ጋዜጠኝነት በሀገራችን አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ በመሆኑ የስራ አጋሮቹ ተሰደዋል፡፡ እሱ ግን ከፍተኛ ጫና ቢፈጠርበትም፤ ምንም ቢፈጠርበትም ለሀገሩ የቻለውን ለማበርከት ስደትን አልመረጠም፤ እዚሁ ሆኖ መታገልን መርጦ ከወራቶች በፊት አንድነት ፓርቲን ተቀላቅሎ የፓርቲው የንድፈ ሀሳብ ዳንዲ መፅሄት ላይ ዋና አዘጋጅ ሆኖ እየሰራ ይገኛል፡፡
የቅርብ ጓደኛዮ የሆነው ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጎስ ጋር ስደውልለት አናንያ እንደታሰረ አረዳኝ በጣም አዘንኩ አናንያ በጣም ይቅርብ ጓዴ ነው፤ ገና ብዙ የሚሰራ ይቺ ሀገራችን ተለውጣ በዲሚክራሲ አብባ የሁላችንም እንድትሆን የሞቀ ሀይል ነበረው፡፡ ሁላችንም ያንተን ያህል ብንሆን ይቺ ሀራችን ዛሬውኑ ትለወጥ ነበር፡፡
ከጎንህ ብዙዎች አለን እስር አይገድበንም አንተ ብትታሰርም ሀሳብህ ግን ከኛ ጋር ነው፡፡