Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, August 6, 2014

እንዋሃዳለን ያሉ ፓርቲዎች እና ምርጫ ቦርድ እንዲሁም የውስጥ ሃይሎች እየተጎሻሸሙ ነው።


"የማይበርድ የመንገድ ላይ አመጽ እጠራለሁ ።" መኢአድ - ውህደቱ አሁንም ተራዝሟል።
መኢአድ በምርጫ ቦርድ ላይ ጠንከር ያለ የተቃውሞ ጋዜጣዊ መግለጫ እና ህዝባዊ ጥሪ ሊሰጥ ነው።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ከፍተኛ ድርጅታዊ መዋቅር እንዳለው የሚታወቀው መኢአድ የጎዳና ላይ አመጽ እንደሚጠራ ምርጫ ቦርድን እና የወያኔ መንግስትን አስጠንቅቋል።በቅርቡ እንዋሃዳለን ያሉት አንድነት እና መኢአድ በውስጣቸው ያለው የአባላት መጎሳሰም የገንዘብ ችግር እና ውህደታቸውን ለማደናቀፍ የሚጥሩ ውስጣዊ ወገኖች እንደተጠበቁ ሆነው ክምርጫ ቦርድ ጋር አዲስ አተካራ መግጠማቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ ።
በመኢአድ እና በአንድነት በኩል አሉ የሚባለው እና በውህደቱ ላይ ተቃውሞ ያላቸው ሃይሎች ወያኔ በአንድነት በኩል አድርጎ መኢአድን ሊውጠው ነው በሚል መነሾ ውህደቱን የሚቃወሙ ሲሆን እንደ ኢንጂነር ግዛቸው እና ዘረቀ ረዲ የመሳሰሉት የወያኔ ደሞዝተኞች የተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ ለማልፈስፈስ ከወያኔ ጋር ይሰራሉ በማለት ውህደቱ አንፈልግም የሚሉ ወገኖች ይናገራሉ።
የማይበርድ የጎዳና አመጽ እንደሚጠራ የሚናገረው መኢአድ ምርጫ ቦርድን ውህደቱ ለማደናቀፍ ደፋ ቀና ይላል ሲል ይወነጅላል። ባለፈው ቀናት መግለጫ የሰጡት እና እንዋሃዳለን ያሉት መኢአድ እና አንድነት በገንዘብ ችግር ምክንያት ውህደቱ እንደዘገየ መናገራቸው የሚታወስ ነው።
ምርጫ ቦርድ እና ወያኔ ውህደቱን ለማደናቀፍ የሚያደርጉትን ሴራ ክላቆሙ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ ላይ በመሆን እንዲንቀሳቀስና የምርጫ ቦርድንም ሆነ የኢትዮጵያን መንግሥት በሰላማዊ መንገድ እንዲቃወምና ለትግልም እንዲነሳ ሰላማዊ ሰልፍን፣ የመንገድ ላይ አመፅን እና የመሳሰሉትን እርምጃዎች ሁሉ እንዲወስድ እናስተባብራለን ያለው መኢአድ በነገው እለት የተቃውሞ መግለጫ እና የአመጻ ሕዝባዊ ጥሪ እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል

No comments:

Post a Comment

wanted officials