Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, August 23, 2014

በሳውዲ አፈሳው ተጠናቅሮ ቀጥሏል ዋንኛ ሰለባዎቹ ኢትዮጵያውያን ናቸው

በሳውዲ አፈሳው ተጠናቅሮ ቀጥሏል
ዋንኛ ሰለባዎቹ ኢትዮጵያውያን ናቸው ተብሏል
http://www.goolgule.com/crackdown-continues-ethiopians-are-targeted-in-saudi/
ማለዳ የሳውዲ ፀጥታ ሃይሎች በሪያድ ከተማ በኢትዮጵያውያን ላይ ያነጣጠረ አፈሳ ማድረጋቸውን የሪያድ ምንጮች ገለጹ። የሳውዲ አረቢያ መንግስት ያለመኖሪያ ፈቃድ የሚኖሩ ህገወጥ የውጭ ሃገር ዜጎች ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የሚገልጸውን መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ የፀጥታ ሃይሉ በወሰዱት እርምጃ ከ1 መቶ 80 ሺህ በላይ እትዮጵያውያን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የሳውዲን ምድረ ለቀው ወደ ሃገር መመለሳቸው ይታወሳል።
ይህ በዚህ እንዳለ የሳውዲ ከስደት ተመላሽ ወገኖችን መልሶ የማቋቋም ከፍተኛ ሃላፊነት የተጣለበት የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉንም ለማድረግ በተደጋጋሚ ቃል ቢገባም በወቅቱ የዓለምን ህዝብ ትኩረት ስቦ የነበረው የኢትዮጵያውያኑ ጉዳይ እስኪረጋጋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቴድሮስ አድሃኖም ከስደተኛው ጋር ፎቶ በመነሳት በኢቲቪ ሲሰራጭ ከነበረው ሰፊ የዜና ሽፋን ባሻገር ስደተኛው ምንም አይነት ማቋቋሚያም ሆነ ድጋፍ እንዳልተደረገለት ይነገራል።
በተለይ የስደት አለም ህጻናት ልጆቻቸውን ታቀፈው ለሃገር የበቁ እናቶች ለጎዳና ተዳዳሪነት የተዳረጉበት አስዛኝ ታሪክ የአብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ሆድ አላውሷል።
መንግስት በወቅቱ አዲስ አበባ በስደተኞቹ እንዳትጨናነቅ የስደተኞቹ ጉዳይ በየክልሉ ባለስልጣናት ይታያል በሚል ሽፋን በመቶሺህ የሚቆጠረውን ስደተኛ በየጉራጉሩ ወሽቆ ነገሮቹን ለማድበስበስ ቢሞክረም አብዛኛው ወገኖች በቋፍ ላይ ያለችውን ህይወታቸውን ለመታደግ አቅም ያለው አይቀሬውን ሞት በመጋፈጥ፤ በህይወቱ ቆርጦ ሳውዲ አረቢያ ለመግባት ቀይ ባሀርን በጀልባ አቋርጧ ለዳገም ስደት ተዳርጓል።
በአንጻሩ በሰው ሃገር ወልዶ ከብዶ በወቅቱ ያገኛት በነበረች የዕለት ገቢው ከእጅ ወደ አፍ የሆነ የስደት አለም ጎጆውን አሙቆ ያለጥሪት ይኖር የነበረው አባወራ ያቺን ቀውጢ ወቅት መቋቋም ተስኖት የቤተሰቦቹን ህይወት ከወረበሎች ለማዳን ወደ ሃገሩ እግሬ አውጪኝ ቢልም ያልጠበቀው ገጥሞት የሞቀ የስደት ዓለም ትዳሩን መቅኔ ያሳጣውን የመንፉሃው ሁከት እየረገመ በገዛ ሃገሩ ሰማይ ተድፍቶበት ለልጆቹ የዕለት ጉርስ ዳቦ መግዣ አጥቶ የህጻናቱን ስቃይ እና መከራ ላለማየት እግር ወዳመራው ሲኳተን በረሃ በልቶት እንደወጣ የቀረውን ከሳውዲ ስደት ተመላሽ ኢትዮጵያዊ ቤት ይቁጠረው።
ይህ ባለበት ሁኔታ የሳውዲ ፀጥታ ሃይሎች ሐሙስ ዕለት ሐሙስ ባደረጉት የተጠናከረ የቤት ለቤት ፍተሻ ከ1 ሺሕ በላይ ህገ ወጥ ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የሚናገሩ ምንጮች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ጉዳዩን የበለጠ አሰደንጋጭ ያደርገዋል። የፀጥታ ሃይሉ ከህብረተሰቡ በሚቀርብላቸው መረጃ መሠረት ዘመቻውን በቀጣይነት በሪያድ ከተማ በተለምዶ ነሲም አል ሃማም እና ጉቤራ እየተባሉ የሚጠሩ መንደሮችን በማማከል አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ማረጋገጥ ተችሏል።
ከአንድ ወር በፊት በሪያድ ከተማ የአንድ ወህኒ ቤት ግርግዳ ደምርሰው ኢትዮጵያውያኑን ጨምሮ ቁጥሩ በውል የማይታወቅ እስረኞች ማምለጣቸው ይታወሳል። ሐሙስ መንፉሃ ውስጥ በተካሄደው የቤት ለቤት ፍተሻ በኢትዮጵያውያን ላይ ስለደረሰው እንግልት ወደ ሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ስልክ በመደወል ለማረጋገጥ ባደረኩት ጥረት አንድ ስሜ እንዳይገለጽ ያሉ ዲፕሎማት የቤት ለቤት ፍተሻው በኢትዮጵያውያኖች ላይ ብቻ ያነጣጠረ እንዳልነበረ ገልጸው በዘመቻው ወቀት ከፍተኛ የሳውዲ ፀጥታ ሃይል መኮንኖች እና የመዲናይቱ ባለስልጣናት የቅርብ ክትትል እና ቁጥጥር ያደርጉ እንደነበር ተናግረዋል።
ሲቀጥሉም እርምጃው በባህር የመጡ የመኖሪያ ፈቃድ በሌላቸው ህገወጥ የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ብቻ ያነጣጠረ እና በየትኛውም ዜጋ ላይ ምንም አይነት እንግልት ያለተፈፀመ ጥንቃቄ የተሞላበት ዘመቻ እንደነበር አረጋግጠናል ብለዋል። በማስከተል “ትላንት የሸኛችኋቸውን ኢትዮጵያውያን ደግማችሁ ዛሬ ስትሸኙ ምን ይሰማችኋል?” ላልኳቸው ጥያቄ ምላሽ ሳይሰጡኝ ተሰናብተውኛል።
ዛሬ ማለዳ መንፉሃ ውስጥ በሳውዲ ፀጥታ ሃይሎች ተካሄደ በተባለው የቤት ለበቤት አፈሳ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ከአካባቢው ነዋሪዎች እና ወህኒ ከሚገኙ ወገኖች መረጃ በማሰባሰብ በሰፊው ለመዘገብ የማደርገው ጥረት ይቀጥላል።
Ethiopian Hagere Jed Bewadi በፌስቡክ በኩል ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የላኩት

No comments:

Post a Comment

wanted officials