Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, January 31, 2015

የአርበኞች ግንቦት7 ሴት አባላት የትግል ጥሪ አቀረቡ

የአርበኞች ግንቦት7 ሴት አባላት የትግል ጥሪ አቀረቡ
ጥር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ገዢውን ፓርቲ በሃይል ለማንበርከክ በትግል ላይ የሚገኙ የአርበኞች ግንቦት7 ሴት አባላት ጥሪያቸውን ያቀረቡት የመስክ ጉብኝት ለማድረግ ለተንቀሳቀሱት የኢሳት ጋዜጠኞች ነው።
ሴት አርበኞቹ በአገሪቱ ውስጥ እየተካሄደ ያለው አፈናና የመብት ጥሰት በስልጣን ላይ ያለውን የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት በሃይል ለማንበርከክ ነፍጥ እንዲያነሱ እንዳስገደዳቸው ገልጸዋል።
ለሁለት ወራት ያክል ከኢህአዴግ ታጣቂ የሰራዊት አባላት ጋር ጠንካራ ፍልሚያ ስታደርግ ቆይታ በመጨረሻ ምንም ችግር ሳያጋጥማት ሌሎች አርበኞችን ለመቀላቀል መቻሉዋን የገለጸችው አርበኛ ሃብታም ታደሰ፣ ወያኔ ደካማ መሆኑን በጫካ ህይወቴ ለማረጋገጥ ችያለሁ ብላለች።
አርበኛ ሃብታም ገዢውን ሃይል ለማንበርከክ በሚደረገው ትግል ሴቶች ትግሉን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርባለች
ሌላዋ አርበኛ ሰላማዊት ትኩ በበኩሏ ሴቶች የግድ በረሃ መውረድ እንደሌለባቸው ገልጻ፣ ለነጻነት ለሚደረገው ትግል ባሉበት ቦታ ሁሉ ሆነው ሊደግፉ፣ ሊታገሉ ይችላሉ ብላለች።
አርበኛ ሰናይት ወርቅነህም እንዲሁ በኢትዮጵያ ውስት የሚታየው ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መሄዱን ገልጻ በውጭና በአገር ውስጥ የሚኖሩ ሴቶች ትግሉን ተቀላቅለው ታሪክ የጣለባቸውን ሃላፊነት ይወጡ ስትል መልክት አስተላልፋለች።
የኢሳት የጋዜጠኞች ቡድን ተዘዋውሮ ለመታዘብ እንደቻለው በርካታ ሴቶች ገዢውን ሃይል በመሳሪያ ለማንበርከክ ወስነው እየታገሉ ነው። አርበኞች ግንባርና ግንቦት7 ውህደት ከፈጸሙ በሁዋላ ከሌሎች ሃይሎች ጋር ትብብር እና ጥምረት በመፍጠር ገዢውን ፓርቲ በሃይል ለማንበርከክ እንደሚሰሩ መግለጻቸው መዘገቡ ይታወሳል።
በሌላ በኩል ደግሞ የቀድሞ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አርበኞች ማህበር በአርበኞች ግንባርና በግንቦት7 መካከል የተፈጸመውን ውህደት በመደገፍ መግለጫ አውጥቷል። ማህበሩ በመግለጫው ኢትዮጵያን ከገባችበት ውድቀት ነጻ ለማውጣት የተናጠል ትግል እንደማያዋጣ በመግለፅ ድርጅቶቹ ያደረጉት ውህደት አስደሳች ነው ብሎአል።

የአንድነትና የመኢአድ ቢሮ በፖሊስ ተከቧል

UDJ office

የአንድነት ለፍትሕና ዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) ቢሮ በፖሊስና በደህንነት መከበቡን አቶ አስራት አብርሃ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ቢሮው በደህንነትና በፖሊስ በመከበቡ አባላት መውጣትና መግባት እንደማይችሉ የገለጹት አቶ አስራት ‹‹ውጭ ያለነው ወደ ውስጥ እንዳንገባ ተከልክለናል፡፡ ውስጥ ያሉትም መውጣት አይችሉም፡፡›› ብለዋል፡፡ የአንድነት አመራሮችና አባላት እንዳይወጡና እንዳይገቡ የከለከሉት ደህንነትና ፖሊሶች የከበባውን ምክንያት እንደማይናገሩ አቶ አስራት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ቢሮው በፖሊስና በደህንነቶች በመከበቡ አመራሮችና አባላቱ ወደ ውስጥ መግባትም ሆነ ወደ ውጭ መውጣት እንደማይችሉ ተግልጾአል



ምርጫ ቦርድ ዕውቅና የነሣቸው የፓርቲው አመራር አባላትም ወደ ፅህፈት ቤቱ እንዳይገቡ መደረጋቸውን ይገልፃሉ። ፖሊስ ከፅህፈት ቤቱ ሲያግዳቸው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዳላሳየም ተናግረዋል። የየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ እርምጃውን የወሰደበትን ምክንያት ተጠይቆ መልስ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆነም። የአንድነት ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና እንደራሴ አቶ ግርማ ሰይፉ ለቪኦኤ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/38622#sthash.uABK7UlZ.dpuf


- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/38595#sthash.TBhfFxdI.dpuf

Internet censorship: The worst offenders – By Barclay Ballard

n the UK, policies that restrict the flow of information across the Internet are generally met with outcry and consternation for contradicting our fundamental right of free speech, but for many individuals widespread Internet censorship is the norm.
Ethiopians-using-the-internet-300x195
However, online censorship is much more pervasive than one might initially think, with Ethiopia, Russia and even the UK currently listed as Enemies of the Internet by the French non-governmental group Reporters without Borders (RWB).
The most high-profile example remains of course China, which has monitored and regulated online use almost since the Internet’s introduction in the country back in 1994. The Golden Shield Project, often referred to as the Great Firewall of China, was officially begun in 1998 and attempts to restrict the distribution of what it calls “sensitive” information.
Websites referring to Tibetan or Taiwan independence, the Tiananmen Square protests or freedom of speech, amongst other topics are all outlawed. Well-known Western sites such as Twitter, Facebook and YouTube are also banned. Despite the rise of domestic social media platforms like Sina Weibo and attempts to circumvent censorship via VPNs and proxy servers, China remains one of the most stringently censored countries in the world.
Another country influence by a Communist regime, North Korea’s general level of secrecy may make its censorship programme less well-known, but in many ways it is even more authoritarian. All media is controlled by the government and estimations suggest that just four per cent of the population have Internet access.
Aside from high-ranking government officials, most citizens must use the national intranet Kwangmyong. Unsurprisingly, Kwangmyong is a heavily watered-down version of the World Wide Web, containing between 1,000 and 5,500 websites compared to a figure of more a billion than for the global Internet. As a result, the head of the Internet desk at RWB Julian Pain described North Korea as “by far the worst Internet black hole”.
Aside from issues of political sensitivity, the Internet’s free exchange of ideas can also place it at odds with countries that have a more strictly religious society.
In Saudi Arabia, for example, all Internet traffic first goes through a government run filter which, according to the country’s Internet Services Unit , blocks all material of an “offensive or harmful nature to the society, and which violate the tenants of the Islamic religion or societal norms”. In reality this often means any sites of a pornographic nature or which are supportive of LGBT rights, any found to be promoting Shia ideology, and any that are critical of the national government.
Interestingly, the government encourages the Saudi people to be complicit in the censorship programme by asking them to actively report immoral pages to the government’s website. Other Middle Eastern nations known to implement at least some form of online censorship include Syria, Iran, Bahrain and the United Arab Emirates.
While large scale censorship programmes may be restricted to a few high-profile countries, many nations have blocked or threatened to block popular websites in isolation. Social media is often targeted due to the way it encourages discussion and the transfer of information. In the past year for example, Pakistan, Iran, Eritrea, Turkey and Vietnam, alongside China and North Korea, have all blocked Twitter, Facebook or YouTube.
However, while Western nations generally allow their citizens to freely browse social networks and the majority of other sites, it is easy to forget that many of these countries have experienced some form of online censorship in recent times. For example, both the United Kingdom and the US were listed as “Enemies of the Internet” by RWB in 2014, with the former dubbed the “world champion of surveillance”.
The UK’s use of a web filter known as Cleanfeed to block child pornography is surely beyond criticism, but over the last couple of years the UK government has taken steps to increase its control over the World Wide Web. Since 2011, UK ISPs have been ordered to block websites that infringe upon copyright laws such as file sharing site the Pirate Bay.
However, it is Prime Minister David Cameron’s controversial decision to enforce a filter on pornography as well as abusive material such as violent and suicide-related content, that has drawn the most criticism. For many, censoring what content an individual can privately access is a slippery slope to more proactive Internet control.
Worryingly, Cameron looks set to continue on this path, telling the Australian parliament in November that “we must not allow the Internet to be an ungoverned space”, if the threat of religious extremism is to be thwarted. With British citizens continuing to join the extremist group Islamic State in Iraq, a government-backed decision to place further limits on this kind of narrative is not entirely unfeasible.
It is clear that Internet censorship is not an issue restricted to China, the Middle East or even countries that unashamedly place limits upon freedom of speech. When Wikipedia founder Jimmy Wales questioned whether the West was losing its “moral leadership” regarding online censorship, he hit upon a very pertinent point. It is the responsibility of every nation to appraise its barriers to free speech so that, not only the safety, but also the freedom of its citizens is ensured.
Published under license from ITProPortal.com, a Net Communities Ltd Publication. All rights reserved.
- See more at: http://www.zehabesha.com/internet-censorship-worst-offenders-barclay-ballard/#sthash.oAskejJA.dpuf

Wednesday, January 28, 2015

የዞን9 የጦማርያን እና ጋዜጠኞች ችሎት ክሱ ተሻሻሏል ሲል "ፍርድ ቤቱ" ወሰነ


ለስድስት ወራት የክሱን ፎርማት ይዘትና ህጋዊ መሰረት ሲያጠና የከረመው "ፍርድ ቤት" ክሱ ተሻሽሏል የሚል ብያኔውን ዛሬ በተደረገው 16ተኛ የዞን9 የጦማርያን እና ጋዜጠኞች ችሎት ላይ በንባብ አሰምቷል ፡፡
አንዲሻሻሉ ከታዘዙት አራት ነጥቦች መካከል ሶስቱ መሻሻላቸውን አይቻለሁ ያለው "ፍርድ ቤቱ "
1. ቡድን በሚል የተጠቀሰው ተከሳሾቹ ያቋቋሙት የህቡህ ቡድን አንደሆነ ፍርድ ቤቱ ተረድቷል ቡድኑ ዝርዝር ሁኔታ በማስረጃ መስማት ወቅት ተቀባይነት ሊኖረው ወይም ደግሞ ውድቅ ሊሆን የሚችል ስለሆነ ክሱ ውስጥ መካተት አለበት ሲል ወስኗል ፡፡

2. ስልጠናን አስመልክቶ ‹‹ተከሳሾች ከ2004 ጀምሮ እጃቸው እስከተያዘበት ጊዜ ድረስ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት በግንቦት 7 አመቻችነት ስልጠና መውሰዳቸውን የተሻሻለው ክስ አስፍሯል፡፡ ስለሆነም ጊዜውና በማን የሚለው ስለተጠቀሰ ክሱ መሻሻሉን ፍርድ ቤቱ ተቀብያለው ብሏል፡፡
3. ለሽብር ተግባር ዋለ የተባለውን 48.000 ብር አስመልክቶ ክሱ ውጨ አገር የሚገኙ የቡድኑ አባላት ናቸው በሚል ስለሚያብራራው ተቀባይነት አግኝቷል ያለ ሲሆን ስራ ክፍፍልን አስመልክቶ በቂ ዝርዝር ባለመቀረቡ ከስራ ክፍፍል ፍሬ ነገር ውጪ ያሉት የክሱ ፍሬ ነገሮች ተካተው ተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመስጠት ዝግጁ መሆን አለመሆናቸውን ፍርድ ቤቱ ጠይቋል፡፡
በተከሳሾች ጠበቃ የፍርድ ቤቱ የሶስቱን ፍሬ ነገሮችን መቀበል ያልተጠበቀ መሆኑን ገልጸው ከደንበኞቻቸው ጋር ለመመካከር ጊዜ ጠይቀዋል ፡፡ በዚህም መሰረት ችሎቱ ለከሰአት 8.00 በድጋሚ ተቀጥሮ የጠዋቱ ችሎት ተጠናቋል፡፡
በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ብዙም ያልተገረሙት ተከሳሾች ወንዶቹ የምሳ እረፍታቸውን በልደታ ፍርድ ቤት ውስጥ ሲያሳልፉ፣ ሴቶቹ ወደ ቃሊቲ ተመስደው ተመልሰዋል፡። በጠንካራ መንፈስ ላይ የነበሩት እስረኞች ብይኑ በችሎት ሲሰማ ከፈገግታ እና ሳቅ ባለፈ ምንም አይነት መደናገጥ አልታየባቸውም ፡። በቆይታቸውም እርስ በርሳቸው ሲያወሩ ሲወያዬ እና ወዳጅ ዘመዶችን ሰላም ሲሉ ተስተውለዋል፡፡
በከሰአቱ ችሎት በቂ የመወያያ ግዜ ለማግኘት ስላልተቻለ ጠበቃ አምሃ አጭር ቀጠሮ በመጠየቃቸው ችሎቱ ለሚቀጥለው ማክሰኞ ለጥር 28 ተቀጥሮ ተጠናቋል፡፡
ማስታወሻ
የዞን9 ጦማርያን ፍርድ ቤቱ እድሉን ተጠቅሞ የፍትህ ስርአቱን ነጻነት የሚያረጋግጥበትን ወርቃማ እድል አንዲጠቀም ደጋግመን መጠየቃችን ይታወሳል፡፡ ከማስረጃው 90 በመቶው ጦማራችን ላይ የወጡ ጽሁፎች በመሆናቸው ክሱ ሃሳባቸንን በነጻነት በመግለጻችን ብቻ የተቀናበረ ፓለቲካዊ ክስ መሆኑን ግልጽ ያደርገዋል ፡፡ አሁንም አልረፈደምና ዞን9 ጦማርያንን እና ጋዜጠኞችን በነጻ በማሰናበት የፍትህ ስርአቱ ራሱን እንደቁምነገር የሚያስቆጥርበትን እድል አንዲጠቀም ደግመን እናሳስባለን፡፡ የፍትህ ስርአቱ መስተካከል ከጦማርያኑ እና ጋዜጠኛ ወዳጆቻችን ከታሰሩለት አገራዊ አጀንዳ አንዱ ነውና !

(ሰበር ዜና) አንዳርጋቸው ጽጌ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት መዛወራቸው ተሰማ

andargachew new picture
(ዘ-ሐበሻ) የመን ላይ በሕወሓት አስተዳደር ታግተው ኢትዮጵያ ከገቡ በኋላ እስካሁን የትኛው እስር ቤት ታስረው እንደነበር የማይታወቁት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ቃሊቲ እስር ቤት መዘዋወራቸው ተሰማ::
ምንጮች ለዘ-ሐበሻ እንዳስታወቁት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በቃሊቲ እስር ቤት ቀድሞ ስዬ አብርሃ የታሰሩበት ክፍል ታስረዋል::
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላለፉት 6 ወራት የት እንዳታሰሩ የማይታወቅና የብዙ ሕዝብ ጥያቄ የነበረ ሲሆን ከሳምንታት በፊት ከማይታወቀው እስር ቤት ከባለቤታቸው ጋር ማውራታቸውና ለልጆቻቸውም ያልሆነ ተስፋ እንደማይሰጡ መናገራቸውን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ ይታወሳል::
በተለይም ሰሞኑን የ እንግሊዝ ፓርላማ አባላት ወደ አዲስ አበባ በአንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ለመነጋገር እንደሚሄዱ ከተነገረ በኋላ አቶ አንዳርጋቸው ወደ ቃሊቲ እስር ቤት መዘዋወራቸው አነጋጋሪ ሆኗል:: አቶ አንዳርጋቸው ለሕዝብ ክፍት ሆነው እንዲጠየቁ የሕወሓት አስተዳደር ይፍቀድ አይፍቀድ የታወቀ ነገር የለም::

Source: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=38475 

Ethiopia Bloggers to Enter Pleas in Terrorism Case

Ethiopia Bloggers to Enter Pleas in Terrorism Case


(Bloomberg) — Ethiopian bloggers accused of plotting acts of terrorism will probably enter pleas next week after a court accepted amended charges from the prosecution.Three journalists and six bloggers who have been held for the past five months in Ethiopia
The Federal High Court accepted most of the charges against 10 bloggers and journalists, Ameha Mekonnen, a defense lawyer for the writers, said on Wednesday from Addis Ababa, the capital. The defendants will enter pleas on Feb. 3, he said by phone.
Nine of the accused were detained in April and charged under a 2009 anti-terrorism law that the U.S. and United Nations said criminalizes legitimate dissent. The prosecution has said that the group participated in the planning of a plot with the U.S.-based Ginbot 7, which is classified as a terrorist organization in Ethiopia.
In November, the court rejected earlier charges and asked prosecutors to present more specific and clear accusations.
“They’ve said now it’s sufficiently clear but for us it’s not yet clear at all,” Mekonnen said.

Tuesday, January 27, 2015

በኖርዌይ ኦስሎ እንግሊዝ ኢንባሲ ፊት ለፊት በደማቅ ሁኔታ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

norway 1
norway ethiopian
norway ethiopian
norway ethiopian 3
                             ቀን፡ 01/26/2015
በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ በወጣቶች ክፍል አስተባባሪነት በዛሬው እለት ሰኞ( January 26,2015) በኖርዌ ኦስሎ በእንግሊዝ ኢንባሲ ፊት ለፊት በኖርዌይ የሚኖሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በህብረት ሁነው ከ14፡00 _15፡00 ስዓት ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፉ በደማቅ ሁኔታ አካሄዱ።
የሰልፉ ዋና አላማ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ የነበሩትንና የሰባዊ መብት ተቆርቋሪ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በአረመኔው፣ ሰው በላ፣ ጨቋኙና በአንምባ ገነኑ የወያኔ ፋሺስታዊ ቡድን የአለም አቀፍ የሰባዊ መብትን ህግ በጣሰ መንገድ በሰኔ 2014 ታፍነው እስኳሁንም ድረስ ፍትህ ተነፍገው በእስር ቤት መታሰራቸውን ለመቃወም እንዲሁም የእንግሊዝ መንግስት አርበኛው የነጻነት ታጋዩ አንዳርጋቸው እየተፈጸመበት ያለውን ተፈጥሮአዊና ዲሞክራሲያዊ የመብት ጥሰት ተመልክቶ ከእስር ሊወጣበት የሚችልበትን አፋጣኝ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ ለማሳሰብ ነው።
በተጨማሪም አንዳርጋቸው ከተያዘበት ቀን ጀምሮ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በወያኔ የተፈጸመውን የውንብድና ድርጊት በመቃዎም ለእንግሊዝ መንግሥት በተለያየ መልኩ የአገሩን ዜጋ ህይወት ይታደግ ዘንድ በተደጋጋሚ ለማሳሰብ ቢሞከርም አፋጣኝ እርምጃ አለመወሰዱ ብዙዎችን አስቆጥቷል።
አንዳርጋቸው አገር ወዳድ፣ ሰላም ፈላጊ፣ ነጻነትና ፍትህ ናፋቂ፣ ለህዝብና ለአገር ክብር ተቆርቋሪ፣ ከእራሱ እና ከሚወዳቸው ቤተሰቦቹ ይልቅ ለእናት አገሩ ኢትዮጵያ ጊዜውን፣ እውቀቱንና ህይወቱን የሰዋ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ጀግና መሆኑን በኩራት መስክረዋል። የውጭ ዜጎችም ሳይቀሩ ኢትዮጵያዊ ማንዴላ ብለው ሰይመውታል። ለዲሞክራሲ መከበር ለሚታገል አርበኛ እስርና እንግልት ኮቶ እንደማይገባ በተለይ የእንግሊዝ መንግሥት በትኩረት ሊመክርበት የሚገባ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን እና በወያኔ ላይ ግፊትና ጫና መፍጠር እንዳለበት ሁሉም ተሰላፊዎች ድምጻቸውን ከፍ አድርገው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
እንዲሁም ሰልፈኞቹ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ በታላቅ ድምጽና ስሜት የኖርዌይ ቅዝቃዜና በረዶ ሳይበግራቸው ለኢንባሲው አሰምተዋል። ከአሰሟቸው መፈክሮች መካከል ለአብነት ፣ “Andargachew is a freedom fithter, UK, were is your citizen, Free Andrgachew Tsige, Andargachew is our icon of democracy, where is your action , stop discrimination among citizens, Yes, we are all Andrgachew Tsige, Yes, Andargachew is an Ethiopian Mandela, Brtain don’t support terrirost regim in Ethiopia, ” የሚሉት ይገኙበታል::
እንደተለመደው በድርጅቱ የተዘጋጀውን ደብዳቤ በድርጅቱ ተወካዮች በአቶ ይበልጣል ጋሹ እና በአቶ ዮናስ ዮሴፍ አማካኝነት ለእንግሊዝ ኢምባሲ ተወካይ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳዩ ትኩረት የሚሻና ጊዜ የማይሰጠው መሆኑን በመግለጽ ህይወቱም በእጅጉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንዳለ በጥብቅ በማሳሰብ ደብዳቤውን በኢምባሲው ተወካይ አማካኝነት እንዲደርሳቸው ተደርጓል።
በመጨረሻም ግፈኛው የወያኔ ቡድን በለመደው ተራ የሀሰት ወሬ በሚያወራበት ቴሌቪዥኑ ላይ ለትርጉም በሚያስቸግር መልኩ ቆራርጦና በጣጥሶ አንዳርጋቸውን ለማስወራት መሞከሩ የወያኔን ከንቱነት እና እውቀት ዓልባነቱ እንዲሁም ለህዝብና ለአገር የሚሰጠው ንቀት ይበልጥ ለዓለም መጋለጡ ለእኛ ለአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ህብርትና አንድነት ፈጥረን በእልህ፣ በቁጭትና በቁርጠኝነት ከበፊቱ በበለጠ ትግላችንን አጠናክረን እንድንቀጥል ትልቅ በር ከፍቶልናል፤ ለትግልና ለተቃውሞም ይበልጥ አነሳስቶናል። እንደ አርበኞችና ግንቦት ሰባት የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችም ውህደት ፈጥረው በሁለገብ ትግል ዘረኛው ወያኔን  ለማስወገድ ቆርጠው እንዲነሱ የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ዮሐንስ ዓለሙ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። በተመሳሳይም የወጣቶች ክፍል ተወካይ አቶ ይበልጣል ጋሹ ወጣቶች ለፍትህ፣ ለነጻነትና ዲሞክራሲ ለሚደረገው ትግል አስትዋጾ ማድረግ እንዳለባቸው በአጽንኦት አሳስበዋል።
ወጣት ሁሉን ነገር የመለወጥ ኃይልና አቅም አለው!አምባገነን መንግሥትን ማስወገድ እንችላለን! ወያኔን ከኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ማስወገድ እንችላለን!
ዛሬም ነገም ሁላችንም አንዳርጋቸው ፅጌ ነን!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
የወጣቶች ክፍል

ያልተቀደሰው ጋብቻ!! ኢህአዴግ፣ ፋና፣ ኢብኮ፣ ምርጫ ቦርድ (ጌታቸው ሺፈራው)



በአንድ ወቅት ኢህአዴግ «የሚወዳደረኝ ተቃዋሚ ጠፋ» ብሎ ቀልዶ ነበር። በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ተበታትነው የነበሩት ተቃዋሚዎች ቅንጅትን ፈጥረው 1997 ምርጫ ላይ ሲያሸንፉት ደግሞ ቀልዱን ረስቶት ወደ ምርጫ የሚያመራውን መንገድ ሁሉ ለመዝጋት መታተር ያዘ። የፀረ ሽብር፣ የፕሬስ፣ የሲቪክ ማህበራት….አዋጆች «ከእኔ ጋር ለመወዳደር አቅም የላቸውም።» ይላቸው የነበሩትን ተቃዋሚዎች ወደ ምርጫ የሚያመሩበትን መንገድ የሚዘጉ መሰናክሎች ሆኑ። ያም ሆኖ ግን በእነ ኢዴፓ፣ የአየለ ጫሚሶው «ቅንጅት»ና መሰል ፓርቲዎች በመታጀብ ምርጫን ለይስሙላነት መጠቀሙን ቀጥሏል። በዚህ ሂደት ውስጥ ሳያሸንፍም ቢሆን አሸንፈሃል የሚለው «ምርጫ ቦርድ» ጋር እጅና ጓንት ሆኖ ይሰራል። ለኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ ያልሆነውን ኢህአዴግን ብቸኛ አማራጭ አድርገው የሚያቀርቡት ኢቲቪና ፋና አሉ። ሚዲያና ምርጫ ቦርድ ኢህአዴግ በተቃዋሚዎች ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚጠይቃቸውን ጥያቄዎች በማንሳት ተቃዋሚዎችን በህዝብ አይን ማሳነስ ዋነኛ ስራቸው ሆኗል። በተለይ ምርጫ በተቃረበ ቁጥር ኢህአዴግ፣ ፋና፣ ኢብኮ፣ ምርጫ ቦርድ ሆነው በአንድነት በተቃዋሚዎች ላይ መዝመታቸው የተለመደ ነው።
የኢህአዴግ፣ የፋና፣ የኢብኮና የምርጫ ቦርድ ጥምረት በዚህ አመትም ተጠናክሮ ቀጥሏል። ኢህአዴግ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ህጋዊ እውቅና አግኝተው በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ መሆናቸውን ረስቶ «ህገ ወጥ፣ አሸባሪ…» እያለ መክሰስና ስም ማጥፋቱን የመጀመሪያ ስልት አድርጎ ውስዶታል። ምርጫ ቦርድ ይህን የኢህአዴግ ፍረጃ ተንተርሶ መኢአድ፣ አንድነትና ሰማያዊ ፓርቲ ላይ ምርጫ ቦርድ እሱ የማያገባውን ጥያቄ እያነሳ «ህገ ወጦች ናችሁ» እያለ በሆነ ባልሆነው ሲጠምዳቸው ከርሟል። ኢቲቪ (ኢብኮ) እና ፋና ምርጫ ቦርድ እና ኢህአዴግ ተቃዋሚዎች ላይ የሚለጥፉትን ስም፣ የሚያነሱትን ክስ ደጋግመው ለህዝብ ያሰማሉ።
አሁን አሁን ደግሞ እነዚህ ያልተቀደሰ ጋብቻ የፈፀሙት አካላት ለተቃዋሚ ፓርቲዎች አንጃ እስከመፍጠር ደርሰዋል። ለዚህ ያልተመቿቸውን ፓርቲዎች ደግሞ ክፍተት በመፈለግ ለመክሰስና ስም ለማጥፋት ሌት ተቀን እየሰሩ ነው። በእነዚህ አካላት የስም ማጥፋት መዝገብ እየተፈለገላቸው ካሉ ፓርቲዎች መካከል ሰማያዊ ፓርቲ አንዱ ነው።
በቅርቡ እስካሁን ለሰማያዊ ፓርቲ ምንም አይነት ሽፋን ሰጥተው የማያውቁት ፋና እና ኢቲቪ (ኢብኮ) በአንድ ቀን ልዩነት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነቱ ጋር ሰፊ ቃለ መጠይቅ አድርገው ነበር። የፋናው «ሞጋች» ፕሮግራም አዘጋጅ አቶ ብሩክ ኢ/ር ይልቃልን፣ እንዲሁም ኢብኮ (ኢቲቪ) አቶ ዮናታን ተስፋዬን አነጋግረው ነበር። ሆኖም የሁለቱም ቃለ መጠይቅ ሳይቀርብ የቀረ ሲሆን ፋና «ፋይሉ ጠፍቶብኝ ነው። ሌላ ቀን ቃለ መጠይቅ እናደርጋለን›› የሚል መልስ ሰጠ። ሰማያዊ ፓርቲ ሁለቱም ሚዲያዎች የአመራሮቹን ሀሳብ አፋልሰው ያቀርባሉ በሚል ቀረጻ አድርገው ስነበር «ችግር የለም። እኛ ጋር ስላለ ውሰድ። ቢሉትም «እናንተ የቀረጻችሁት ለሚዲያ አይሆንም» በሚል ሳያቀርቡት ቀርተዋል። የሚገርመው በፕሮግራሙ ወቅት ሰማያዊ ፓርቲን በመክሰሻነት ሊቀርቡ የነበሩት ሰማያዊ ፓርቲ ቀርጾ በሚዲያ ያስተላለፋቸው ድምጾች መሆናቸው ነው። እነዚህ በተለያዩ ጊዜያት የሰማያዊ አመራሮች ያደረጓቸውን ንግግሮች ከኢንተርኔት ተለቅመው በመሞገቻነት ሲቀርቡ ይህኛው ግን «ለሚዲያ አይሆንም!» ተብሏል። ነገሩ ወዲህ ነው። ፋና እንደፈለገ ቆራርጦ፣ ከፍቶ እንዳያቀርብ ሰማያዊ ሙሉውን ይለቀዋል። ከዚህ በላይ ግን ሌላም ምክንያት ነበረው። ፋናዎች ከኢህአዴግና ምርጫ ቦርድ ጋር በጋራ ያቀዱትን አላማ የሚያሳካ አልነበረም።
በተመሳሳይ ኢቲቪ (ኢብኮ) ቅዳሜ ጥር 16/2007 ዓ.ም ጠዋት ማታ ከ2 ሰዓት ዜና በኋላ የሚቀርብ ቃለ መጠይቅ ነው ብሎ ዮናታን ጋር ሰፊ ቃለ መጠይቅ አድርጎ ነበር። እሱም ቢሆን ሳያስተላልፈው ቀርቷል። ከዚህ ይልቅ በአንድ ወቅት የህዝብ ግንኙነቱ ከሌላ ጋዜጣ ጋር ያደረገውን ቃለ መጠይቅ መሰረት በማድረግ (አብዛኛዎቹ ጋዜጣው ላይም የሉም) «ሰማያዊ ፓርቲ ህዝቡ የምርጫ ካርድ እንዳይወስድ እየቀሰቀሰ ነው፣ ምርጫውን የሚጠቀምበት አመፅ ለማንሳት ነው…» የመሳሰሉ ክሶችን አቅርቧል።
ፋና እና ኢቲቪ (ኢብኮ) ከሁለቱ አመራሮች ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ አግኝቼ እንዳዳመጥኩት ሁለቱም «ሚዲያዎች» ያቀረቧቸው ጥያቄዎች ተመሳሳይ ናቸው። ከጥያቄዎች መካከል አብዛኛዎቹ «ሰማያዊ ምርጫውን የሚፈልገው አመፅ ለማስነሳት ነው፣ የቀለም አብዮት ማስነሳት ትፈልጋላችሁ፣ ለምርጫ ቦርድ እውቅና አትሰጡም፣ ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን አትፈልጉም…» የሚሉ ለኢህአዴግና ለምርጫ ቦርድ ክስ የሚያመቹ ክፍተቶችን ያስገኛሉ ተብለው የታሰቡ (ምን አልባትም የተቀነባበሩ) ጥያቄዎችን ናቸው። ሆኖም ሁለቱም አመራሮች የሰጡት ቃለ መጠይቅ ኢህአዴግና ምርጫ ቦርድ በሚፈልጉት መልክ ሆኖ አልተገኘም። ሰማያዊን በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ ያሳውቃል ተብሎ በኢህአዴግ አመራሮች ዘንድ ስለታሰበበትም ይመስላል በሁለቱም ሚዲያዎች እንዳይቀርብ ተደርጓል።
በተለይ «ሞጋች» የሚባለው ፕሮግራም አዘጋጅ ኢ/ር ይልቃል ኢህአዴግና ምርጫ ቦርድ ወደሚፈልጉት ክፍተት እንዳልገባ ሲያውቅ «ይህ አሁን የሚነግሩን ቀድሞ ስትሉት ከነበረው አቋም ይለያል፣ ተለሳለሳችሁ!» ሲል ምን ይፈልግ እንደነበር ሳያስበውም ቢሆን ተናግሯል። ኢንጅነሩ በበኩሉ እሱም ሆነ ፓርቲው የተለየ አቋም እንዳልያዙ ብሩክ ከኢንተርኔት የወሰዳቸው ድምጾች ላይ የተነገሩት ነገሮች ምንም አይነት ስህተት እንደሌለባቸው ደግሞ ያስረግጣል። አሁንም ብሩክ ሌላ ድምጽ አሰምቶ ሰማያዊን «ህገ ወጥ» ሊያደርግ ይሞክራል። ኢንጅነሩ «ምንም ስህተት የለበትም» ብሎ ዳግመኛ ያስረግጣል። አቶ ብሩክ በኢህአዴግና በምርጫ ቦርድ በኩል ሰማያዊን «ህገ ወጥ» የሚያሰኝ ክፍተት ለማግኘት «አገዛዝ ፈቅዶ መብት አይሰጥም» የተባለበትን ድምጽ ሳይቀር ህገ ወጥ አድርጎ ለማቅረብ ሞክሯል። «ምርጫ ቦርድን ትዘልፋላችሁ፣ ስብሰባዎችን ረግጣችሁ ትወጣላችሁ» ይላል ብሩክ፤ ኢንጅነር ይልቃል በበኩሉ «አሁንም የሚሳሳት ከሆነ ደግመን ደጋግመን አቋርጠን እንወጣለን» ብሎ አቋማቸውን ያስረግጣል።
በአጠቃላይ ሁለቱም ሚዲያዎች ከሰማያዊ አመራሮች ጋር ያደረጓቸው ቃለ መጠይቆች ላይ የተነሱ ጥያቄዎች ሰማያዊን ለመክሰስ ቀዳዳ የተፈለጉባቸው ይመስላሉ። ሆኖም አመራሮቹ ለክስ የሚመቹ ነገሮች ይልቅ ፓርቲውን የሚያስተዋውቁ መልሶችን በመስጠታቸው ጥያቄዎቹን ላወጧቸው የፓርቲ አመራሮች ኪሳራ እንደሆነ ገብቷዋልና እንዳይቀርቡ ተደርገዋል። የሁለቱ ሚዲያዎች ሆን ተብለው የተቀነባበሩ የሚመስሉ ጥያቄዎች፣ እንዲሁም ቃለ መጠይቁ ፓርቲውን መክሰስ ለሚፈልጉ አካላት የማይጠቅም በመሆኑ እንዳይተላለፍ መደረጉ አራቱ ተቋማት በጋራ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ የከፈቱትን ዘመቻ የሚያሳይ ነው። ሁለቱም ሚዲያዎች ከሰማያዊ አመራሮች ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ ገዥውን ፓርቲና ምርጫ ቦርድን እንዳያጋልጥ ተብሎ ባይቀርብም ሁለቱም ለኢሳት እንደደረሰ ታውቋል። ከገዥው ፓርቲና ከምርጫ ቦርድ ጋር ባበሩት ሁለቱ «ሚዲያዎች» ለህዝብ እንዳይደርስ የታፈነው ድምጽ በኢሳት በኩል ለህዝብ እንደሚደርስ ይጠበቃልና ኢሳት ላይ ተከታትሎ ፍርድ መስጠት ይቻላል።
~~ነገረ–ኢትዮጵያ~~

የኢትዮጲያ ፖለቲካ መልኩን የሚቀይርበት 11ኛው ሰዓት ላይ ደርሷል!



መግቢያ መውጫ አሳጥቶ፤ የወንድ በር እንኳን ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን በማን አለብኝነትና በትምክህት ስነልቦና ተወጥሮ በአፈና ጅራፉ ሲገርፈን ፀጥ ብለን የምናይበት የፈሪ ልብ፤ መጠን ያለፈውን የጭቆና ቀንበር የምንሸከምበት ጫንቃ የለንም፡፡
አዎን ኢህአዴግ የደም መስዋዕትነት የከፈልኩበትን ስልጣን በቀላሉ አለቅም በሚል የሞት የሽረት ትግል እንደሚያደርግ ሁሉ እኛም ጓዶቻችን የታሰሩበትን ትግል እና ፓርቲ ወደጎን ትተን የትም አንሄድም፡፡ አንዱአለም አራጌ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ አብርሀ ደስታ፣ አግባው ሰጠኝ እና ሌሎቹም የታገሉለትን አላማ ከግብ ሳናደርስ ወደኋላ ማለት የለም፡፡
ትግሉ ሰላማዊ እና ሰላማዊ ብቻ እንዲሆን ከአንድ ወገን ብቻ (ከተቃዋሚዎች በኩል) እየተደረገ ያለውን ጥረት ኢህአዴግ እንደፈሪነት እየቆጠረው በትዕቢት ተወጥሮ ያስራል ይገላል፡፡ ነገም ኢህአዴግ ከዚህ የተለየ ነገር አያደርግም፡፡
ፓርቲያችን አንድነትን ለጀሌዎችህ ስትሰጣቸው እጃችንን አጣጥፈን ዝም ብለን አናይህም በሚል ነገ የአንድነት አባላቶች እና ደጋፊዎች ሰልፍ ሲወጡ ወያኔ እንደለመደው ያስራል፡፡
ዛሬ በልሳኑ ኢቲቪ/ኢቢሲ ደግሞ ሰማያዊ ምርጫው ሰላማዊ እንዳይሆን እሰራለሁ አመፅንም እጠራለሁ ብሏል ሲል በሬ ጥጃ ወለደ ዲስኩሩን ደስኩሯል፡፡
አንድነትን ለእነ ትዕግስቱ አወሉ ሰጥቼ እውነተኛ አመራሮቹንም አስሬ አፈርሰዋለሁ፤ ሰማያዊን ደግሞ አመፅ ሊጠራ ነው በሚል ፓርቲውን አግዳለሁ አመራሮቹንም አስራለሁ በሚል ስሌት እየሰራ እንደሆነ ከመቼውም ጊዜ በላይ ግልፅ ሆኗል፡፡
እንግዲያው ፓርቲዎችን ከዘጋ፣ ህጋዊ አመራሮችንም ካሰረ እና ሰላማዊውን መንገድ ከዘጋው የኢትዮጲያ ፖለቲካ መልኩን ይቀይራል፡፡
ጓዶቹ የታሰሩለትን ፓርቲ፣ አላማ እንዲሁም ትግል ወደጎን ትቶ የሚሄድ የለምና አሁን ትግሉ ሞትን ፊት ለፊት የመጋፈጥ እና ነፃነትን የመሻት ነው፡፡ ‹‹የሰላም በሮች ሲዘጉ የአብዮት በሮች ይከፈታሉ›› እንዲል ጋዜጠኛው ነቢዩ፡፡
አንለያይም ሞትም ቢመጣ!!!

አቶ ትግስቱ አወሉ በአንድነት የክልል አመራሮች ላይ በስልክ ዛቻ እየፈፀሙ መሆኑ ተገለፀ፡፡


የአንድነት ፓርቲ ሰሞኑን በኢህአዲግና ምርጫ ቦርድ ከፍተኛ ዘመቻ ተከፍቶበት እንደሚገኝ መላው ኢትዮጵያዊ እየተከታተለው ያለ እውነታ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከምርጫ ቦርድ ጋር በመሆን አንድነት ፓርቲን ለመፈረካከስ ከሚሰሩት ግለሰቦች መካከል አቶ ትግስቱ አወሉ የተባሉና የቀድሞ የአንድነት አባል በአሁኑ ሰዓት እራሳቸውን ፕሬዝደንት አድርገው ከምርጫ ቦርድ ጋር በጋራ በመስራት ላይ ያሉ ግለሰብ በ16/05/2007 ዓ.ም ላደረጉት ህገ…-ወጥ ጉባኤ ተልእኳቸውን ለማስፈፀም በየክፍለሀገሩ የሚገኙ የአንድነት ፓርቲ የጉባኤ አባላትን በስልክና በአካል በመሄድ ለዚህ ህገ-ወጥ አንድነት ፓርቲ ነኝ ባይ ጉባኤ እንዲገኙ በማግባባት፤ከመንግስት ፈሰስ በተደረገላቸው ገንዘብ በመደለል እንዲሁም እንቢ ያሉ ግለሰቦችን ‹‹መንግስት ከኔ ጎን ነው እንቢ ካልክ/ሽ እርምጃ እንወስዳለን፤…..ወዘተ›› ማስፈራሪያ ሲጠቀሙ እንደነበር በየአካባቢው የሚገኙ የአንድነት አባላት ሰሞኑን ሲገልፁ የነበረ ሲሆን ዛሬ በደረሰን መረጃ መሰረት ግለሰቡ በደቡብ ወሎ የአንድነት መዋቅር በሚገኝባቸው ሐይቅ፤ወረባቦ፤ደሴ፤ኮምቦልቻ፤ኩታበር …….የመሳሰሉት ወረዳዎች የሚገኙ የአንድነት የወረዳ አመራሮች ጋር ስልክ በመደወል ከፍተኛ መስፈራራትና ዛቻ የተቀላቀለበት ድርጊት መፈፀማቸውን ከየወረዳዎቹ ያሉ የአንድነት አመራሮች ሪፖርት አድርደዋል፡፡ ግለሰቡ አንድነት ፓርቲ የኔ ነው፤እኔም ነኝ የምመራው፤ በኔ አስተዳደር ስር ሆናችሁ ላለመሳተፍ ከወሰናችሁ፤ በመንግስት በኩል ከፍተኛ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት ተደርጓል›› ….ወዘተ የሚል ማስፈራሪያ እንደሚያሰሙ ገልፀዋል፡፡ አባላቶቹ አያይዘውም ‹‹እኛ አንድነት አንድ እንጂ ሁለት አይደለም፤ህጋዊ የሆነው አንድነት ፓርቲ በተገቢው ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ ባለበት አግባብ መንግስትና ምርጫ ቦርድ ፓርቲውን ለመበታተን ለሚያደርጉት ዘመቻ ተገዢ አንሆንም፤ሰላማዊ ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ አቶ ትግስቱ አወሉ በህጋዊውና በትክክለኛው የአንድነት ፓርቲ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ እራሳቸውን እጩ አድርገው አቅርበው በመሳተፍ የራሳቸውን አንድ ድምፅ ብቻ አግኝተው መውደቃቸው የሚታወስ ነው

Ethiopian woman gives birth at the age of 56

Ethiopian woman gives birth at the age of 56


Following years of struggling to conceive, Ethiopian woman gives birth at 56.

A 56-year-old Kiryat Malachi woman gave birth at the age of 56 to her first child — a healthy 3.01-kilo baby boy.
The new mother came on aliya from Ethiopia during Operation Solomon in 1991.
Ethiopian immigrant has baby at 56
Ethiopian immigrant has baby at 56 at Kaplan Medical Center.. (photo credit:Courtesy)
Kaplan Medical Center in Rehovot reported on Monday that the woman was kept in a hospital bed for a month to protect the fetus from movement that could endanger the birth, which was carried out by cesarean section.
The woman, Tami, has nine brothers and always dreamed of having her own child, but she and her husband did not succeed. After a long, supportive talk with her niece, who urged her not to give up, she discovered she was pregnant. She thanked the hospital staff for their devotion and support. “I am so excited that I am now able to hold this stota (“gift” in Amharic) in my arms,” she said.
Prof. Zion Hagai, head of obstetrics at the hosptial, said that “the Kaplan medical staff honor the will of women who want to become a mother even at an advanced age. There is no doubt that there are risks posed by pregnancy and during a cesarean section at an advanced age. But at the same time, the risks vs. benefits are considered, especially for a first birth… In this case, Tami gave birth to a healthy baby.”

Sunday, January 25, 2015

UK diplomats clash over Briton on death row in Ethiopia:

UK diplomats clash over Briton on death row in Ethiopia: Officials’ fury after Foreign Secretary claims he couldn’t ‘find time’ to help father-of-three facing execution

    • Andargachew Tsege was snatched by officials at Yemen airport last June
    • The 59-year-old was transferred to Ethiopia where he is thought to remain
    • Father-of-three moved to London in 1979 from native African country
    • He was dubbed ‘Ethiopian Mandela’ after exposing government corruption
    • Leaked emails revealed British officials’ frustration at political inaction
    • Philip Hammond said he could not ‘find time’ for phone call on issue 
    By Ian Birrell for The Mail on Sunday
    An explosive row has erupted between diplomats and Ministers over their reluctance to help a British man on death row in Ethiopia.
    A series of extraordinary emails, obtained by The Mail on Sunday, reveal officials’ increasing frustration at political inaction over Andargachew Tsege.
    Tsege, 59, a father-of-three from London, was snatched at an airport in Yemen last June and illegally rendered to Ethiopia. There are concerns he may have been tortured.
    Yet Foreign Secretary Philip Hammond said he could not ‘find time’ for a phone call to raise the issue and did not want to send a ‘negative’ letter.
    In one email, an exasperated official asks: ‘Don’t we need to do more than give them a stern talking to?’
    MCILG-Ethiopia-Tsege-001.jpgTsege, who has lived in the UK since 1979, has been called Ethiopia’s Nelson Mandela. Tsege fell out with his university friend ex-Prime Minister Meles Zenawi, after he exposed government corruption and helped establish a pro-democracy party.
    In 2009, he was sentenced to death in his absence for allegedly plotting a coup and planning to kill Ethiopian officials – claims he denies.
    He was abducted on June 23 while en route to Eritrea, emerging two weeks later in Ethiopia, where he has since been paraded on TV. It is not known where he is being held.
    The diplomatic exchanges disclose how officials were dismayed when British Ministers rejected requests to raise the case with Ethiopia.
    ‘I feel so shocked and let down,’ said Tsege’s wife Yemi Hailemariam. ‘I thought Britain was a nation driven by fairness but it seems my husband’s life is simply not valued.’
    The series of emails begins on July 1, with Foreign Office officials confirming his capture: ‘His detention in Yemen is significant news, and could get complicated for the UK.’
    Diplomats noted that neither Yemen nor Ethiopia informed Britain about the rendition of its citizen. ‘It feels a bit like I’m throwing the kitchen sink at the Yemenis but I want them to think twice before they do this again,’ wrote one senior figure at the British Embassy in Addis Ababa.
    He also noted that a prominent Ethiopian minister had given assurances over Tsege’s treatment –‘but I wouldn’t take them with complete confidence’.
    Ethiopia has claimed Tsege tried to recruit other Britons to become involved in terrorism. But the regime has used anti-terror laws to jail journalists and silence political rivals, and UK officials had not seen credible evidence.
    Foreign Secretary Philip Hammond said he could not ‘find time’ for a phone call to raise the issue and did not want to send a ‘negative’ letter.

























    Foreign Secretary Philip Hammond said he could not ‘find time’ for a phone call to raise the issue and did not want to send a ‘negative’ letter.
        One diplomatic cable says: ‘All we have seen are a few pictures of him standing in an Eritrean village – hardly proof that he was engaged in terrorist training.’
      Three weeks after Tsege’s kidnap, the Foreign Office’s Africa director wrote that Ministers ‘have so far shied away from talking about consequences… their tone has been relatively comfortable’.
      On July 21, Hammond’s office was still reluctant to talk to his Ethiopian counterpart on the phone.
      ‘I don’t think we are going to be able to find time for that at the moment,’ wrote his private secretary. He also turned down sending a ‘negative’ letter, asking for it to be rewritten ‘setting out areas of co-operation. It can end with a paragraph on the Tsege case.’
      Despite concerns over Ethiopia’s human rights record, the nation receives £376 million a year in UK aid. One farmer there is suing Britain, claiming the money was used to usurp him from his land.
      Hammond is believed to have finally called his counterpart at the end of July, one month after the kidnap. It is understood he focused on requesting consular access rather than condemning the capture.
      Reprieve, which campaigns against the death penalty said: ‘These shocking emails show the Foreign Secretary appears to have blocked any meaningful action that could potentially bring this British father home to his family, unharmed.’
      The Foreign Office said they were ‘deeply concerned’ by Tsege’s detention and were lobbying for further consular access as well as seeking confirmation the death penalty would not be carried out.



      የ9ኙ ፓርቲዎች ስብስብ ስርዓቱ ዛሬ በአዲስ አበባ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የፈጸመውን ድርጊት አወገዘ


      ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ
      የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር አብሮ ስለመስራትና ሌሎቹም ትብብሩን እንዲቀላቀሉ በየጊዜው የሚወተውተው አገራችን በዚህ ዘመን በማይመጥን አምባገነንና የጭካኔ ስርዓት ውስጥ የምትገኝ መሆኑን በመረዳቱ ነው፡፡ ይህ የህወሓት/ኢህአዴግ አምባገነንና ጨካኝ ስርዓት ህዳሩ 27/28 2007 ዓ.ም የአዳር ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በወጡት አመራሮቻችን፣ አባላቶቻችን፣ ደጋፊዎቻችንና በየጎዳናው የተገኙት ንፁሃን ላይ ከፍተኛ ድብደባና የጅምላ እስር በመፈፀም ስርዓቱን ለመታገል የተነሳነበትን አላማ ትክክለኝነት አረጋግጦልናል፡፡
      በዛሬው ዕለትም ገዥው ፓርቲ በፓርቲያቸው የውስጥ ጉዳይ ገብቶ የሚፈፅመውን ደባ፣ ምርጫ ቦርድንና የህዝብ ሚዲያን ተጠቅሞ ፓርቲውን ለመከፋፈልና አሳንሶ ለማሳየት የሚያደርገውን እኩይ ተግባር በመቃወም ሰልፍ የወጡ የአንድነት አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎችና የፓርቲው ጽ/ቤት ፊት ለፊት የሚገኘው ቤተ ክርስትያን አካባቢ የነበሩ አዛውንት ምዕመናንን ሳይቀር በመደብደብ ጭካኔውን ዳግመኛ አሳይቶናል፡፡ ፖሊስ በትዕዛዝ በአንድነት አባላት ላይ ከፍተኛ የጭካኔ እርምጃ ወስዷል፡፡ አብዛኛዎቹንም በጅምላ አስሯል፡፡
      udj 10
      ስርዓቱ በእነዚህ ሰላማዊ ዜጎች ላይ አሁንም የጭካኔ እርምጃውን መድገሙ ስልጣኑን የማጣት ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንዳለ እና ከይስሙላ ያለፈ ለሰላማዊ ትግሉ ዝግጁ አለመሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ትብብራችን የስርዓቱን ጨካኝነት እያወቁም ቢሆን በሰላማዊ መንገድ ጥያቄያቸውን ለማቅረብ በስርዓቱ የማይከበረውን ህገ መንግስታዊ መርህ ተከትለው ሰልፍ ለወጡ ቆራጥ የአንድነት አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች አድናቆቱን መግለጽ ይወዳል፡፡ መስዋዕትነታችሁ ለነገ ድላችን ስንቅ በመሆኑ ይበልጡን ተጠናክራችሁ በጋራ ትግላችን እንደምናጠናክርም እምነታችን ነው፡፡
      በተቃራኒው ገዥው ፓርቲ ህግ የማክበርና የማስከበር ሚናውን ረስቶ ፖሊስ፣ ደህንነትንና ሌሎች ተቋማትን ለራሱ ስልጣን ማስጠበቂያ በማዋል በአንድነት አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎች ላይ የፈፀመውን ለዘመኑ የማይመጥንና በሰላማዊ መንገድ መብታቸውን ለጠየቁት ኢትዮጵያውያንም የማይገባ የጭካኔ እርምጃ በጥብቅ እናወግዛለን፡፡
      ኢትዮጵያውያንን የማስተዳደር አቅምና ሞራል ያጣው ገዥው ፓርቲ የዜጎችን ጥያቄ በኃይል ማዳፈን የማይቻል መሆኑንና አገራችን ወደባሰ ችግር እንደሚከታት ተረድቶ ከዚህ የጭካኔ እርምጃው እንዲቆጠብ፣ እርምጃውን የወሰዱትን አካላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑና የታሰሩትን በአስቸኳይ እንዲፈታ እናሳስባለን፡፡ ፖሊስ፣ ደህንነት፣ መከላከያና ሌሎች ተቋማት ገዥው ፓርቲ አላፊ መሆኑን በመገንዘብና ከገዥው ፓርቲ ታዛዥነት በመውጣት ወገኖቻቸሁ ላይ እንዲህ አይነት የጭካኔና አሳፋሪ እርምጃ ከመውሰድ ተቆጥባችሁ ከህዝብ ጎን እንድትቆሙ ጥሪያችን እናቀርባለን፡፡
      ያለ መስዋዕትነት ድል የለም!
      ጥር 17/2007 ዓ.ም
      አዲስ አበባ

      Open Letter to Deutsche Bank officials

      Open Letter to Deutsche Bank officials

      January 10, 2015
      Mr Jürgen Hinrich Fitschen
      Co-Chairman of Management Board and Co-Chief Executive Officer, Deutsche Bank AG
      Taunusanlage 12, Frankfurt am Main, 60325, Germany
      Dear Mr Hinrich Fitschen
      The Global alliance for human rights and Justice in Ethiopia have learned that you are one of the underwriters of sovereign bond issued by the repressive regime in Ethiopia, the bond that would mortgage the country itself, with the pretext to finance projects that include electricity generation and sugar cane plantation involving displacement of 500,000 habitants.
      Ethiopia a country at the bottom of the UN Human Development Index – 173rd out of 187 nations and cautions about the possibility of political turmoil is already heavily indebted. As of 31st December 2013 this national debt was reported to stand at $11.99 billion and the rulers in power are finding it difficult to service their obligations. We trust that you are already aware of the risk, by the admission of the Ethiopian regime itself, the sovereign bond bears to investors besides the possible disaster it would bring upon the human rights conditions in Ethiopia. (see the Financial Times of London 31/12/2014 “Ethiopia issues unfamiliar investor warning over war and famine” (http://www.ft.com/cms/s/0/c8691100-7a07-11e4-8958-00144feabdc0.html#axzz3NKioSfNd).
      Ethiopia’s repressive practices include jailing and silencing critics and media, enacting laws to close civil society, undermine human rights activity, and hobbling the political opposition. Only a few days before we celebrate Christmas 2014 scores of Christian parishioners were shot dead in a city north of the Capital for protesting against the grabbing of their historic place of worship by officials of the brutal regime in the name of development.
      The brutal regime in Ethiopia has extended its repressive network and engaged in abducting European citizens (British and Norwegian nationals) demanding freedom in their home land and subjects them to daily torture. Human Rights Watch recently reported on a host of other political refugees Abducted by Ethiopian Security forces from neighbouring countries and rendered to Ethiopia for inhuman treatment.
      Therefore, we kindly request you to distance yourself from the blood-tainted hands of the Ethiopian regime, and desist from the unethical practice of doing business with the authoritarian regime of Ethiopia.
      Yours sincerely,
      —————————————
      For free fax: http://faxzero.com/

      አንድነት በደብረማርቆስ እና በሸዋሮቢት ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ


      • 156
         
        Share
      udj deberemarkos
      አንድነት ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በደብረማርቆስ እና በሸዋሮቢት ከተሞች ዛሬ ጠርቶት የነበረው ሰላማዊ ሰልፎች በስኬት መጠናቀቃቸውን ለዘ-ሐበሻ የደረሱት መረጃዎች አመልክተዋል::
      እንደ እንደረሰን መረጃ ከሆነ ደብረ ማርቆስ ሰልፉ ከጠዋቱ በአራት ሰዓት የተጀመረ ሲሆን በርከት ያለ ሰው በሰልፉ ተገኝቷል።
      በሰልፉ ላይ የተገኘው ሕዝብ
      – ድል የሕዝብ ነው !
      – አንድነት አንድ ነው !
      – ዉሸት ሰለቸን ፣
      – ኢሕአዴግ በቃህ፣
      – ጭካኔ በቃን፣
      – ግፍ በቃን፣
      – ኢሕአዴግ ይወድቃል !
      – ኢትዮጵያ ነጻነቷን ትሻለች !
      ኢቲቪ፣ ኢቢሲ ዉሸት ነህ ! ….የሚሉ መፈክሮች ሰልፈኞቹ ከማሰማታቸውም በላይ የሕወሓት መንግስት አንድነትን ለማፍረስና ተለጣፊ አንድነት ለመመስረት የሚያደርገውን ሴራ እንዲያቆም ጠይቀዋል።
      ሰልፈኞቹ በአዲስ አበባ የሕወሓት ወታደሮች በሰላማዊው ተቃዋሚ ሰልፈኛ ላይ የቆመጥ መዓት ማውረዳቸውን በሰልፉ ላይ እንደሰሙም በአዲስ አበባ እየደረሰ ያለውን ግፍ እናወግዛለን ሲሉም ኢሰብዓዊ ግፍ አውግዘዋል::
      በሸዋሮቢት ከተማም እንዲሁ ተመሳሳይ ድምጽ የተሰማ ሲሆን የሕዝቡ ስሜትና መነቃቃት በጣም አስደናቂ እንደነበር ከሰልፈኞቹ ያገኝነው መረጃ ያመለክታል:: በሸዋሮቢት ምንም አይነት እስር ሆነ ድብደባ በአገዛዙ የደህንነት ሰራተኞች ያልታየ ሲሆን ምናልባትም ከሰልፉ መጠናቀቅ በኋላ የሕወሓት ተላላኪዎች እርምጃ ሊወስዱ እንደኢችሉ ይጠበቃል::
      የሚሊዮን ድምጽ ስለደብረማርቆሱ ሰልፍ የሚከተለውን ዜና ዘግቧል:-
      አንድነት ፓርቲ በደብረማርቆስ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄደ
      አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ በደብረማርቆስ ከተማ በዛሬው ዕለት የተቃውሞ ሰልፍ አካሄደ፡፡
      አንድነት በዛሬው ዕለት መነሻውን ከደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ መድረሻውን ደግሞ የንጉስ ተክለሀይማኖት ቤተመንግስት ከሚገኝበት ተክለሀይማኖት አደባባይ ያደረገ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዷል፡፡ ፓርቲው ባደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የፓርቲው አባላት፣ ደጋፊዎች እና የደብረማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች የተገኙ ሲሆን በሰልፉ ላይ የተገኙት ታዳሚዎችም ምርጫ ቦርድና ገዢው ፓርቲ አንድነትን ለማፍረስ የሸረቡትን ሴራ አውግዟል፡፡
      በሰልፉ ላይ በርካታ መፈክሮች የተስተጋቢ ሲሆን ከእነዚህም መሐል በሕዝብ ላይ ፍርሐትን ማንገስ የአምባገነንነት መገለጫ ነው፣ አንድነት አንድ ነው፣ ምርጫ ቦርድ ለገዢው ፓርቲ እያሳየ የሚገኘውን ወገንተኝነት ያቁም፣ አንድነት የህዝብ ነው፣ ሬዲዮ ፋና እና ኢቲቪ በህዝብ ላይ ውዥንብር ለመፍጠር እየሰሩ የሚገኙትን ደባ እንቃወማለን እና ሌሎች መፈክሮችም በስፋት ተስተጋብተውበታል፡፡
      በእለቱ በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ለተገኙት ታዳሚዎች የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል አቶ ዳዊት አስራደና የአንድነት ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ሰብሳቢ አቶ አየነው ተመስገን በሰልፉ መጠናቀቂያ ቦታ በሆነው ተክለሀይማኖት አደባባይ የመዝጊያ ንግግር አድርገዋል፡፡
      የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዳዊት አስራደ ሰልፉን በማስመልከት ለሚሊየኖች ድምፅ ሲገልፁ ‹‹የህዝቡን የቁርጠኝነት ደረጃ ያሳየ ስኬታማ የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄድ እንደተቻለ አውስተው ለህዝቡ ሊተላለፍ የሚገባው መልዕክት በአግባቡ መተላለፉን›› ገልፀዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ፓርቲው በደብረማርቆስ በሚገኘው ፅ/ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በአዲስ አበባ በአንድነት ፓርቲ አመራር አባላት፣ ደጋፊዎችና በሰልፉ ታዳሚዎች ላይ የደረሰውን እጅግ አሰቃቂ ድብደባ አውግዟል፡፡ የደረሰው ድብደባም ‹‹የእኛን አቅም የሚያጎለብት እንጂ የሚያንበረክክ አይደለም›› ሲሉ በመግለጫው አውስተዋል፡፡
      አንድነት ፓርቲ ከዚህ ቀደም በደብረማርቆስ ከተማ የሚሊየኖች ድምፅ ንቅናቄ ወቅት የተሳካ የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄዱ ይታወሳል፡

      wanted officials