መንግስት በማህበራዊ ገፆች ያሰማራቸውን ሰልጣኞች ና የሙስሊሙን ትግል አስመልክቶ ስብሰባ አካሄደ
''ድምጸችን ይሰማን ተቀባይነት ለማሳጣት አሁንም ስራዎችን መስራት አለብን'' የደህንነት ሹም
ትላንት የተካሄደው ቦርድ ምስረታ መረጃው በመውጣቱ የመንግስት ሃላፊዎችን አበሳጭቷል
የአዲካ ባለቤት በድረገጽ ለሚሰማሩት የኮምፒተር ስፖንሰር ሆነ
ቢቢኤን፡-ረቡእ ነሃሴ 21/2006
''ድምጸችን ይሰማን ተቀባይነት ለማሳጣት አሁንም ስራዎችን መስራት አለብን'' የደህንነት ሹም
ትላንት የተካሄደው ቦርድ ምስረታ መረጃው በመውጣቱ የመንግስት ሃላፊዎችን አበሳጭቷል
የአዲካ ባለቤት በድረገጽ ለሚሰማሩት የኮምፒተር ስፖንሰር ሆነ
ቢቢኤን፡-ረቡእ ነሃሴ 21/2006
በዛሬው በሸዋ ጸጋ ህንጻ አሹ ቢሮ እየተባለ በሚጠሩት ቢሮ በዛሬው እለት የደህንነት፤የፖሊስ፤ የመጅሊስ አባላት እንዲሁም ትግሉን ለማኮላሸት የተመለመሉ ወጣቶች ጋር ሰብሰባ ማካሄዳቸው ታወቀ፡፡ ተቃውሞ ለማስቆም ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚያደረገው ይህ ቡድን በዛሬው ስብሰባ ላይ ከማእከላዊ የመጡ ሃላፊዎች እንደነበሩ ታዉቋል፡፡ ከነዚህም መካከል ሰይፈዲን የሚባል እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ አቶ በለጠ የተባሉ የአዲስከተማ ክፍለ ከተማ የደህነነት ሃላፊ ከሁለቱ ጋር በመሆን ነበር ስብሰባውን የመሩት
የማእከላዊ ሃላፊዎችም በትላንትናው እለት መጅሊሶች ቦርድ ምስረታ ብለው የጠሩት ጉባኤ ለህዝቡ መረጃው በመውጣቱ መበሳጨታቸው የታወቀ ሲሆን መጅሊስ ያዘጋጀውን ሽልማት አንቀበልም ባሉት ተማሪዎች ላይ መዛታቸው ታዉቋል፡፡ መንግስትን መጅሊስ ከዚህ የቦርድ ምስረታ ላይ ፖለቲካዊ ትርፍ ለማግኘት ፈልገው ያደረጉት እንደሆን በዛሬው ስብሰባ ላይ ተንጸባርቋል ተብሏል፡፡ የአወልያ ተማሪዎችንም ከኢህአዴግ ጫማ ስር እንዲሁኑ ማድረግ አለብን ብለው ሲዝቱም ተደምጠዋል፡፡
በሌላ በኩል በስብሰባው ላይ የተነሳው ሃሳብ መንግስት ለዩንቨርስቲ ተማሪወች ስልጠና እንደሰጠው ሁሉ በየአካባቢው ላሉ ወጣቶችም ስልጠና እንዲሰጥ መንግስት ደብተር ነጻ ይሰጣል ተማሪ እያላችሁ ቀስቅሱ ተብለዋል ዛሬ የተሰበሰቡት ወጣቶች፡፡
በዛሬው ስልጠና ላይ እስከ ዛሬ ለነበሩት 400 ወጣቶች በተጨማሪ ከስልጤ ዞን ከአዘርነት በርበሬ ከተባለ ቦታ አስር ካድሬዎች እንደቀላቀሉ ስልጠና እንደሰጣቸው በማህበራዊ ድረገጽ ስራ እንዲጀምሩ መደረጉ ታዉቋል፡፡ እነዚህም ስራ የጀመሩት ወጣቶች '' ቅድሚያ ለተውሂድ ''በሚል ተውሂድ የሚያስተምሩ በመምሰል ትግሉን የማጣጣል ስራ እንዲሰሩ ለዚህም ኡስታዝ እንደሚመደብላቸው በዛሬው ስብሰባ ላይ ተነግሯቸዋል፡፡ እስከዛሬ ድረስ ሌሎቹ ሙከራዎች ስላልተሳኩ በዚህ መልኩ ተውሂድ የሚያስምሩ ሰዎችን ተመሳሳይ አካውንትና አዳዲስ አካውንት በመክፈት እየተንቃቀሱ መሆናቸውም ታዉቋል፡፡

በሌላ በኩል ድምጻችን ይሰማን እንዳትከተሉ ህዝብ ሊያስጨርስ ነው የሚል መልእክት እንዲያስተላልፉና የድምጻችን ይሰማን ተአማኒነት ለማሳጣት ተግተው እንዲሰሩ ተነግሯቸዋል፡፡ መንግስት ኮሚቴውን ይፈታ ነበር እነሱ እንዳይፈቱ ያደረገው ድምጻችን ይሰማ ነው ትግሉ ባለመቆሙ ነው የሚል ሃሳብ በህዝቡ ውስጥ አሰራጩ የሚል ትእዛዝም ተሰጥቷቸዋል፡፡ በድረገጽ ለተሰማሩትም አዲስ ለተመለመሉት የአዲካ አስጎብኝ ድርጅት ባለቤት አቶ አዋድ ሙሃመድ ለወጣቶቹ ኮምፒተሮቹን በመግዛት ስፖንሰር መሆኑም ታዉቋል፡፡
ሰልጣኞቹ ስራቸውን በአግባቡ ለመስራት የሚያግዳቸው ነገር ምን እንደሆነ የተጠየቁ ሲሆን መንግስት እስከ መቼ ህዝብ ጋር ይጣላል የሚል አስተያየት በድፍረት የጠየቁ ሲሆን ህዝብና መንግስት አልጣላም ከጥቂት ዉህብያዎች ጋር ነው ሲሉ ከማእከላዊ የመጡት ግለሰብ የመለሱ ሲሆን መንግስት ሁሉም መሳሪያ ስላለው ከመንግስት ጋር መጣላት ከባድ ነው በማለት ለማስፈራራት ሞክረዋል፡፡

ሌላኛው ወጣት በመነሳት ኮሚቴዎቹ ነገ ይፈታሉ ህዝቡ ሙስሊሙም ከነሱ ጋር መቀጠሉ የማይቀር ነው የሚል አስተያየት የሰጠ ሲሆን ሰብሰባዎቹም ኮሚቴው መፈታቱን በምን አወቃችሁ ገና ከፈለግን ካሁን በሁላ ሰባትና ስምንት አመት እናሻቸዋለን፡፡ ከፈለግን በአንድ ቀን እንፈርድባቸዋለን፡፡ ፍርድ ቤቱም በኢህአዴግ እጅ ነው ኢህአዴግ ይህን ስልጣን የያዘው ከፍተኛ መስዋእትነት ከፍሎ ነው ያመጣው ራሱ እንደፈለገ ማድረግ ይችላል የሚል አስገራሚ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ኮሚቴዎቹን ብናሰርም አሁንም ተቃውሞው እየጨመረንጅ እየቀነሰ አልመጣም ሰልችቶት እንዲተው አሁንም በኮሚቴዎቹ ላይ የምናደረገውን በደልና ጭቆና እንቀጥላለን ሲሉም ተደምጠዋል፡፡ ኮሚቴዎቹን በግድ ጫና አድረገን ካስፈረምን በሁላ ነው የምንተዋቸው፡፡ ከተፈቱ በሁላ መልሰው ከቀሰቀሱ ደግመን እናስራቸዋለን፤ " ብለው መናገራቸውን የቢቢኤን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ''ኮሚቴዎቹ መቼ እንደሚፈቱ አይታቅም መንግስት ህዝቡ ኮሚቴዎቹን እንዲረሳ ስራዎች ይሰራል፡፡ የፍርድ ሂደቱንም ያጓትታል ሲሉ ተናገረዋል፡፡
ለአራት መቶዎቹ ምልምል ወጣቶችም ሁለት ሃላፊዎች ተመድቦላቸዋል፡፡ መንግስት እንደፈለገ ማድረግ ይችላል ያሉት አቶ ሰይፈዲን የአንዋር መስጅድን በማንሳት በቂ ሃይል አለን ሲሉ ፎክረዋል፡፡ የአንዋር መስጅድን ሱቆች የሚቃወሙት ዉህብያዎች ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
መንግስት ህዝበ ሙስሊሙ እያደረገ ያለው ሰላማዊ ትግል ራስ ምታት እንደሆነበት በዛሬው ስብሰባ ላይ የተንጻባረቀ ሲሆን በዋናነት ትግሉን ለማዳከም የሚያደረገውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ መቀጠሉን ነው ለመረዳት የተቻለው፡፡ ህዝበ ሙስሊሙን ድምጻችን ይሰማ በሚያወጣው መርሃግብር በመደራጀት ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል እየገለጸ ይገኛል፡፡ ቢቢኤን ተጨማሪ መረጃዎችን እየተከታተለ እንደሚያቀርብ ለመግለጽ እንዳለን

No comments:
Post a Comment