Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, January 16, 2015

ሰበር ዜና: የጋዜጠኛ ተመስገን ወንድም ታሪኩ ድብደባ እና ዘረፋ በዝዋይ እስር ቤት ፖሊሶች ተፈጸመበት

ሰበር ዜና
የጋዜጠኛ ተመስገን ወንድም ታሪኩ ድብደባ እና ዘረፋ በዝዋይ እስር ቤት ፖሊሶች ተፈጸመበት

'
ታሪኩ ዝዋይ እሥር ቤት ወንድሙን ለማየት ይገባል። እዚያም፣ "ተመስገንን ጥሩልኝ " ሲል ፖሊሶችን ይጠይቃል። በዚህ ግዜ የመቶ ዓለቃ ማዕረግ ያለው ወታደር (ፖሊስ) ተመስገንን መጠየቅ እንደማይችል ይነግረዋል።
ታሪኩም "ምን ተፈጠረ ወንድሜን እንዳልጠይቀው የተከለከልኩት ?" በማለት ለፖሊሱ ጥያቄ ያቀርባል። 
ፖሊሱም በማመናጨቅ "ውጣ" ይለዋል። ነገሩ ያላማረው ታሪኩ ለወንድሙ ያመጣውን ስንቅ እንደያዘ ወደ በሩ ያመራል። ነገር ግን" ውጣ" ያለው ፖሊስ በድጋሚ ታሪኩን እንዲቆም ያዘዋል።
ታሪኩም ወንድሜን ሊያገናኘኝ ነው ብሎ በደስታ ይቆማል። ፖሊሱ በመገናኛ እያወራ " የተመስገን ወንድም ነህ አይደል?."ይለዋል።" አዎ' ብሎ ሳይጨርስ 8ፖሊሶች ታሪኩን ይከቡታል። ለወንድሙ ያመጣውን ምግብ ከደፉ በኅላ የዱላ ውርጅብኝ ያዘንቡበታል። ለ8። ደም በደም እስኪሆን። በድብደባ ከጎዱት በኅላ ወደ አዲስ አበባ መመለሻ የያዘውን ገንዘብ ከኪሱ (700 ብር) ይቀሙትና የእጅ ሥልኩን በመስበር ከግቢ ያስወጡታል።
ታሪኩም በዱላ የተጎዳውን ሰውነቱንና የሚፈሰውን ደም እየጠራረገ መታወቂያውን እስይዞ ገንዘብ ለትራንፖርት ተበድሮ ወደ አዲሥ አበባ ይመለሳል።...ታሪኩ ደስአለኝ በትላንትናው ዕለት በተክለኅይማኖት ሆስፒታል ህክምና ያደረገ ሲሆን፣ ጀርባው ላይ በጠመንጃ ሰደፍ በመመታቱ የአጥንት ስፔሻሊስት እንዲያየው እንደታዘዘለት ለማወቅ ችያለሁ።
ታዲያ የአባት ዕዳ ለልጅ ይተርፋል ይህ አይደል?...
ፍትህ! ፍትህ !

No comments:

Post a Comment

wanted officials