የመኢአድ ምክትል ፕሬዝደንት አዘዞ ጦር ካምፕ መወሰዳቸው ተነገረ።
ጥር ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቀናት በፊት በፖሊሶች ከፍተኛ ድብደ ተፈጽሞባቸው ወዳልታወቀ ስፍራ ስለመወሰዳቸው የተዘገበው የመላው ኢትዮጰያ አንድነት ድርጅት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ዘመነምህረት አዘዞ በሚገኘው መከላከያ ካምፕ መታየታቸውን ፓርቲያቸው ገለጸ።
መኢአድ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የድርጅቱ ምክትል ፕሬዝደንት እና የሰሜን ቀጠና ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘመነ ምህረት የድርጅታቸውን ጠቅላላ ጉባኤ አድርገው ወደ መኖሪያቸው ጎንደር ከተማ ከተመለሱ በኋላ ከፍተኛ የደህንነት ክትትልና ጫና ይደረግባቸው እንደነበር ለፓርቲያቸው አሳውቀው እንደነበር አስታውሷል።
አቶ ዘመነ በ10/05/2007 ዓ.ም ጎንደር ከሚገኘው መኖሪያው ቤታቸው ከባቤታቸውና ከህጻን ልጃቸው ፊት የፖሊስ ልብስ በለበሱ አካላት ከፍተኛ ደብደባ ተፈጽሞባቸው ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን ያወሳው መኢአድ ፤በአሁኑ ወቅት የፓርቲው አባላት ባደረጉት ክትትል አዘዞ የሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ውስጥ እንደሚኙ መረጋገጡን ገልጿል።
<<በአቶ ዘመነ ላይ የደረሰባቸው ስቃይና እንግልት በሰው ልጅ ላይ ይፈጸማል ተብሎ ፈጽሞ የማይገመት ነው >>ብሏል-መኢአድ። ከአቶ ዘመነ በተጨማሪ ጠቅላላ ጉባኤውን ተሳትፈው የተመለሱት የፓርቲው የማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ አቶ እያሱ ሁሴን 3 አመት ተፈርዶባቸው እስር ቤት እንደሚገኙ እንዲሁም የፓርቲው አመራር አካላት የሆኑት አቶ ተስፋዬ ታሪኩ፣ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንንና አቶ ጥላሁን አድማሴ ታስረው እየተሰቃዩ እንደሚገኙ ገልጿል።
በሌላ በኩል ምርጫ ቦርድ- መኢአድ በምርጫ 2007 እንዳይሳተፍ የኢህአዴግ ቀኝ እጅ ሆኖ በመስራት ላይ እንዳለ ያወሳው መግለጫው፤ ፓርቲው በምርጫው እንዳይሳተፍ ከተደረገ ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል፡፡
ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ በፓርቲው ላይ የሚፈጽሙትን በደል ለማስቆም በሚደርገው ትግልም ህዝቡ ከጎኑ እንዲቆም ጥሪ መኢአድ አቅርቧል።

No comments:
Post a Comment