የአንድነት ፓርቲ ሰሞኑን በኢህአዲግና ምርጫ ቦርድ ከፍተኛ ዘመቻ ተከፍቶበት እንደሚገኝ መላው ኢትዮጵያዊ እየተከታተለው ያለ እውነታ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከምርጫ ቦርድ ጋር በመሆን አንድነት ፓርቲን ለመፈረካከስ ከሚሰሩት ግለሰቦች መካከል አቶ ትግስቱ አወሉ የተባሉና የቀድሞ የአንድነት አባል በአሁኑ ሰዓት እራሳቸውን ፕሬዝደንት አድርገው ከምርጫ ቦርድ ጋር በጋራ በመስራት ላይ ያሉ ግለሰብ በ16/05/2007 ዓ.ም ላደረጉት ህገ…-ወጥ ጉባኤ ተልእኳቸውን ለማስፈፀም በየክፍለሀገሩ የሚገኙ የአንድነት ፓርቲ የጉባኤ አባላትን በስልክና በአካል በመሄድ ለዚህ ህገ-ወጥ አንድነት ፓርቲ ነኝ ባይ ጉባኤ እንዲገኙ በማግባባት፤ከመንግስት ፈሰስ በተደረገላቸው ገንዘብ በመደለል እንዲሁም እንቢ ያሉ ግለሰቦችን ‹‹መንግስት ከኔ ጎን ነው እንቢ ካልክ/ሽ እርምጃ እንወስዳለን፤…..ወዘተ›› ማስፈራሪያ ሲጠቀሙ እንደነበር በየአካባቢው የሚገኙ የአንድነት አባላት ሰሞኑን ሲገልፁ የነበረ ሲሆን ዛሬ በደረሰን መረጃ መሰረት ግለሰቡ በደቡብ ወሎ የአንድነት መዋቅር በሚገኝባቸው ሐይቅ፤ወረባቦ፤ደሴ፤ኮምቦልቻ፤ኩታበር …….የመሳሰሉት ወረዳዎች የሚገኙ የአንድነት የወረዳ አመራሮች ጋር ስልክ በመደወል ከፍተኛ መስፈራራትና ዛቻ የተቀላቀለበት ድርጊት መፈፀማቸውን ከየወረዳዎቹ ያሉ የአንድነት አመራሮች ሪፖርት አድርደዋል፡፡ ግለሰቡ አንድነት ፓርቲ የኔ ነው፤እኔም ነኝ የምመራው፤ በኔ አስተዳደር ስር ሆናችሁ ላለመሳተፍ ከወሰናችሁ፤ በመንግስት በኩል ከፍተኛ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት ተደርጓል›› ….ወዘተ የሚል ማስፈራሪያ እንደሚያሰሙ ገልፀዋል፡፡ አባላቶቹ አያይዘውም ‹‹እኛ አንድነት አንድ እንጂ ሁለት አይደለም፤ህጋዊ የሆነው አንድነት ፓርቲ በተገቢው ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ ባለበት አግባብ መንግስትና ምርጫ ቦርድ ፓርቲውን ለመበታተን ለሚያደርጉት ዘመቻ ተገዢ አንሆንም፤ሰላማዊ ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ አቶ ትግስቱ አወሉ በህጋዊውና በትክክለኛው የአንድነት ፓርቲ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ እራሳቸውን እጩ አድርገው አቅርበው በመሳተፍ የራሳቸውን አንድ ድምፅ ብቻ አግኝተው መውደቃቸው የሚታወስ ነው
No comments:
Post a Comment