Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, January 21, 2015

ሰማያዊ ፓርቱ እና በሰሜን አሜሪካ የሰማያዊ ፓርቲ ድጋፍ ኮሚቴ በመተባበር ያዘጋጁትን ውይይት ተካሄደ

<<ኢትዮጰያ ውስጥ ያለው ችግር የዘር ፉክክር ነው>>ሲሉ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ተናገሩ።

 ኢሳት ዜና :-ፕሮፌሰር መስፍን ይህን ያሉት ሰማያዊ ፓርቱ እና በሰሜን አሜሪካ የሰማያዊ ፓርቲ ድጋፍ ኮሚቴ በመተባበር ያዘጋጁትን ውይይት ሲከፍቱ ነው።
<<ሁላችንም ስንለወጥ ነው ለውጥ የሚመጣው ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን፤ ከጣሊያን ጊዜ አንስቶ አሁን እስካለንበት ጊዜ ድረስ ባንዳው፣ፖሊሱ፣ባለስልጣኑ ሁሉ በመሸጦነት ማለፋቸውን በማውሳት፤ አንድ ትውልድ ይህን የመሸጦነት ባህል እየተባበረ ከሄደ ለውጥ እንደማይመጣ በአንጽንኦት ተናግረዋል።
ተከታዩ ተናጋሪ ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ደግሞ፦‹ለህወሓቶች ፖለቲካ ማለት ወዳጅና ጠላት የሚለይበትና ፍልሚያ የሚደረግበት ነው ፡፡ አንድ የናዚ ሰውም ፦<<ፖለቲካ ማለት ወዳጅና ጠላት የሚለይበት ሜዳ ነው>> ነው የሚለው፡፡>>ብለዋል።
<<ህወሀቶች ያለ ጠላት መንቀሳቀስ አይችሉም፡፡>>ያሉት ዶክተር ዳኛቸው፤ <<ድህነትንም ጠላት ብለውታል፡፡ ሲጀመር እኛ እና እነሱ ይባልና- ጠላትና ወዳጅ ወደሚለው ያድጋል፡፡›› ብለዋል። ሁላችንም በሀገራችን የባለቤትነት መብት ቢገባንም የሀገሪቱ ፖለቲካ ዝግ ሆኗል ያሉት ዶክተር ዳኛቸው፤ <<ውድድር በሌለበት ቦታ ፍትሐዊ ምርጫ ማድረግ እንደማይቻል ገልፀዋል።
የአዲሲቷ ኢትዮጰያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶ በበኩላቸው፤ <<በጎሳና በዘር ተከፋፈግለናል፤ ሀገራችንን ለመቀየር ከፈለግን ለውጡ ከራሳችን መጀመር አለበት ብለዋል።
<<እኛ ለሀገራችን ዋጋ ካልከፈልን፤ማንም ለኢትዮጰያ ዋጋ ሊከፍልልን አይችልም>>ብለዋል-አቶ ኦባንግ።
የዞን 9 ጦማርያን አባል የሆነችው ሶልያና ሽመልስ በበኩሏ ትንሽ የሚመስሉ ጥረቶችን ማድነቅ እንደሚያስፈልግ በመጥቀስ፤ ቀደም ሲል ጠቀሜታው ብዙም ግምት ያልተሰጠውንና በአሁኑ ወቅት ተጽእኖ እየፈጠረ ያለውን በኢንተርኔት መረጃ የመለዋወጥን  እና የመጻፍን ጉዳይ በተደራጀ መልኩ መጠቀም እንደሚያስፈልግ መክራለች።
በምርጫ 97 ወቅት የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ ሊቀ-መንበር የነበሩት ዳኛ ፍሬህይወት ሳሙኤል በበኩላቸው ኢትዮጰያ ውስጥ የህግ የበላይነት እንደሌለ ምሳሌዎችን በመጥቀስ ተናግረዋል።
ኢትዮጰያ ውስጥ ወደ እስር ቤት የተወረወሩት አንድም በፖለቲካ የተሳተፉ አለያም ድሆች ናቸው ያሉት ዳኛ ፍሬህይወት፤ “የሀብታም ክስ ከፖሊስ አልፎ ፍርድ ቤት አይደርስም>> ብለዋል።
“ለውጥ ይመጣል፡፡ ለውጥ ይሸተኛል”በማለት ንግግራቸውን የጀመሩት ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ናቸው።
<< ለውጡ እንደስከዛሬው እንዳይከሽፍ ግን ፖለቲከኞችና የፖለቲካ ቡድኖችበራሳችን ላይ አብዮት ማምጣት አለብን፡፡>>ያሉት ኢንጂነር ይልቃል << ከእስካሁኑ የተለየ ለውጥ እንዲመጣ የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣን ባለቤት እንዲሆን ማድረግ አለብን›› ብለዋል።
ሰማያዊ ፓርቲ ያዘጋጀውን ይህን ውይይት በርካቶች  በአካል በስብሰባው ቦታ ተገኝተው ከተከታተሉት ታዳሚዎች ባሻገር በርካቶች ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች በስካይፒ የተከትሉት ሲሆን፤ ፓናሊስቶቹ ባቀረቧቸው ሀሳቦች ላይ ውይይት ተካሂዷል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials