች ወ ደ አረብ አገር ተሰደዉ ሲሰቃዩ ለነዚህ ወገኖች እንደ ማዘን ፈንታ በነዛ እኛ ባልናቸሁ ተንፍሱ ተብለዉ የሚታዘዙ የመንግስትና የፓርቲ ሬድዮ ጣቢያዎች ከኤፍኤም ቴሌቪዢን አድርገዉ እነዚህ ለልመና ለስደት የሚፈልሱ ሰዎች ባቋራጭ ለማደግ የሚፈልጉ ተብለዉ ሰብኣዊ መብታቸዉ ተነክተዋል። በተለይ ደግሞ ሰሓረቲ ሳምረ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ ወገኖች እጅጉን ሃብታሞች ነበሩይሁን እንጂ በ 17 አመቱ የትጥቅ ትግል ጊዜ ልጆቻቸዉ ወደ ትግል አክትተዉ የተሰዉባቸዉ ቤታቸዉ ተቃጥሎባቸዉ ሃብታቸዉ በደርግ ተወርሶ የቀረረዉ ሃብታቸዉ ለህዋሃት አስረክበዋል። ብዛት ያላቸዉ ወገኖችም ለህወሃት አመራርና ካድሬዎች ጥያቄ አንስተዉ በመቃወማቸዉ ብዙ ታስረዋል ከባድ ቅጣት ተቀጥተዋል ተሰቃይተዋል ባሁኑ ጊዜ ….. እነዚህ ከጥንት ጀምረዉ እምቢ ለጭቆና አንገዛምብለዉ ያምፁ የነበሩ በመሆናቸዉ ይህ መንግስት የነዚህ ወገኖች ጥንካሬ አይፈልግም ያሰጉታና።
mekelle university
አሁን እነዚህ የበለስ አብቃዮችና ተጠቃሚ ወገኖች የነዛ በለሳቸዉ የወደመባቸዉ ዜጎች በመመልከታቸዉ እያነሱት ያለዉ ጥያቄ የህወሃት ስሪት የዩኒቨርሲቲ ምሁራን እርሻና የተፈጥሮ ሃብት ባለሞያዎች ያላነነሱት ጥያቄ ከቺንያ የሚባል ባክቴርያ ወይም (ቫይረስ) 1ኛ ወደ ሁሉ የበለስ አብቃይ ከባቢዎችከተዘመተ የወደፊት እጣ ፈንታችን ምን ይሆን? 2ኛ ወደ ሌላ እፅዋትና የእርሻ ሰብል ክዘመተ እቺ ኣገር ምድረ በዳ ትሆናለች 3 ይህ በሽታ ሂወት ያለዉ እፅዋት አውዳሚ ከሆነ ከሆነ ሰውና እንስሳም ሂወት ያላቸዉ በመሆናቸዉ ለዜጎች ያለዉ ጠንቅነት ምን ሊሆን ይችላል ። ምክንያቱም ባክቴርያዉ በንፋስ ሃይል እየተዘመተ ስላለ አንድ እርምጃ መውሰድ አለበት ይላሉ። የትግራይ የበለስ ተጠቃሚ ወገኖች 4 ይህ እፅዋት አውዳሚ ኤድስ ወደ አገራችን ያስገቡ የህወሃት ባለስልጣናትና ምሁራን ወደ ፍርድ ይቅረቡልን እያሉም ይገኛሉ 5 የዋጀራት ብቻ የወደመው በለስ በመንግስት ትግራይ የተጠናው በኣንድ አመት 750 ሚሊየን ብር የሚገመት ኪሳራ አጋጥሟል የአላጀ፣ የእንደርታ ራያ ዓዲቐይሕ መኾኒ ቤት ማራ የወደመዉ በለስ ሲገመት በቢሊየን የሚቆጠር ብር ነዉ ይህ የእንስሳትና የሰዉ ሞት ሳይጨምር ነዉ።
6 ይህ በሽታ መንግስት ክልል ትግራይ ስላመጣዉ እሱ ወደ ፍርድ ቤት ቀርቦ የፌደራል መንግስት ይድረስልን እያለ ነዉግን ማን ሰማውና?
7 የሃገራችን ህዝቦች ለምን ችግራችንተረድቶ ችግራችን እንዲፈታለን ለመንግስት ተፅኖ አያሳድርም ?አሁንም ይድረስልን እያለ ነዉ
8 የሃገራችን ብቁ ምሁሮች ተመራማሪዎች በነዚህ የህወሃት ስሪት የልማት ሰራዊት ተብዬዎች የደረሰብን ኣደጋ ተረድታችሁ ዝምታን መምረጣችሁ ስህተት ነዉ ይላል የዋጅራት ህዝብ
9 የሃገራችን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለዜጎችህ ፍትህ ነፃነት የመኖር ፣ የመስራት መበት ለማረጋገጥ እንታገላለን እያላችሁ ከ 400ሺ ህዝብ በላይ በከችንያ ኤድስ ህዝብ ቀለብ ሲወድም ዝምታ መምረጣችሁታዲያ ለማን ነዉ የምትታገሉት ብሎ ይወቅሳል
ከላይ የተዘረዘሩት የህዝብ ጥያቄዎች በኔ እምነት ትክክል ናቸዉ እላለሁ። እኔም ባክቴርያዉ ያለ ጥናት ያስገቡ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ ተመራማሪዎች የትግራይ ክልል ባለስልጣናት በሙሉ የኪቺኒያ ቫይረስ ሲገባ ትግራይ የሃር ክምር በማምረት በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር ገቢ ያገኛል ብለዉ የዋሹ የመንግስትና የፓርቲ ሚዲያዎች ወደ ፍርድ ቤትይቅረቡ የወደመዉ በለስ ካሳ ለህዝቡ ይሰጥ ለዘላቂ ጊዜም መቋቋሚያ ይሰጣቸዉ። የቀረዉ በለስ እንዳይወድም በምን እንከላከለዉ ምን እርምጃ ይወሰድ መልስ ማግኘት አለበት።ለወደመውስ እንዴት ወደ ነበረበት ይመለስ የሚል መልስ ማግኘት አለበት። ሃይለማርያም ደሳለኝም ከአንድ ሚሊየን ህዝብ በላይ አሸብሮ ላለዉ የኪንችያ ቫይረስ እንደ ማሸበር ለሰላም ለሚታገሉ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራር አባላት እያሸበሩና እያሰሩ ይግኛሉ። በመሆኑ ለኪንቺያ ባክቴርያ አለመጋለጣቸዉ ሃይለማርያም ደሳለኝና አለቆቻቸዉም በደረጃቸዉ መፈረድ አለባቸዉ የህግ የበላይነት አለ ከተባለ የሃገራችን የህዝብ ተወካዮች ፓርላማም ይህ አደጋ እያወቀ ዝምታ መምረጡ እጅጉን ሃላፊነት የጎደለዉ ከመሆኑም በተለይ ከሕንጣሎ ዋጅራት ከአላጀ ከመኾኒ ከእንደርታ ከአፅቢ ወንበርታ ወረዳዎች የተወከሉ የፓርላማ አባላት በወከላቸዉ ህዝብ ደርሶ ያለዉ አደጋ አለማጋለጣቸዉና መፍትሄ ለማግኘት አለመጣራቸዉ ለህዝብ ሳይሆን ውክልናቸዉ ለሆዳቸዉ መሆኑ ውክልናቸዉ ያሳያል። በነገብሩ በቀድሞ የትግራይ ክልል መሪዎች ጊዜ የበለስ አትክልት እንደ የድህነት ማጥፊያ ተቆጥሮ በትግራይ ክልል እንዲስፋፋ ይተከል የነበረዉ ከትግራይ አልፈሎ ወደ መላዉ የሃገራችን ክልሎችም እየተቆረጠ ይሄድ የነበረዉ አሁን እንደዚህ ሆኖ የወደመ ዝም ብለዉ ለሚመለከቱ ባለስልጣናት ሃይለማርያም ደሳለኝ እርምጃ እንዲወስድ ካላደረጉ ራሳቸውም ተባባሪ የበለስ አሸባሪ ሆነዋልማለት ነዉ።
የድረሱልኝ ጥሪ
በሃገራችን የሳይንስ ተመራማሪዎች ይህ የበለስ ቫይረስ በበለስ ላይ እያደረሰ ያለዉ ውድመት በሌሎች እፅዋት እንስሳ ሰዉ አደጋ እንዳይደርስ ከአለም አቀፍ የሳይንስ ምርምር በመተግበር ድርሻችሁንብትወጡ ጥርዬን አቀርባለሁ ይህ በሽታ ነገ ሃገራዊ ሊሆን ይችላል።
በትግራይ ክልል በሰሜን ምእራብ ዞን በታሕታይ ቀራሮ በፃዕዳ የእምባ ቀበሌ ( በቖላቑል) የጀመረዉ መድሃኒት ያልተገኘለት ሰዉ ጨራሽ በሽታ አሁን በወልቃይት በፀለምቲ ባድመ አድያቦ አድዋ ተምቤን ነጋሽ አንዲሁም ወደ አገውና መተማ የተስፋፋዉ ይህ ኪንቺያ የሚባል የበለስ ባክቴርያ ተስፋፍቶ ተፈጥሮ እንዳይጨርስ አሁንም የሳይንስ ምሁራን የዜግነት ግዳጃችሁን ብታውቁ።
በውጭ አገር የምትገኙ ኢትዮጵያወያን ሁሉ በምስራቅ ፣ በደቡብምስራቅ በደቡብ ትግራይ ዞኖች ተፈሮ ያለዉ በበለስ እፅዋት ቫይረስ የአለም የሳይንስ ምሁራን ይምርምር እርዳታዎን እንዲለግሱ ታደርጉ ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለሁ::
የሃገራችን የሃይማኖት መሪዎች የእድሜ ባለፀጎች የተቀዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ምሁራን ተማረሚዎች ወጣቶች ማህበራት ይህ አደጋ ለመከላከል የአቅማችሁን በመስራት ለመንግስት ተፅእኖ በማድረግ የተለመደዉ ልግስናችሁን ትችሩ ዘንድ ጥርዬን አቀርባለሁ።
ባገር ውስጥና በውጭ የምትገኙ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ለዚህ በበለስ እፅዋትና የበለስ ተጠቃሚዎች የሆኑ ዜጎች የመኖር መብት የመኖር አቤት በቦታዉ መጥታችሁ ምስክርነታችሁን ትሰጡ ዘንድ ጥሪዬን አቀር ባለሁ። እንደዚሁ ያገር ውስጥና የውጭ እርዳታ ለጋሽ የመሆናችሁ ለዚህ ህዝብ ድረሱለት ህዝብ እየተበታተነ ነዉ።
በሃገራችን ያላችሁ የነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞች ከያኒዎች ፀሃፊዎች አመደኞች በዚህ በተሸገረዉ ህዘብ በአካል አይታችሁ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለአለም አስታውቁት በተጨማሪ የውጭ ብዙሃን መገናኛም ለዚህ አዲስ አ ደጋ ተከታትላችሁ ብትዘግቡት
የሃገራችን የወገን ወዳጅ የሆናችሁ ጠበቆች ለዚህ እፅዋት አውዳሚ ቫይረስ ያስገቡ ህዝቡ ለረሃብ ለስደት የዳረጉ ባለስልጣናትና ተመራማሪ ተብዬዎች ደንቆሮ ዶክተሮች ወ ደ ህግ አቅርባችሁ ታስፈርዱዋቸዉ ዘንድ ደግሜ ጥርዬን አቀርባለሁ በተለይ በቅርብ የምትመለከቱት ያላችሁ በመቐለ የምትገኙ ጠበቆች በቆራጥነት በህግ ድጋፍ ብታደርጉ ለወገን ደራሽ ወገን ነውና::

No comments:

Post a Comment

wanted officials