Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, August 27, 2014

በሰልጣኝ ተማሪዎች ላይ ቁጥጥሩ ጠብቋል • ማታ ማታ ተማሪዎች ይቆጠራሉ

በሰልጣኝ ተማሪዎች ላይ ቁጥጥሩ ጠብቋል
• ማታ ማታ ተማሪዎች ይቆጠራሉ
• ‹‹ከማን ጋር እንደምትገናኙ እናውቃለን›
• ‹‹በፌስ ቡክ ውዥንብር ትነዛላችሁ››
በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች ስልጠና እየወሰዱ የሚገኙ ተማሪዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር መጀመሩን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ ነሃሴ 17 ከሰዓት ጀምሮ እሁድንም በስልጠና እንዲያሳልፉ የተጠየቁት ተማሪዎች ‹‹ስልጠናው የዕረፍ ቀናችን ሊሻማብን አይገባም›› በሚል ከማሰልጠኛ ጣቢያው ወጥተው ወደየቤታቸው እንደሄዱ የታወቀ ቢሆንም ሰኞ ነሀሴ 19 ጀምሮ በየ ስልጠና ጣቢያዎቹ ጥብቅ ቁጥጥር መጀመሩን ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡
ለቁጥጥሩ መጠናከር ተማሪዎቹ ቅዳሜና እሁድ አንሰለጥንም በማለታቸው እንደሆነ የገለጹት ምንጮቹ ከዚህም በተጨማሪ ከማሰልጠኛ ጣቢያዎቹ ውጭ ለሚገኘው ህዝብ በተለይም ሚዲያዎች መረጃ እየሰጣችሁ ነው የሚል ወቀሳ እንደቀረበባቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ማታ ማታ ከግቢው እንዳይወጡ መከልከሉን፣ ለዚህም ሲባል ስም እንዲጠራና ተማሪ እንዲቆጠር በመደረጉ ያሉበት ሁኔታ ማሰልጠኛ ሳይሆን እስር ቤት እንደሚመስል ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ ጥያቄ የሚጠይቁና በስልጠና ሰነዱ ላይ የሰፈሩት ጉዳዮች ትክክል እንዳልሆኑ የሚተቹ ተማሪዎች እየተጠሩ ማስፈራሪያ እንደሚደርስባቸው፣ ሌሎች ሰልጣኞችም ‹‹በፌስ ቡክ ውዥንብር ትነዛላችሁ፣ ከግቢ ወጥታችሁ ከማን ጋር እንደምትገናኙ እናውቃለን›› እና ሌሎችም ዛቻና ማስፈራሪያዎች እንደሚደርስባቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ምንጭ ነገረ ኢትዮጵያ

No comments:

Post a Comment

wanted officials