Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, January 21, 2015

በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት ባለፉት ሁለት ዓመታት በእጅጉ ማሽቆልቆሉን <፣ያንግ ላይቭስ>> የተሰኘ ተቋም ይፋ አደረገ።


በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት ባለፉት ሁለት ዓመታት በእጅጉ ማሽቆልቆሉን <፣ያንግ ላይቭስ>> የተሰኘ ተቋም ይፋ አደረገ።

ጥር ፲፪(አስራ ሁለት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ልጅ በሆኑት በዶክተር አሉላ ፓንክረስ የሚመራው <፣ያንግ ላይቭስ>> ሰሞኑን ይፋ ባደረገው ጥናት ኢትዮጵያ ውስጥ የትምህርት ደረጃና ጥራት ከክልል-ክልል እንደሚለያይ ጠቁሟል።
ትምህርት ከጀመሩ ተማሪዎች መካከል 17 በመቶ ያህሉ በተለያዩ ችግሮች እንደሚያቆሙ ያመለከተው ጥናቱ፤ ከሚማሩት መካከልም 24 በመቶዎቹ ወደተከታዩ ክፍል ማለፍ እየተሳናቸው እንደሚደግሙ ይጠቁማል።
ዋና ጽህፈት ቤቱ በእንግሊዝ የሆነው<< ያንግ ላይቭስ>> የኢትዮጵያን የትምህርት ጥራት አሰመልክቶ ያጠናውን ይህን ጥናት ሰሞኑን በአዲስ አበባ ይፋ አድርጓል።
ባለፉት አመታት በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቀለ እንደመጣ በርካታ ምሁራን በተደጋጋሚ ሲናገሩ ቆይተዋል።
Young Lives

No comments:

Post a Comment

wanted officials