Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, January 22, 2015

የሕሊና እስረኛዋ ርዕዮት ዓለሙ ልደት: ከርዕዮት በጎውን እንቅና !


ይድነቃቸው ከበደ
ዙርያን በመመልከት ካለንበት መጀመር ለምንም ነገር የተሻለ ነው፤ ከቤተሰብህ፣ከጓደኛ፣ከማህበረሰብ ራስን ለመረዳት እና ትርጉም ያለው ሥራ ለመስራት፣ በጎውን ለማድረግ ብንቀና ለስኬታችን ቀላል መንገድ ነው፡፡ ለዚህም ይመስላል “በጎውንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቀችሁ ማን ነው ? በማላት በጴጥ.መ.ምዕ 3ቁ 13 ላይ ተገልፆ ይገኛል ፡፡
1310 ቀን በእስር እያሣለፈች የምትገኘው፣የተወዳጇ የጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ የልደት በዓል ፣እጅግ በጣም ደስ በሚል ሁኔታ በድምቀት ተከብሯአል፡፡ በልደት ቀኗ ተዋቂ ግለሰቦች፣የፓለቲካ ፓርቲ መሪዎች እና አባላት፣ጋዜጠኞች፣የማህበራዊ-ድረ ገፅ ዋንኛ አንቀሳቃሾች፣ ጓደኞቿ እና ቤተሰብ በመገኘት የበዓሉ ተካፋይ ለመሆን ችለዋል፡፡ በቦታው በመገኘት ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም፣ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ፣ኢ/ር ይልቃል ጌትነት እንዲሁም አቶ በላይ በፍቃዱ በተሰጣቸው አጭር ደቂቃ በመጠቀም ለርዮት መልካ ልደት ከመመኘት በላፈ ፣አስደማሚ ንንግር አድረገዋል፡፡
reyot alemu
በተለይ ፕ/ር መስፍን ያደረጉት ንግግር እና ያስተላለፉት መልዕክት በሁሉም ዘንድ አድናቆት የተቸረው ልብን ሰርስሮ የሚገባ ነው፡፡ አቶ በላይ በበኩላቻው ያደረጉት ንግግር የተጀመረው ሠላማዊ ትግል ለደቂቃ ያካል ወደኋላ ሣይል፣ ተጠናክሮ መቀጠል እናዳለበት እና ለዚህም በመትጋት ርዕዮት እና መሰሎቻ የእስር ጊዜ ለማሣጠር ያስተላላፉት መልዕክት እና ለተግባራዊነቱ የሚባክን ጊዜ አለመኖር ያመላከቱበት ንግግር በታዳሚው ዘንድ ተደማጭነት ያገኘ ሃሳብ ነው፡፡ኢ/ር ይልቃል ከርዕዮት ጋር ካለቸው ቀረቤታ መነሻ በማድረግ ፣መሠረታዊ የሆነ የርዕዮት የሁል ጊዜ ፀባይ ደፈርነት እና ግልፅነት በማስታወስ፣የሰው ልጅ እነዚህን ፀባይ ከአድር-ባይነት ተላቆ በአስታዋይነት የሁሉ ጊዜ ተግባሩ ካደረግ ፣ለየትኛውም ስኬት ቅርብ ነው፡፡ለዚህም ደግሞ ምስክር የምትሆነን ርዕዮት ናት በማላት ሁሉን አመላካች የሆነው ምርጥ ንግግር አድርገዋል፡፡
ከምንም በላይ ደግሞ በቃሊት እስር ቤት 1310 ቀን በስቃይ እያሳለፈች የምትገኘው ጋዜጠኛ እና መምእርት ርዮት አለሙ፡፡ አሁንም ደከመኝ ሰለቸኝ ሣትል የሁል ጊዜ እምነቷ በሆነው ሰላማዊ ትግል ያላት ተስፋ ሣይደበዝዝ፤ ለፓርቲ መሪዎች እና ለፖለቲካ ፓርቲ አባላት ያስተላላፈችው መልዕክት ነው፡፡የመልዕክቷ ዋንኛ ማጠጠኛ እውነተኛ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ቢቻል አንድ ሆነው ፣ካልሆነም ተከባብረው በሰላማዊ ትግል በአጭር ጊዜ አምባገነኑን ሥርዓት በማሸነፍ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣን ባለቤትነት እንዲያረጋግጡ ተማፅኖ ያልተለየው መልዕክቷ ፣ ከአምባገነን አገዛዝ ወደ-ዲሞክራሳዊ ለውጥ ለሚደረገው ትግል የሞራል ስንቅ መሆኑ ፣መልዕክቱ ተነቦ እንዳለቀ የነበረው ጭብጨባ እና አድናቆት አማላካች ነበር፡፡
ሻምፓኝ ተከፍቶ ወዲኽ-ወዲያ መወዛወዝ ባይኖርም ፣በግጥም ሥራው ብዙ አድናቂ ያተረፈው ፤በተለይ በማህበራዊ ድረ-ገፅ በሚያስገርሙ ግጥሞቹ የሚያስደስተን፣ ገጣሚ ዮሐንስ ሞላ ለርዕዮት መልካም ልደት ተመኝቶ ያቀረበው ግጥም ታዳሚውን ያስደመመ ነበር፡፡ የፋክት መፅሔት ም/ክ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ኃይለመስቀል በሸዋመምየለህ እና ጋዜጠኛ ስለሺ አጎስ እንደ-ቅደም ተከተላቸው ያቀረብት ፁሑፍ፣ የዕለቱን ፕሮግራም ፈካ በማድረግ ፁሑፍ ፃሃፊ ብቻ ሣይሆን ምርጥ አንባቢ መሆናቸውን አስመስክረወል፡፡
Journalist Reeyot Alemu
Journalist Reeyot Alemu
እነዚህ ከላይ የገለፅኳቸው በዛሬው ዕለት ቀበና በሚገኘው አንደነት ፓርቲ ፅ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከተከናወኑ ድረጊቶች በከፊል ነው፡፡በአጠቃላይ በዛሬው እለቱ የተገኙት በሙሉ እኔን ጨምሮ ለርዕዮት ልደት ነው፡፡ ርዕዮትን የሚያስታውስ አስከንድር ነጋ ፣ ተመሰገን ደሣለኝ፣ የሱፍ ሐመድን፣ውብሸት ታዬ፣ ዞን ዘጠኝ ጦማሪያን በፍፁም አይረሳም፡፡ስለ ርዕዮት እስር የሚጨነቅ ናትናኤል መኮንን፣አንዱአለም አረጌ፣አበበ ቀስቶ፣አብታሙ አያሌው፣ዳንኤል ሽበሺ፣የሺዋስ አሰፋ፣አብርሃ ደስታ፣አግባው ሰጠኝ እና ሌሎች የፖለቲካ እስረኛ ለመርሳት እንዴትም አይቻለውም፡፡ ስለ ርዕዮት ፍትህ ማጣት የሚያንገበግበው ሁሉ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ለሰኮንድም አይዘነጋቸውም ፡፡ሁሉም አንድ የሚያደርጋቸው ለነፃነት እና ለፍትህ የከፈሉት ዋጋ ነው ! ይህ ነገራቸው ደግሞ ያስቀናል፡፡ እናም በጎውንም ለማድረግ ብንቀና የሚያስጨንቀን ማን ነው ?”
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላላም ትኑር !

No comments:

Post a Comment

wanted officials