በጣይቱ ሆቴል መቃጠል ህብረተሰቡ ቁጣውን እየገለጸ ነው።
ጥር ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ትናንት እሁድ ጥር 3-2007 ማለዳ ላይ ነበር በ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሰመናዊ ሆቴል የሆነው ታሪካዊው ጣይቱ ሆቴል በእሳት የወደመው።
የዓይን ምስክሮች በወቅቱ እንደተናገሩት፤የእሳት አደጋ ብርጌድ መስሪያ ቤት በሆቴሉ አቅራቢያ ሆኖ ሳለ እሳቱ ከተነሳ በትንሹ ለአንድ ሰኣት ያህል አንድም የ እሳት አደጋ መኪና አለመታዬቱ፣ሰግይተውም ከመጡት ሶስት መኪኖች መካከል አንድኛው ወሃ የለኝም ብሎ እንዲሁ መቆሙ ነው ለአደጋው መክፋትና ለሆቴሉ መውደም ዋነኛው ምክንያት የሆነው። ይህም በርካቶችን አስቆጥቷል። ሌላው የህስብን ቁጣ የቀሰቀሰው ደግሞ የሀገር ቅርስ ከሆነው ታሪካዊ ሆቴል ይሶታ በትንሹ 80 በመቶ ያህሉ ከወደመ በኋላ የኢትዮጵያ ቴሌቪጽንን ቸምሮ ሌሎች የመንግስትና የድርጅት ሚዲያዎች “በጣይቱ ሆቴል የተነሳው አደጋ በ አደጋ ብርጌድ ሰራተኞችና በፖሊስ በተደረገ የተቀናጀ ሰመቻ በቁጥጥር ስር ውሏል” የሚል ሴና ማወጃቸው ነው። ጣይቱ ሆቴል – የአርት ጋለሪው፣የመመገቢያው አዳራሹ፣እንግዳ መቀበያ ክፍሎቹ፣ እና በዛ ያሉ መኝታ ክፍሎቹ በእሳት አደጋው መሉ በሙሉ በ እሳት ወድመዋል። ሀገሬውና የውጪ እንግዶች የሚጎርፉለትና በሆቴሉ የሚገኘወ የኢትዮጵያን ጃዝ ሙዚቃ ምንጪ ጃዝ አምባ ላውንጅ ሙሉ በሙሉ ወድሟል፡፡
ከፎቁ ላይ ያሉት የተለያዩ የትንራንስፓርት እና የጉዞ ትኬት ቢሮዎች እና ህብረት ባንክም እንዲሁ ጋይተዋል።
ከፎቁ ላይ ያሉት የተለያዩ የትንራንስፓርት እና የጉዞ ትኬት ቢሮዎች እና ህብረት ባንክም እንዲሁ ጋይተዋል።
የአደጋው መ ስዔ እስካሁን ያልታወቀ ቢሆንም፤ በማህበራዊ ድረ ገጽ ላይ ከሚንጸባረቁ አስተያዬቶችም ሆነ ለኢሳት ከሚደርሱ እጅግ እርካታ የስልክ መልእክቶች 90 በመቶ ያህሉ መንግስትን ተጠያቂ የሚያደርጉ ናቸው።ከምኒልክና ከጣይቱ ታሪክ ጋር ክፉኛ በተጣላው መንግስት ሆነ ተብሎ ተቃጥሏል ብለው ያመኑ ሰዎች ፤ <<ታሪካዊው የጣይቱ ሆቴል በእሳት መውደሙ ያስቆጫል፤ያንገበግባል፤ ሆኖም የህንጻን እንጅ ታሪክን ማቃጠል አይቻልም ።>>ብለዋል።
በውስጥም፣በውጭም የተፈጠረበትን ፖለቲካዊ ውጥረት ለማስተንፈስና የፖለቲካውን ትኩሳት አቅጣጫ ለማስቀየር መንግስት ሆነ ብሎ ታሪካችንንና ቅርሳችንን አውድማል በማለት አስተያየታቸውን ያሰፈሩና የገለጹም እጅግ በርካታዎች ናቸው።
ራሄል ገብረ እግሲአብሄር የተባለች ወጣት ደግሞ፦ <<_የጣይቱ እሳት ቢጠፋም፤ የኔ የውስጥ እሳት ግን አልጠፋም፤ ሃዘኑ እየለበለበኝ ነው።>>ብላለች።
ወደ ኢሳት ስልክ በመደወል ቅሬታቸውንና ቁጣቸውን የገለጹም በርካቶች ናቸው።

ሰዓሊ አምሳሉ ገብረኪዳን አረጋዊ በሰጠው አስተያዬት ፦”ቅርስ ነውና ቢቃጠልም እድሳት ተደርጎለት በአግልግሎቱ እንዲቀጥል መደረግ አለበት፡፡ “ጉዳቱ ከባድ ነው ለዚህ አይመችም” ከተባለም ቀሪው ክፍል ባለበት ሁኔታ ሆኖ በመስህብነቱ መኖር ይኖርበታል፡፡ “አይሆንም” ተብሎ “ቀሪውን ክፍልም ጠራርገን አፈራርሰን ለሌላ ሥራ እናውለዋለን” ከተባለ ግን ያኔ እንዲቃጠል የተደረገው ሆን ተብሎ ቅርስን ለማውደም እንደሆነ እናረጋግጣለን፡፡” 109 ዓመታትን ያስቆጠረው የእቴጌ ጣይቱ ሆቴል ሙሉ ለሙሉ በእንጨት ጣውላ የተሰራ ሲሆን የመጀመሪያው ሥራ አስኪያጅም ሙሴ ፍሬደሪክ ሐል ይባል ነበር::
ጋዜጠኛ ጌታቸው በቀለ ከኦሰሎ በሰጠው አስተያየት ደግሞ፦<<እቴጌ” ብለህ ዘፈንክ ብሎ ፓስፖርት ነጥቆ ከአየር መንገድ የሚመልስ….፣ በወመዘክር ለዘመናት የቆዩ የኢትዮጵያ የታሪክ መፃህፍትን ”ቦታ ጠበበኝ” ብሎ በኪሎ የሚሸጥ ….፣
ለጣይቱ ሆቴል ቅርስነት ጭንቅ ጥብብ ይለዋል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው ብሏል።
ለጣይቱ ሆቴል ቅርስነት ጭንቅ ጥብብ ይለዋል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው ብሏል።
አርቲስት ቴዲ አፍሮ በፌስ ቡክ ገጹ ባሰፈረው አስተያየት፦<<በታላቁ ታሪካዊዉ የአዲስ አበባ የመጀመሪያዉ በሆነዉ በአቴጌ ጣይቱ ሆቴል ላይ በደረሰዉ የእሳት አደጋ እጅጉን አዝነናል….ሆቴሉ በርካታ ስራዎችን የሰራንበት ቦታ ስለነበር ተስስራችን ዉስጣዊ ነበር….የጣይቱ ሆቴል በርካታ ታሪኮችን ይዞ ከትዉልድ ወደትዉልድ ያስተላለፈ ያገር ቅርሰ ነበር…. የኋላዉ ከሌለ የለም የፊቱ>> ብሏል።
No comments:
Post a Comment