ሰሞኑን ከተሰደዱት የነጻው ፕረስ ጋዜጠኞች ጋር የተደረገ ኢንተርቪው ከሜልቦርን ሬዲዮ ጋር
(በስተመጨረሻ ያለውን ሊንክ በመጫን ኦዲዮውን ያድምጡ)
በአምስት ሣምንታዊ መጽሔቶችና አንድ ጋዜጣ ላይ የተመሰረተውን ክስ ተከትሎ አስራ አንድ ጋዜጠኞች ለስደት ተዳረጉ። አስራ አንዱ ጋዜጠኞች የተሰደዱት በፍትህ ሚኒስቴር ሐምሌ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. “የዐመጸ ቅስቀሳና የሐሰት ወሬዎችን በመንዛት ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመናድ ጥረት አድርገዋል” በተመሰረተባቸው ክስ መሆኑን የደረሱን መረጃዎች ያስረዳሉ።

ፍትህ ሚኒስቴር ክስ የመሰረተባቸው ሎሚ፣ ዕንቁ፣ ፋክት፣ ጃኖ እና አዲስ ጉዳይ መጽሔቶች እና አፍሮ ታይምስ ጋዜጦች ሲሆኑ፤ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ አስራ አንድ ጋዜጦች ለስደት መዳረጋቸውን ለማረጋገጥ ችለናል።
ተሰዳጆቹ ጋዜጠኞች
1፣ ቶማስ አያሌው (የአፍሮ ታይምስ ጋዜጣ ማኔጂንግ ዳይሬክተር)፣
2፣ ግዛው ታዬ (የሎሚ መጽሔት አሳታሚ እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር)፣
3፣ ዳንኤል ድርሻ (የሎሚ መጽሔት ሚዲያ ዳይሬክተር)፣
4፣ ሰናይ አባተ ቸርነት (የሎሚ መጽሔት ዋና አዘጋጅ)፣
5፣ አቦነሽ አበራ (የሎሚ መጽሔት ከፍተኛ ሪፖርተር)፣
6፣ ሰብለወንጌል መከተ (የሎሚ መጽሔት ከፍተኛ ሪፖርተር)፣
7፣ እንዳልካቸው ተስፋዬ (የአዲስ ጉዳይ መጽሔት አሳታሚ)፣
8፣ ኢብራሂም ሻፊ (የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ምክትል ዋና አዘጋጅ)፣
9፣ እንዳለ ተሼ (የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ከፍተኛ አዘጋጅ)፣
10፣ ሃብታሙ ስዩም (የአዲስ ጉዳይ አዘጋጅና አምደኛ) እና
11፣ አስናቀ ልባዊ (የጃኖ መጽሔት አሳታሚ እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር) ናቸው።
ጋዜጠኞቹ የተሰደዱት በደረሰባቸው ወከባ፣ እንግልት፣ ማስፈራራት፣ የቢሮ መታሸግ እንዲሁም ፍትህ ሚኒስቴር በመሰረተባቸው የክስ እስከ አስራ ስድስት ዓመት በእስር ሊቆዩ እንደሚችሉ በመረዳታቸው መሆኑን ለመረዳት ችለናል።
ኦዲዮውን ለመስማት ሊንኩን ይጫኑ-
No comments:
Post a Comment