Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, August 27, 2014

ዘመናዊ የባሪያ ንግድ በቃፈታ ሁመራ

ዘመናዊ የባሪያ ንግድ በቃፈታ ሁመራ
የዛሬን አያደርገውና ሁመራ ጎንደር ውስጥ አሉ ከሚባሉ ለም መሬቶች የመጀመሪያውን ስፍራ ትይዛለች:: ሁመራ በአሁኑ ስአት በኢትዮፒያ ውስጥ ቁጥር አንድ ሰሊጥ የሚመረትባት በታ ናት:: በሁመራ ውስጥ ከሚሰሩ ባለሀብቶች የህውሀቱ EFFORT የአንበሳውን ድርሻ ቢወስድም ሌሎቹ ጥቃቅን ባለሀበቶች ብዛታቸው እንደ አሸን ነው:: እንዴው ከ EFFORT ጋ ሲወዳደሩ ጥቃቅን ይሁኑ እንጅ ነገርየው ሌላ ነው:: እያንዳንዱ ጥቃቅን ባለ ሀብት በትንሹ በአመት ከወጭ ገቢ 30 ሚሊዮን የኢትዮፒያ ብር ያገኛል::
ይህን ፁህፍ እንድጽፍ ያደረገኝ የእነሱን ሀብት ለማሳወቅ አይደለም:: ነገሩ ወዲህ ነው #### እንደነገርኩአቹህ EFFORT የተሰጠው መሬት በሄክታር ሲሰላ ከ 15 ሺ በላይ ነው:: ከዚህ ውስጥ ከ ግማሽ በላይ የሚሆነው አሁን ጎንደር ተብሎ ከተከለለው ውስጥ ይገኛል:: እዚህ ላይ ሊነሳ የሚገባው ጥያቄ አሁን EFFORT ከያዘው ቦታ ወደ ሰሜናዊ ክፍል 8 ሺ ሄክታር የሚሆን ብዙ ክፍት ቦታ እያለ ለምን ጎንደር መሬት ውስጥ ገብቶ እንዲያለማ ተደረገ?
ሌላው ነገር በቃፈታ ሁመራ እርሻ ውስጥ የሚሳተፉት የቀን ሰራተኞች ብዛት ነው:: 1.4 ሚሊዮን የቀን ሰራተኛ ከ ጎንደርና ከ ጎጃም ብቻ ከወርሀ ሰኔ እስከ ጥቅምት ባለው ግዜ ውስጥ በኩልበት ስራ ይሳተፋል:: በአማካይ በወር ውስጥ 500, 000 የጉልበት ሰራተኞች ይስተናገዳሉ:: በዚህ ሁናቴ ውስጥ የሚከተሉትን እውነታዎች ይዘን ብቅ አልን!!!!!!!!!!
1 EFFORT ለሰራተኞች የሚያቀርበው ምግብ ወደህአክር ከሚባል የሰብል አይነት የተዘጋጀ ዱቄት ሲሆን ትል ከማፈራቱ የተነሳ ትሎች ከዱቄቱ የሚለዩት በወንፊት ነው::
2 ካለው አስቸጋሪ የአየር ንብረት, ጊንጥ, እና የውባ በሽታ ተጋላጭነት የተነሳ ቢያነስ በቀን 5 ሰው ይሞታል
3 ለጉልበት ሰራተኞች በቀን የሚከፈላቸው ገንዘብ 19 ብር ሲሆን EFFORT ከሚያገኘው ትርፍ ለነዚህ ሰራተኛ የሚያውለው ከአንድ ሚሊዮን 10 ብር ብቻ ነው::
4 አንድም የትግራይ ተወላጅ በጉልበት ሰራተኝነት ተቀጥሮ ወደ ቦታው እንዳይሄድ ተወስኖል
5 መቶ በመቶ የጉለበት ሰራተኞች ከ ጎጃምና ጎንደር እንዲሁም ከፊል ወሎ የመጡ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 55 % የሚሆኑት ደራ ወረዳ ከሚባል ደቡቡ ጎንደር ዞን የመጡ ናቸው::
የሚገርመው በኢትዮፒያ ውስጥ ቀጥር አንድ ትልቅ ድርጅት ባልተማሩ ዜጎች ላይ ይህን የመሰለ ግፍ ሲፈጽም አቤት ባይ ወገን መጥፋቱ ያስተዛዝባል::
የተከበራቸሀ ወዳጆቸ ይህ አስተሳሰብ በምንም መለኩ ፖለቲካዊ ይዘት እስከሌለው ድረስ አማራ ክልል ውስጥ የምትገኙ ማናቹህም ሙህራኖች ለክልሉ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ኩዳይ ጽቤት ለማመልከት እንዘጋጅ ስል በትህትና እጠይቃለሁ:: ለክልሉም ብቻ ሳይሆን ለ ፌድራል ማሀበራዊ ጉዳዮች ተጠሪ ለአቶ ደመቀ መኮነን ግልባጭ ይሆንለት ዘንድ ደብዳቤ ማረቀቅ ይኖርብናል::
በመጨረሻም ጉዳዩ ያገባናል የምትሉ ማናቹህም በውጭም በውስጥም የምትኖሩ ኢትዮፒያዊያን ከአሁኑ ስአት ጀምራቹህ አብሮነታቹህን ብትገልጹልኝ ነገሩ ውጤት ይኖረዋል ብየ ስለማስብ ከፊት ለመሰለፍ ሙሉ ፍቃዴን ስግልጽላቹህ በደስታ ነው:

No comments:

Post a Comment

wanted officials