የመኢአድ አመራር መንገድ ላይ ሞቶ ተገኘ ።#Ethiopia #AEUP #UDJ #EPRDF
በዚህ አመት ከአዲስ አበባ ብቻ ሞተው የተገኙ አመራሮች ሁለት ሆነዋል።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
በኮልፌ ክፍለከተማ የመኢአድ አመራር እና ይፋይናንስ ጉዳዮች ሃላፊ የነበረው አቶ ዳኜ አለሙ በዛሬው እለት ከመንገድ ላይ ሞቶ መገኘቱን እና ሬሳው ምንሊክ ሆስፒታል ውስጥ እንዳለ የድርጅቱ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል።
ነዋሪነቱ በዘነበ ወርቅ አከባቢ የሆነው አቶ ዳኜ ከመንገድ ላይ ሞቶ የተገኘ መሆኑን እና ዳግማዊ ምንሊክ ሬሳው እንዳለ የተነገረው መኢአድ የድርጅቱን አመራሮች ወደ ሆስፒታሉ ቢልክም የምርመራ ውጤቱን ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ለነገ ጠዋት በመቅጠር አመራሮቹን አሰናብተዋል።
በዚህ አመት ብቻ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ከአዲስ አበባ አመራሮቹ ውስጥ የአቃቂ ክፍለ ከተማ አመራር የነበሩት እንዲሁ ሞተው የተገኙ ሲሆን የምርመራ ውጤታቸውን ለማግኘት ብዙ እንደተለፋ ይታወሳል። እንዲሁም በተለያዩ ክፍለሃገራት ያሉ የመኢአድ መዋቅሮችን ለማፈራርረ ክመግደል ጀምሮ እስር ድብደባ እና ማግለል እየተፈጸመባቸው ነው።ወያኔ መኢአድን አዳክሞ ጠንካራ የተባለ መዋቅሩን ለማፈራረስ ከምርጫው በፊት ብዙ እየሰራ መሆንን ይታወቃል።

No comments:
Post a Comment