Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, August 12, 2014

የሎሚ መጽሔት ባለቤት የክስ ቻርጅ ደረሰው

የሎሚ መጽሔት ባለቤት የክስ ቻርጅ ደረሰው
በቅርቡ ፍትህ ሚኒስትር አምስት መጽሔቶችንና አንድ ጋዜጣን መክሰሱን በመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ማስነገሩ አይዘነጋም፡፡እንደተከሰሱ ከተነገረባቸው የህትመት ውጤቶች መካከል በዛሬው ዕለት ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ እንዲቀርብ ተነግሮት የነበረው የሎሚ መጽሔት ባለቤት ጋዜጠኛ ግዛው ታዬ ማዕከላዊ በማምራት የክሱን ቻርጅ ተቀብሎ ተመልሷል፡፡
ክሱ የደረሰው የሎሚ መጽሔት ባለቤት የፊታችን አርብ ልደታ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ የተነገረው መሆኑም ታውቋል፡፡እንደሎሚ ሁሉ ፋክት፣ዕንቁ፣ጃኖ ፣አዲስ ጉዳይ እና አፍሮ ታይምስ ጋዜጦች ክስ የተመሰረተባቸው ቢሆንም ማዕከላዊ እንዲቀርብ የተነገረውና ክሱን የወሰደው ግን የሎሚ መጽሔት ባለቤት ብቻ ነው፡፡የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ባለቤትና አዘጋጆች መሰደዳቸው አይዘነጋም፡፡
LikeLike ·  · 

No comments:

Post a Comment

wanted officials