Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, August 27, 2014

ከጅቡቲው ፕሬዚዳንት ግድያ ሙከራ በስተጀርባ ያለው ማን ነው?

ከጅቡቲው ፕሬዚዳንት ግድያ ሙከራ በስተጀርባ ያለው ማን ነው?

  • 1104
     
    Share
ከመላኩ ጸጋው/ሰንደቅ ጋዜጣ
የጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ በአዲስ አበባ ሰሞኑን የተካሄደውን የኢጋድ ስብሰባ ተካፈለው ሲመለሱ ከተቃጣባቸው የግድያ መትረፋቸውን የሀገሪቱን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር መሀመድ አሊ የሱፍን ጠቅሶ ብሉምበርግ ትናንት ባሰራጨው ዘገባ ገልጿል። በሀገሪቱ ዋና አውሮፕላን ማረፊያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ታጣቂ ወታደር በከፈተው ተኩስ የፕሬዝዳንቱ የግል ዶክተር ሁለት ጊዜ ደረታቸው አካባቢ እንዲሁም አንድ ጥይት ደግሞ ጭንቅላታቸውን በጨረፍታ ያገኘው መሆኑ ታውቋል። ተኩስ ከመከፈቱ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ፕሬዝዳንቱ ከኤርፖርቱ ወደ ቤተመንግስታቸው ያመሩ መሆኑን ዘገባው ያመለክታል።
Djibouti President ismael











ተኩሱን የከፈተው ወታደር በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ከዚህ ጥቃት ጀርባ የማን እጅ እንዳለ የማጣራቱ ስራ እየተካሄደ ነው ተብሏል። ባለፈው ግንቦት ወር በአንድ የጅቡቲ ሬስቶራንት ውስጥ የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት መድረሱን ተከትሎ አልሸባብ ኃላፊነቱን ከወሰደ በኋላ ሀገሪቱ የፀጥታ ጥበቃዋን ለማጠናከር ተገዳለች። በዚሁ ጥቃት የበርካታ የውጪ ሀገራት ዜጎች የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሲሆን ይህም በሀገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያው የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት የተባለለት ነው። ጥቃቱ ከተፈፀመ በኋላ አሜሪካ ወደ ጅቡቲ የሚጓዙ ዜጎቿ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማስጠንቀቂያ የሰጠች ሲሆን እንግሊዝም አልሸባብ በጅቡቲ በሚገኙ የምዕራባውያን ጥቅሞች ላይ ሌሎች የሽብር ጥቃቶችን ሊሰነዝር የሚችል መሆኑን በወቅቱ ገልፃ ነበር።

No comments:

Post a Comment

wanted officials