Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, January 25, 2015

የወያኔ ቅልብ ወታደሮች ዳግም የሰላማዊ ሰልፈኞችን ደም አፈሰሱ * ነብሰ ጡር ሳይቀር በቆመጥ ቀጠቀጡ

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በ ጥር 17/2007 ዓም በ አዲስ አበባ ና በሌሎች ከተሞች መንግስት አንድነት ፓርቲን ተለጣፊ በማበጀት ከማፍርስ ይታቀብ  ምርጫው ፍትሃዊ ይሁን በሚሉ አጀንዳዎች ሰልፍ ለማድረግ ቅስቀሳ የጀመረው ቀደም ብሎ ነው። ይሁንና የ አዲስ አበባ ከተማ መስተዳድረ ግን ሰልፉን አልፈቅድም ቢልም አንድነቶች መብት አይለመንም በሚል መርህ በዛሬው ዕለት ድብደባ በይፋ እስኪፈጸምባቸው ድረስ እየተንቀሳቀሱ ነበረ።

ይሁንና ቁራቸው ከ200ያማያንስ የ ፌደራል ፖሊሶች ና ደህንነቶች ሰለፈኞቹ ቢሯቸው አካባቢ እንደተንቀሳቀሱ ከፍተኛ ድብደባ ና ክልከላ ፈጽመውባቸዋል።ቀበና ከሚገኘው የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት የተነሳው ከ 150 በላይ የሚሆን ሰልፈኛ ከጽ/ቤቱ 100 ሜ/ር ርቀት ላይ ከሚጠብቁ ከ500 በላይ ሰልፈኞች ጋር ከመቀላቀላቀላቸው አስቀድሞ የህወሓት/ኢህአዴግ ፖሊሶች ቆርጠው በመግባት ከባድ ድብደባ አድርሰዋል፡፡ አራት ኪሎ፣ በፒያሳና የሰልፉ ማጠናቀቂያ በሆነው ኢቲዮ ኩባ አደባባይ ይጠባበቅ የነረው ሰልፈኛ ሊበተን ችሏል፡፡ ጉዳት የደረሰባችው 24 ሰልፈኞች ህክምና በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡ ፖሊሶች ያደረሱትን ጉዳት በቅርብ ሲከታተሉ የነበሩት የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች የአንድነት አመራሮችን እና ጉዳት ደርሶባቸው በየሆስፒታሉ የሚገኙ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎችን አነጋግረዋል፡፡ የፓርቲው አመራሮች ከአባላትና ከደጋፊዎች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን አንድነት በአዲስ አበባ ተከታታይ የተቃውሞ ሰልፎችን እንደሚያደርግ ይፋ ተደርጓል፡፡ 
አንድነት ፓርቲ ያወጣውን መግለጫ ከዚህ በታች ይመልከቱ፡፡

የፍትህና የነፃነት ጥያቄያችን ደም በማፍሰስ አይቀለበስም!!!
ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ፓርቲያችን አንድነት ገዥው ፓርቲ፣ ምርጫ ቦርድና የገዥው ፓርቲ ልሳን በመሆን እያገለገሉ ያሉ ሚዲያዎች በመተባበር ከምርጫ ለማስወጣትና ተለጣፊ አንድነት ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ መጥራቱ የሚታወቅ ነው፡፡
የተቃውሞ ሰልፉን ጥር 17 ቀን 2007 ዓ.ም እንደምናከናውን ለአዲስ አበባ መስተዳድር ብናሳውቅም መስተዳድሩ በ12 ሰዓት ውስጥ በፅሁፍ ምላሽ መስጠት ባለመቻሉ ሰልፉ እውቅና አለው፡፡ መስተዳድሩ ግን የተጣለበትን ሃላፊነት ከመወጣት ይልቅ ወደ ጎን በመግፋት የተወሰኑና የማይታወቁ ግለሰቦች ፔቲሽን ተፈራርመው አምጥተዋል በማለት ብዥታ ለመፍጠር ሞክሯል፡፡ ፓርቲያችን ህጉን ጠብቆ ህጋዊ የሆነ ሰልፍ ለማካሄድ ቢሞክርም አሁንም ሃላፊነት በጎደለው ሁኔታ የፓርቲያችን ከፍተኛ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ጭካኔ በተመላበት ሁኔታ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል፡፡ በተደጋጋሚ እንዳየነው ፖሊስ ደንብ ማስከበር ሲገባው አድሎ ለፈፀመው አካል በመወገን ድብደባ መፈፀሙ ከወገንተኝነት ያልፀዳ መሆኑን እንድናረጋግጥ አድርጎናል፡፡
ጥያቄያችን አሁንም የፍትህ፣ የእኩልነትና ህግ እንዲጠበቅ የማድረግ ነው፡፡ ገዥው ፓርቲ የመንግስትነት ስልጣኑን በመጠቀም የስልጣን ዘመኑን ለማስረዘም እየከወነ ያለውን ሴራ ማስቆም ነው፡፡ ጥያቄያችን የነፃነትና ያልተሸራረፈ ዴሞክራሲ ይረጋገጥ የሚል ነው፡፡
ጥቄያችን ምርጫ ቦርድ የገዥው ፓርቲ አጋር መሆኑ ቀርቶ ገለልተኛ ሚናውን ይወጣ የሚል ነው፡፡ እነዚህ ጥያቄዎቻችን ደግሞ ደም በማሰስ፤ በድብደባም ሆነ በእስር ፈፅሞ አይቆሙም፡፡ ትግላችን የአንድ ፓርቲ የበላይነት አገዛዝ እስከሚያበቃ ድረስ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
በሚቀጥለው ሳምንትም በተለያዩ ከተሞችና በአዲስ አበባ የሰላማዊ ተቃውሞ ድምፃችንን ከፍ አድርገን እናሰማለን፡፡ ትግሉ ይቀጥላል፡፡
ድል የህዝብ ነው!!
በዛሬው ዕለት በህወሃት/ኢህአዴግ ፖሊሶች አንድነት ፓርቲ የጠራውን ሰልፍ ለመበተን ከፍተኛ ድብደባ 
ፈጽሞባቸዋል።
 ድብደባው የአካል ማጉደልንም ያካተተ ነው፡፡ ጋዜጠኛ ስለሺ ሐጎስና አቶ ዳግማዊ ተሰማ ራሳቸውን ስተዋል፡፡
መስከረም ያረጋል በቅርብ በሰላ ፁሁፎ ዋ የሚሊዮኖች ድምፅ ጋዜጣ ላይ የምትፅፈው ወጣት ከፍተኛ ድብደባ ተፈፃሞባታል ስርአቱን በመቃወም እሶና ጎደኞቻ በስርአቱ አገልጋይ በሆኑ የፖሊስ ሀይልና በተቀላቀለበት ሁኔታ ጉዳት ደርሶባቸዋል

መስከረም ያረጋል 

በቅርብ በሰላ ፁሁፎ ዋ የሚሊዮኖች ድምፅ ጋዜጣ ላይ የምትፅፈው ወጣት ከፍተኛ ድብደባ  ተፈፃሞባታል ስርአቱን በመቃወም እሶና ጎደኞቻ  በስርአቱ አገልጋይ በሆኑ የፖሊስ  ሀይልና በተቀላቀለበት  ሁኔታ ጉዳት ደርሶባቸዋል
 
የተጎጂዋች ቁጥር ከፍተኛ ነው ብዙሀኑ በጣም ተጎድቶል ሴት ወንድ ትልቅ ትንሽ ሳይል ስርአቱ የአውሬነት ተግባር ተፈጽሞባቸዋል። አሁንም በፖሊስ እጅ ሆነው የሚደበደቡ እንዳሉ መረጃው ያሳያል በአንባገነኑ ስርዓት ከፍተኛ ድብደባ ከተፈፀመባቸው አመራር አባላትና አባላት መካከል፡-
1. አቶ አስራት አብርሃም (የህዝብ ግንኙነት ተጠባባቂ ሃላፊ)
2. አቶ ዳንኤል ተፈራ (የውጭ ጉዳይ ሃላፊ)
3. አቶ ብሩ ብርመጅ (የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊ)
4. አቶ ፀጋየ አላምረው (ምክትል አፈ-ጉባኤ)
5. አቶ አሻግሬ መሸሻ (የሰሜን ቀጠና ሃላፊ)
6. አቶ ሰለሞን ስዩም (የኤዲቶሪያል ቦርድ ሰብሳቢ)
7. ወ/ት ልዕልና ጉግሳ (የም/ቤት አባል)
8. አቶ ዳግማዊ ተሰማ (የም/ቤት አባል)
9. ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጎስ
10. አቶ ስንታየሁ ቸኮል (የአዲስ አበባ የወጣቶች ጉዳይ ሃላፊ)
11. አቶ አሸናፊ አሳምረው (የወረዳ አመራር)
12. አቶ ኢሳያስ ቱሉ (አባል)
13. ወ/ት መስከረም ያረጋል (አባል)
14. አቶ ሃይሉ ግዛው (የወረዳ ሰብሳቢ)
15. አቶ አዲሱ መኮንን (የወረዳ ሰብሳቢ)
16. አቶ ሲሳይ ካሴ (አባል)
17. አቶ ወጋየሁ አድማሴ (አባል)
18. አቶ ክብረት ሃይሉ (የም/ቤት አባል)
19. አቶ ስለሺ ደቻሳ (አባል)
20. አቶ ማሩ አካሉ (አባል)
21. አቶ ክፍሉ በዳኔ (አባል)
22. አቶ ፋሲካ አዱኛ (የወረዳ አመራር)
23. ወ/ሮ ገነት ግርማ (የወረዳ አመራር)
24. ተስፋየ ብዙነህ (አባል) ሲሆኑ በርካቶች የደረሱበት አልታወቀም፡፡ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ህክምና እየተከታተሉ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን ሪፖርት እየተከታተልን እናቀርባለን፡፡
የነፃነት ጥያቄው በድብደባ አይቀለበስም



udj 6     udj 10  udj 9         
















No comments:

Post a Comment

wanted officials