Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, August 29, 2014

በአዲስአበባ የሞባይልና ኢንተርኔት አገልግሎት መዳከም አሳሳቢ ሆኗል

በአዲስአበባ የሞባይልና ኢንተርኔት አገልግሎት መዳከም አሳሳቢ ሆኗል

የኢትዮ- ቴሌኮም በአዲስአበባ የኢንተርኔት አገልግሎትን በማሳደግ የ4ጂ አገልግሎት መስጠት የሚችልበት ደረጃ
ደርሻለሁ ቢልም የአገልግሎቱ ጥራት በከፍተኛ ደረጃ እየወደቀ መምጣቱ ተጠቃሚዎች በከፍተኛ ደረጃ ምሬት ውስጥ እየከተተ ነው፡፡
በ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ወጪ የቻይናዎቹ ሁዋዌ እና ዜድቲኢ የሚባሉ ኩባንያዎች የማስፋፋፊያውን ፕሮጀክት ለመስራት ከኢትዮቴሎኮም ጋር በዚህ ዓመት መጀመሪያ የተፈራረሙ ሲሆን የአዲስአበባው ፕሮጀክት እስከሰኔ ወር 2006 ዓ.ም መጨረሻ ተጠናቆ የተሻለ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሎ ነበር፡፡ ኢትዮቴሌኮም የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ በስኬት ተጠናቋል በሚል ተደጋጋሚ መግለጫ የሰጠ ሲሆን ነገር ግን በአሁኑ ወቅት የሞባይል ሒሳብ ለመሙላትና ቀሪ ሒሳብ ለመጠየቅ አለመቻል፣ የፈለጉትን ሰው በቀላሉ ደውሎ ማግኘት አለመቻል፣ ያልደወሉበት ሒሳብ መቆረጥ፣ የሞባይል ኢንተርኔት በተለይ ፈጣን ነው የተባለውን 3ጂ ጨምሮ ደካማ መሆን፣ የፌስቡክ አካውንት አለመከፈት፣ የገመድ አልባ ኢንተርኔትና ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት መቆራረጥና ደካማ መሆን በስፋት እየታየ ነው፡፡
ያነጋገርናቸው ተጠቃሚዎች የአፍሪካ ህብረትና የሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት የሆነችው አዲስአበባ ጥራት ያለው የሞባይልና ኢንተርኔት አገልግሎት ብርቋ መሆኑ እንደሚያሳዝናቸው ተናግረዋል፡፡ አንድ አስተያየት ሰጪ እንዳሉት ኢትዮቴሌኮም የተሻለ ማስፋፊያ አድርጌለሁ እያለ በተግባር ይህ አለመታየቱ ምናልባትም መንግሥት በተለይ በማህበራዊ ድረገጾች እየተሰነዘረበት ያለውን ጠንካራ ተቃውሞና ትችት ለማፈን የተጠቀመበት አዲስ ዘዴ ሊሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ እንደገባው ተናግሮአል፡፡
የኢንተርኔት ኔትወርክ እንደመብራት ብልጭ ድርግም እያለ ብዙዎች በመበሳጨት አገልግሎቱን እየተው ነው ያለው አስተያየት ሰጪያችን መንግሥት በዚህ ሒደት ከሚያጣው ገንዘብ ይልቅ ተቃዋሚዎቹን ለማፈን ትልቅ ግምት ሳይሰጠው እንዳልቀረ አስረድቷል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials