የኤርትራው ፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከአገር ውስጥ ጋዜጣኛ ጋር ባደረግጉት ቃለ-መጠይቅ በአገር ውስጥ ጉዳይ ላይ ያተኮሩ ነጥቦችን አንስተዋል። አለም አቀፍ ነጥቦችንም ዳስሰዋል።
ዋሽንግተን ዲሲ—
የኤርትራው ፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የአውሮጳውያን አዲስ አመትን መስረት በማድረግ ከአገር ውስጥ ጋዜጣኛ ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ በአገር ጉዳይ ላይ ያተኮሩ ነጥቦችን አንስተዋል። አለም አቀፍ ነጥቦችንም ዳስሰዋል።
የኤርትራው ፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የአውሮጳውያን አዲስ አመትን መስረት በማድረግ ከአገር ውስጥ ጋዜጣኛ ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ በአገር ጉዳይ ላይ ያተኮሩ ነጥቦችን አንስተዋል። አለም አቀፍ ነጥቦችንም ዳስሰዋል።
ከ 15 አመታት በፊት ጸድቆ የነበረው የሀገሪቱ ህገ-መንግስት ሳይታወጅ እንደሞተ ገልጸው አዲስ ህገ-መንግስት የሚያረቅ አካል እንደተመደበ ጠቅሰዋል። በብዛት ከአገር እየተሰደዱ ስላሉት ወጣቶች ጉዳይም በኤርትራ ላይ ከታወጀው የማዳከም ጦርነት ጋር የተሳሰረ ነው ብለዋል። ከሰፊው ቃለ መጠይቅ ጥቂቶቹን ጨምቀን እናቀርባለን።
“በአስራ አምስት አመታት ውስጥ ህልውናችንን፣ ሉአላዊነታችንን፣ እድገታችንንና ልማታችንን የገጠሙት ተግዳሮቶች እንደምክንያት ለማቅረብ አልፈልግም። አብዛኛው የፖለቲካ እርምጃ ጉዟችን በእንደዚህ አይነት ትርምስና በውጭ ጣልቃ መግባት አንዳንዴ አውሎ ነፋስ ሌላ ጌዜ ደግሞ ማዕበል፣ አጥሮችና እንቅፋቶች እየተፈጠሩ በመሄዳቸው ህገ-መንገቱ ሳይታወጅ ሞቷል” ብለዋል ፕረዚዳንት ኢሳያስ።
“ባለፉት አስራ አምስት አመታት ውስጥ የታወጀብን ኢኮኖምያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማስያዊ እንዲሁም የስም ማጥፋት ጦርነቱ ተደማምሮ ሲታይ እኛን ለማጫጨት የታቀደ ጦርነት እንደሆነ ግልጽ ነው” ሲሉም ፕረዚዳንቱ ከሰዋል። ሙሉዉን ዘገባ ያድምጡ።http://amharic.voanews.com/content/article/2583372.html
No comments:
Post a Comment