Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, January 8, 2015

ኢህአዴግ – በመንግስት በጀት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለመምህራንን እና ለመንግስት ሰራተኞች ስልጠና ሊሰጥ ነው።


ታኀሳስ ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሀገራዊው ምርጫ ጥቂት ወራት በቀሩበት በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ መምህራንና የመንግስት ሰራተኞች ማሰተማራቸውንና ስራቸውን በማቆም ስልጠና እንዲገቡ መታዘዛቸውን ለኢሳት ደረሱት መረጃዎች ያመለክታሉ።
በዚህም መሰረት በባህር ዳር የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ መምህራን ከፊታችን ማክሰኞ ጀምሮ ማስተማራቸውን በማቁዋረጥ ወደ ስልጠና እንዲገቡ ታዘዋል። እንዲሁም በጋሙጎፋ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ስራቸውን በማቆም ወደ ስልጠና እየገቡ መሆናቸውን  ለኢሳት ገልጸዋል።
ወቅቱ የመጀመሪያ ሴሚስተር ማጠቃለያ ከመሆኑ አኳያ መምህራን_ ለተማሪዎች ቲቶሪያል ለመስጠት በሚዘጋጁበት በአሁኑ ጊዜ ወደ ስልጠና ግቡ መባላቸው ፤ በትምህርት አሰጣጥ ሂደቱ ላይም ሆነ በስራቸው ከፍ ያለ ጉዳት እንደሚያስከትልባቸው መምራኑ መናገራቸውን፤የዘጋቢያችን ሪፖርት ያመለክታል።
ስሜን ብጠቅስ ጉዳት ይደርስብኛል ያሉ የጋሙጎፋ ዞን  ካምቦ ወረዳ የመንግስት ሰራተኛ በበኩላቸው  ለመንግስት ሰራተኞች  ከሰኞ  እለት  ጀምሮ  ለ15 ቀናት የሚቆይ ስልጠና እየተሰጠ  መሆኑን  ተናግረዋል። በስልጠናው መሰጠት ላይ ቅሬታ ያነሱ ሰራተኞችም የተቃዋሚ ደጋፊዎች ይሆናሉ በሚል ጥርጣሬ እየታሰሩ መሆናቸውን የጠቀሱት  እኚሁ የመንግስት ሰራተኛ፤  በዞኑ በሚገኙ ወረዳዎች የተቃዋሚ ደጋፊዎች ናቸው የሚባሉ ሰዎች   ውሃ የሚያገኙበትን ቧንቧ ከመቁረጥ ጀምሮ ቤታቸውን እስከማፍረስ የሚደርስ  በደል እየተፈጸመባቸው እንደሆነ ተናግረዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials