Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, August 23, 2014

የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር በአዲስ አበባ በቁም እስር ላይ መሆናቸው ተጠቆመ።

ከሶሕዲፓ አመራርነት በደህንነት ሹሙ አቶ ጌታቸው አሰፋ ትእዛዝ ታግደዋል።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
የምስራቅ ኢትዮጵያ ክልል የሆነችው ሶማሊያ ርእሰ መስተዳደር የሆኑት አብዲ መሃመድ ኦማር አብዲ ኢሌ በደህንነት ሹሙ በአቶ ጌታቸው አሰፋ ልዩ ትእዛዝ በአዲስ አበባ በቁም እስር ላይ መሆናቸው ታውቋል። እስከ መጭው ምርጫ ድረስ በክልሉ ባለው ሁኔታ ላይ ተከታታይ ውይይቶች ለማድረግ ስለምንፈልግ ወደ ጅጅጋ እንዳይመለሱ በሚል ሰበብ በአዲስ አበባ እንዲቆዩ እና በደህንነት አይነ ቁራኛ ስር እንዲውሉ ተደርጓል።
በጥቅም ከርእሰ መስተዳደሩ የተቆራኙ በክልሉ ያሉ ባለስልጣናት እና የመከላከያ ሰራዊት ጄኔራሎች እንዲሁም የፌዴራሉ አንዳንድ ባለስልጣናት አቶ አብዲ ወደ ጅጅጋ እንዲመለሱ ወይንም በፌዴራሉ ውስጥ አነስተኛ ስልጣን እንዲሰጣቸው የደህንነት ሹሙን በመለማመጥ ላይ መሆናቸው ተያይዞ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል። ራሳቸውን ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትእዛዝ ውጪ አድርገው ሲናገሩ እና በክልሉ ከሳቸው ውጪ ማንም ባለስልታን አይመለከተውም በማለት ሲዘባነኑ የነበሩት አቶ አብዲ በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ ላይ የትም እንዳይንቀሳቀሱ መደረጉ አስደንጋጭ ሆኖባቸዋል።
በክልሉ በስልጣን ላይ ያለው ፓርቲያቸው አመራሮች በየጊዜው ለሕወሓት መራሹ መንግስት በሚያቀርቡት አቤቱታ መሰረት አቶ አብዲ እና ቤተሰቦቻቸው ከጎሳቸው ጭምር ክልሉን ተቆጣጥረው እየገደሉ እየበዘበዙ ስለሆነ መፍትሄ ሲጠይቁ እንደነበር ታውቋል።ስራቸውን መስራት እንዳልቻሉ እና አቶ አብዲ እንደራሱ የግል አሽከር እንደሚቆጥራቸው አማረው ለጠቅላይ ሚኒስትራቸው አመልክተው ነበር። በክልሉ ለተስፋፋው ሙስና የዘር ማጥፋት ወንጀል እና ሰቆቃ ከሕወሓት መሪዎች ጎን ለጎን እንደሚጠየቁ የሚታወቁት አቶ አብዲ አሌ መተማመኛቸው እየፈራረሰ መሆኑን የውስጥ ምንጮች ተናግረዋል።
በአቶ ጌታቸው አሰፋ ጥርስ የተነከሰባቸው እና በምስራቅ ኢትዮጵያ ወያኔ የሚፈጽመውን ወንጀል በገንዘብ ተደልለው ሰነዶችን ሸጠዋል ከፌዴራሉ ባለስልታናት ጋር የሚያደርጉትን የስልክ ልውውጥ ቀድተው ለምእራባውያን ዲፕሎማቶች አሳልፈው ሰጥተዋል በማለት በደህንነት ቢሮው የሚወነጀሉት አቶ አብዲ ከሶስት ቀን በፊት የሶማሊ ሕዝብ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ጅጅጋ ላይ ባደረገው ስብሰባ በፓርቲው ውስጥ አዲስ የለውጥ ተሃድሶ እንዲደረግ ሰባት ሰዎችን በመምረጥ የክልሉ ርእሰ መስተዳደር የሆኑትን አቶ አብዲ አሌን ከማእከላዊ ኮሚቴ እና ከስራ አስፈጻሚ አባልነት እንዳስወገዳቸው ታውቋል።በአሁን ወቅት አዲስ አበባ ያሉት አቶ አብዲ የተለያዩ ባለስልጣናትን እና ወታደራዊ መክንኖችን ወደ ሃይለማርያም እና ጌታቸው አሰፋ በመላክ እንዲያስተካክሉላቸው እየተማጸኑ እንደሆነ መረጃዎች ጠቁመዋል

No comments:

Post a Comment

wanted officials