Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, August 30, 2014

የወረታ ግብርና ኮሌጅ ተማሪዎች ግቢያቸውን ጥለው ወጡ

የወረታ ግብርና ኮሌጅ ተማሪዎች ግቢያቸውን ጥለው ወጡ

ነሃሴ ፳፫(ሃያሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-
በኮሌጁ የሚማሩ ከ1 ሺ በላይ የክረምት ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው ለመውጣት የተገደዱት
የትምህርቱ ጊዜ በመራዘሙ ነው። የኮሌጁ አስተዳደር ቀደም ብሎ ለ4 አመት ይሰጥ የነበረው ትምህርት ወደ 6 አመት እንደሚራዘም የገለጸላቸው ሲሆን፣
ተማሪዎቹ የኮሌጁን ውሳኔ ተቃውመዋል። “ብትፈልጉ ተማሩ ወይም ግቢውን ልቀቁ መባላቸውን” የገለጹት ተማሪዎች፣ በዚህም የተነሳ ግቢውን ለቀው ወደ
መጡበት መመለሳቸውና ኮሌጁም መዘጋቱን ገልጸዋል። ተማሪዎች የትምህርት ጊዜው የተራዘመው ከመጪው ምርጫ ጋር ተያይዞ ነው የሚል መልስ
እንደተሰጣቸው ቢገልጹም፣ ኮሌጁ ግን በይፋ የሰጠው ምክንያት የለም።

No comments:

Post a Comment

wanted officials