Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, August 27, 2014

የደቡብ ጎንደር የመኢአድ ዋና ጸሃፊ ባልታወቁ ሰዎች ታፍነው ተወሰዱ

የደቡብ ጎንደር የመኢአድ ዋና ጸሃፊ ባልታወቁ ሰዎች ታፍነው ተወሰዱ

ነሃሴ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-

የመኢአድ የሰሜን ጎንደር የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ የሆኑት አቶ ዘመነ ምህረት ለኢሳት እንደገለጹት የደቡብ ጎንደር ዋና ጸሃፊ አቶ ጥላሁን አድማሴ ባለፈው ቅዳሜ 8 ሰአት ላይ በ6 ፌደራል ፖሊሶች ታፍኖ መወሰዱን ገልጸዋል።
ፖሊሶቹ መሳሪያ አለው በሚል ፍትሻ አድርገው የነበረ ቢሆንም ምንም አለመገኘታቸውንና አቶ ጥላሁንን ወዳልታወቀ ቦታ መውሰዳቸውን አቶ ዘመኑ ገልጸዋል።
 
በሰሜን እና ደቡብ ጎንደር እየደረሰ ያለው ግፍ በዚህ አያበቃም ያሉት አቶ ዘመነ፣ በጭልቃ ወረዳ ሰብሳቢው 3 አመት ተወስኖበት በይግባኝ እንዲፈታ መደረጉን፣ ሊሞ ከምከም ወረዳ ይፋግ ከተማ ላይ ሞላ ወረታ የተባለ የፓርቲው አባላት በፖሊስ ተደብድቦ መገደሉን፣ አርባያ ከተማ ላይ ሞላ የሚባል
የድርጅት ጉዳይ ሃለፊ መታሰሩን፣ የደቡብ ጎንደር ሰብሳቢ ቤታቸው ፈርሶባቸው መግቢያ ማጣታቸውን እንዲሁም እርሳቸውን እየተከታተሉዋቸው መሆኑን ገልጸዋል።የፓርቲው አባላት መንግስት የሚያከፋፈልውን ስኳር እና ሌሎች እርዳታዎችን እንዳያገኙ መደረጋቸውን ገልጸዋል።
አቶ ዘመነ እንደሚሉት መኢአድ በአካባቢው ከፍተኛ ህዋስ መመስረቱና ገዢው ፓርቲ በመጪው ምርጫ እንደማያሸንፍ በመረዳት እየወሰደ ያለው እርምጃ ነው ብለዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials