አቶ አባይ ፀሐዬ ቤተክርስቲያን የግል ፕሬሶች ላይ እየተከታተለች ክስ እንድታቀርብ መመሪያ መስጠታቸው ተጋለጠ
ከሁለት ወራት በፊት አቶ አባይ ጸሐዬ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ በፕሬሶች ላይ እየተከታተለች ክስ እንድታቀርብ መመሪያ ማስተላለፋቸውን የዘ-ሐበሻ የቤተ-ክህነት ምንጮች አጋለጡ። እንደምንጮቹ ገለጻ ቤተክርስቲያኗ ይህን መመሪያ ከተቀበለች በኋላ የተለያዩ ክሶችን በፕሬሶች ላይ አዘጋጅታ የነበረ ሲሆን ከነዚህም መካከል በሎሚ መጽሔት ላይ የታሰበው ክስ ጋዜጠኞቹ በመሰደዳቸው የተነሳ ክሱ ሊቀር ችሏል።
የቤተክህነት ምንጮቻችን ዜናውን ሲያደሱን “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በተክርስቲያን በሎሚ መጽሄት ላይ ልትመሰርት የነበረውን ክስ ሰረዛዋለች።” ካሉ በኋላ “ከትላንትና በስቲያ በንብረኡድ ኤሊያስ አብርሃ ለሕግ ክፍል በደረሰ የስልክ ትእዛዝ መሰረት የሎሚ መጽሄት ባልደረቦች ስለተሰደዱ እና ጹሁፉን ጻፈ የተባለው ግለሰብም የሚኖረው በአውሮፓ ሞናኮ መሆኑን የመንግስት አካላት ባደረስን መረጃ ክሱ ዝግጅቱ ቢጠናቀቅም እንዲሰረዝ በስልክ በንበሩድ ኤሊያስ ተነግሮናል።” ብለዋል። እነዚሁ ምንጮች እንዳሉት “ክሱ እንዲመሰረት የተፈለገው “ዜጎችን ያልታደጉ ቆባቸውን ያውልቁ ” በሚል ርእስ ስር የተጻፈው የሃይማኖት መሪዎችን መብት ይጋፋል እንዲሁም የእምነት ነጻነትን በማደፍረስ ሕዝቡ በሃይማኖት መሪዎች ላይ ታማኝነት እንዳይኖር ያደርጋል ..ወዘተ በሚሉ ተያያዥነት ካላቸው ጉዳዮች ጋር ሰበብ እና አቃቂር በመፍጠር መጽሄቱን እና ጸሃፊውን ለመክሰስ ታስቦ ለሕግ ክፍሉ ተጠንቶ ክሱ እንዲዘጋጅ ትእዛዝ ተላልፎልን የነበረ ቢሆንም ከመንግስት በተገኘ በሚል መረጃ መሰረት በንብረኡድ ኤሊያስ አብርሃ ተሰርዟል።” ብለዋል።
ምንጮቹ ጨምረውም ከሁለት ወራት በፊት በቤተክርስቲያኗ ጉዳይ ሁሌም ጣልቃ የሚገቡትና በአንድ ወቅትም ቤተክርስቲያን አንድ ልትሆን በተቃረበችበት ወቅት “ውጭ ያለውን ሲኖዶስ በቅርብ ቀን በአሸባሪነት እንከሳለን፤ ስደተኛው ሲኖዶስ ሀገር ቤት የሚመጣው መንግስት ለመገልበጥ ነው” በሚል አባቶችን ማስፈራራታቸው በሚዲያ የተለቀቀባቸው አቶ አባይ ጸሃዬ ቤተክርስቲያኗ በፕሬሶች ላይ እየተከታተለች ክስ እንድታቀርብ የሰጡትን መመሪያ ተከትሎ በሌሎች ፕሬሶች ላይም ክስ ለመመስረት ዝግጁ ናቸው።
No comments:
Post a Comment